ክበባትና ጥበባት በውበት

በክበባት ቤት ጥበባት እንዳሉ ሁሉ በጥበባት ቤትም ሌላ ትናንሽ ክበባት መኖራቸው እውነት ነው። ቅሉ ዛሬ ሳይሆን ያኔ…ክበባት ዋናዎቹን ጥበባት ለማዘጋጀት የሚጣለው ድፍድፍና ጥንስሱ እንደሚጠነሰስበት ማጀት ወይም መድኃኒት እንደሚቀመርባቸው ትንንሽ ቤተ ሙከራዎች ነበሩ... Read more »

ቲያጥሮን ምን በላው?

ቲያጥሮንን የበላ፣ ቲያትርን የነከሰ ጥርስ መኖሩ እርግጥ ነው። ውስጥ ውስጡን ደግሞ ጥቁር ሀሩንም ሆነ ወርቃማውን ቲያትር ሽበት ወሮታል። በሆነ ዘመን ላይ ደግሞ ቲያጥሮንን አስረክበን ቲያትርን ተቀብለናል። የተቀበልነውም በሽበት ተወሮ ከአናቱ ላይ ችፍፍ... Read more »

ዶቃን ከማሰሪያው

  ዶቃ ከምን? ካሉ…ዶቃ ከማሰሪያው ነው። በኢትዮጵያ ሲኒማ ላይ ውበትን ደርቦ ከአንገት እንደ ጌጥ ፈርጥ የተንጠለጠለው “ዶቃ” ፊልም አሁን ደግሞ ከሌላ ደማቅ የማሰሪያ ክር ጋር ለመታየት በቅቷል። ጥንቱን ዶቃ የሀገሬው ልጃገረድ ሁሉ... Read more »

 ‹‹ሸሙኔ››የቋንቋናወግ ጨዋታ

የመጽሐፉ ስም፡- ሸሙኔ ደራሲ፡- መስፍን ወንድወሰን የህትመት ዘመን፡- 2016 ዓ.ም የገጽ ብዛት፡- 217 የመሸጫ ዋጋ፡- 496 ብር መጀመሪያ መጽሐፉ በማህበራዊ ገጾች ላይ በአንዳንድ ሰዎች ሲዘዋወር ተመለከትኩ። መጽሐፍ ፌስቡክ ላይ ማስተዋወቅ የተለመደ ስለሆነ... Read more »

 ቀታሪ ግጥም

በዚህ ምጥን ሥነ-ጽሑፋዊ ዳሰሳ ጽሑፍ ሁለት ጉምቱ የኪነጥበብ ሰው የሆኑት ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው በ‹‹ውስጠት›› እና አሰፋ ጉያ በ‹‹የከንፈር ወዳጅ›› የግጥም መድብሎቻቸው ያካተቷቸውን ‹‹ሰው እና ሚዛን የለሽ ሚዛን›› ግጥሞችን እንቃኛለን። መቃኛችን ቃል ነው።... Read more »

 ከካሜራ በስተጀርባ

ከካሜራ በስተጀርባ ብዙ ጉዳዮች ሆድና ጀርባ ናቸው ከቴሌቪዥን መስኮት ውስጥ እንደ ፊት መስታየት የምንመለከታቸው ምስሎች ወደ ገሀዱ ዓለም ሲመጡ ግን ያንኑ መሳይ እውነተኛ ምስል አያስመለክቱንም የመስታየቱን አቅጣጫ እየዘወሩ ሲያስመለክቱን የነበሩ ሰዎችን ምስል... Read more »

የቃላት መርፌ

ቃላት መርፌ ናቸው። ቃላት ክር ናቸው። ቃላት ጨርቅና የመድኃኒት ጠብታም ናቸው። ሁሉም ነገር የሚጀምረውም ከቃል ነው። እኛ የሰው ልጆችም ብንሆን…በሚታየውም ሆነ በማይታየው ዓለም ውስጥ ቃላት እምቅ የስሜትና የመንፈስ ንጥረ አካላት ናቸው። ሰማይና... Read more »

 የጉለሌው ሰካራም

በ1941 ዓ.ም ነበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው አጭር ልቦለድ የተጻፈው:: ልቦለዱም “የጉለሌው ሰካራም” ነበር:: ደራሲ ተመስገን ገብሬ አስቀድሞ ተነስቶ ጻፈው። በወቅቱም ተአምር አያልቅ…አጃኢብ! ተባለለት። ታሪኩ የአንድ ተራ የጉለሌ ሰካራም ታሪክ ቢመስልም ከባህር ውሃው... Read more »

 የንባብ እርግማን

አንድ ትልቅ ደራሲ ነበር፤ ንባብ ለዚህ ትውልድ እርግማን ሆኗል ሲል ሰማሁት። አባባሉ አጥንቴን ሰብሮ ስለገባ ቃሉን ተውሼ ብዙ ላሰላስልበት ፈለግኩኝ። እንዴትስ ያለው እርግማን ይሆን? በማንና እንዴትስ ተረገምን? ያ የረገመንስ ማነው? እያልኩ ስብሰለሰል... Read more »

 ዶሳይስ

“ዶሳይስ” ከደራሲና ገጣሚ ኩሪ አየለ ኃይሌ ከሰሞኑ ለአንባቢያን የቀረበ ምርጥ የመጽሐፍ ጦማር ነው። ከዚህ ቀደም የግጥም መድብሏን ጨምሮ ሁለት መጻሕፍትን ያበረከተችልን ደራሲዋ ለሦስተኛው በዶሳይስ መጥታለች። የአሁኑ ዶሳይስ መጽሐፏ በአጫጭር ልቦለዶች ታሪክ ተሰባጥሮ... Read more »