የመንግስትን ጥረትና የኢንተርፕራይዞች አቅም ደጋፊው የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ በኢትዮጵያ ከተጀመረ ከ19ዎቹ አጋማሽ አንስቶ ላለፉት ዓመታት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የገቢ አቅም በማሳደግና ድህነትን በማስወገድ ሰፊ ድርሻ አበርክቷል ። ዘርፉ በርካታ ባለሃብቶች የተፈለፈሉበት ፣ለመካከለኛ... Read more »

እንደ ሻማ ቀልጦ ለሌላው ብርሃን መሆን

ዛሬ ስለ ማይሞቱ ህያው ነፍሶች እናወራለን። ከሰው ወገን ተፈጥረው ለዘላለም ስለሚኖሩ የማይሞቱ ህያው ነፍሶች እነግራችኋለሁ። ይሄ ዓለም ከጥንት እስከዛሬ በነጻ ፍቃዳቸው ለሚኖሩ በርካታ ሰዎች የጋራ መኖሪያ ነው። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በምድር ላይ... Read more »

“ሁላችንም ቆም ብለን ለምን እዚህ ደረጃ ደረስን፤ ከዚህ ችግርስ እንዴት እንውጣ ብለን ማሰብ አለብን”-ፓስተር ጻዲቁ አብዶ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት

አንድ አገር እንደ አገር እንዲቀጥል ከሚያስፈልጉ ነገሮች መካከል ሰላም ግንባር ቀደሙን ሚና ይጫወታል። ሰላም ካለ ወጥቶ መግባት፣ ሰርቶ መብላት፣ ተምሮ መለወጥ በአጠቃላይ ያሰቡትን ሁሉ ማሳካቱ ብዙ ከባድ አይሆንም። ነገር ግን ሰላም በአንድም... Read more »

«ብልህ ሆነን ነገን በማሰብ ዛሬ ላይ ሰከን ማለት ካልቻልን እንደ አገርና ሕዝብ መቀጠላችን አጠያያቂ ነው» – ፓስተር ጻድቁ አብዶ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንትና የአገር ሽማግሌ

አዲስ አበባ፦ ብልህና አስተዋይ ሆነን ነገን በማሰብ ዛሬ ላይ ሰከን ማለት ካልቻልን እንደ አገርና ሕዝብ መቀጠላችን አጠያያቂ እንደሚሆን የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንትና የአገር ሽማግሌ ፓስተር ጻድቁ አብዶ ገለጹ። ፓስተር ጻድቁ... Read more »

ባዕድ ነገሮች ከምግብ ጋር ቀላቅሎ ለገበያ እንዳይቀርቡ ለማድረግ ምን እየተሰራ ነው?

መቼም የአመት በዓል ሰሞን በሃገራችን ሃብታሙም ደሃውም፣ ሴት ወንዱ ሁሉም እንደየአቅሙ በዓሉን በደስታ እና በሰላም ከቤተሰቦቹ፣ ከዘመዶቹ፣ ከጎረቤቶቹ ጋር እየተጠራሩ ለማሳለፍ ከገበያ የሚገዙ ነገሮችን ለመግዛት ሸማቹ ከላይ ታች፤ ከዚያ ከዚህ ያለው የሰዎች... Read more »

የጉዲፈቻ ሕግ በኢትዮጵያ

 ጉዲፈቻ የሚለው ቃል ከኦሮምኛ ቋንቋ በቀጥታ ወደ አማርኛ የተወሰደ ሲሆን፤ ትርጓሜውም ተፈጥሮዓዊ ወላጅነትና የልጁ የሥጋ ዝምድ በተለያዩ ምክንያት ሳይኖር ሲቀር ከሌላ ሰው አብራክ የተወለደን ልጅ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ጥቅሙን ጠብቆ እንደ አብራክ ክፋይ... Read more »

በሽታው እስኪጠፋ እንደ ሰሞነ ህማማቱ እናድርግ

ፈጣሪ ለሰው ልጆች ምህረትና ድኅነት ለመስጠት ሲል ብዙ መከራና ስቃየን ተቀብሏል ። ተገርፏል፣ ተደብድቧል፣ተተፍቶበታል፣በመስቀል ላይ ተሰቅሏል፣ ሞቷል ፣ከሙታን ተለይቶም በትንሳኤው ብርሃን ተነስቷል። እነዚህን የክርስቶስ መከራዎች ሁሌም በሕይወት መስመራችን የምናስባቸው ናቸው ። በዚህ... Read more »

የፋሲካ በዓል ገበያ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ነጋዴዎች ገለጹ

 አዲስ አበባ፡- የዘንድሮ የፋሲካ በዓል የገበያ ሁኔታ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ጭማሪ ማሳየቱን በተለምዶ ሰሜን ማዘጋጃና አራት ኪሎ የበዓል ወቅት ገበያዎች ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችና ሸማቾች ገለጹ። ዝግጅት ክፍሉ ቅኝት ባደረገባቸው በተለምዶ... Read more »

በምርጫው ኢትዮጵያ ታሸንፍ!

አንድ ሀገር በምርጫ አሸነፈች/አሸነፈ የሚባለው ምርጫው ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ያችን/ያንን ሀገር ማሻገር የሚያስችል አቅም ሲፈጥርና በተጨባጭም ማሻገር ሲችል ነው ። ለዚህ ደግሞ መላው ሕዝብ እንደ ሕዝብ ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እንደ አዋላጅ አስተዋጽኦቸው... Read more »

ከሰባት ሺ በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሰባት ሺ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ከ26 መንግሥታዊ ካልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር ተፈራረመ፡፡ የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ትናንት በተከናወነበት ወቅት የቢሮው የሴፍቲኔት... Read more »