
በአንድ ወቅት ብዙዎችን “ማነው?” ያስባለውና በድምጹ፣ በእንቅስቃሴውና በሙዚቃ ቪዲዮዎቹ ጥራት የተደነቁበት፣ የአፋን ኦሮሞ ድምጻዊው ቀመር ዩሱፍ የሙዚቃ ቪድዮ ከወጣ 17 ዓመታትን ተሻገረ። በሙዚቃ ቪድዮው ላይ “ሄሎ”፣ “ኦሮሚያ”፣ “ነነዌ” እና ሌሎችም ተወዳጅ ሙዚቃዎቹ... Read more »

ከሰባት ዓመታት ድካም በኋላ፤ በ8ኛው ወር ላይ ስምንተኛውን አልበሟን አስደመጠች። ከጥበብ አድማስ ባሻገር፣ ከጥበብ ሰማይ በታች እልፍ ክዋክብትን አስከትላ ደጃዝማችነቷን አሳይታለች። ‹ደጅ ለጥበብ፣ አዝማች በሙዚቃ› ደርሰው ሰሞነኛውን ውብ አድርገውታል። ዛሬም ድረስ ከሙዚቃዎቿ... Read more »

ከዘመናት በአንዱ ዘመን፤ ጥበብም እንዲህ ያለውን ልጅ ወለደች። ልጁም፤ በሙዚቃ ቤት አድጎ፤ ሙዚቃን ከልቡ ኖሮ ከልቡ ሠራት። የሙዚቃው የአጥቢያ ኮከብ፤ ኮሎኔል ሳህሌ ደጋጎ…ከስንት አንድ እንደሚወረወሩቱ አጥቢያ ኮከብ ሁሉ፤ እሱም ከስንት አንዴ ከሚወጡት... Read more »

ሰዓሊው- ከእንቆቅልሽ መጨረሻው ጋር ተያይዞ ከሄደ እልፍ ዓመታት ባእተዋል:: ስሙ ግን ዛሬም ድረስ ከምድሩ ነፋስ ጋር እየነፈሰ፣ ከሰማዩ ዝናብ ጋር ሁሉ ይዘንባል:: ከጉና ተራራ አናት ጉብ ብሎ ቁልቁል ሀገሩን ይመለከታል:: ከራስ ዳሽን... Read more »

ማን አልሞሽ? ያሏት ከእንቡጥ አበባ የተገኘች እጹብ ቅመም መሳይ…ታለመች በፍቅር፣ ታለመች በጥበብ፤ መጣች ደግሞ ከሰለሞን መጎናጸፊያ ንጥት! ፍክት! ያለውን የጥበብ ቀሚሷን ለብሳ፣ ጸአዳ ነጠላዋን አገልድማ፣ ውብ ደመግቡ ፊቷን በማይለያት ፈገግታ የመስከረምን ፀሐይ... Read more »

ሥራና መልኩ ዛሬም ቢሆን ከብዙዎቻችን አዕምሮ አይጠፋም። ምክንያቱም ከብዙ ዓመታት በፊት የወደድናቸውንና ዛሬ እንደ ትዝታ የሆኑብንን ቲያትሮች በመድረክ ላይ ሲጫወት ተመልክተነዋል። ከዚህ የምንበልጠው ደግሞ፤ ሁላችንም አንዲት የቴሌቪዥን ጣቢያ ብቻ በምንመለከትበት በዚያ ዘመን፣... Read more »
ስምን መልዓክ ያውጣው፤ ስሙም “መላኩ አሻግሬ” ሆነ:: መላኩም ወዲያ አሻግሮ ጥበብን አየ:: ገና ብዙዎች ያልተዋወቁትን ቲያትር በአንቀልባው አዝሎ፣ ከአንደኛው የዘመን ጋራ ወደ ሌላኛው አሻገረ:: ታዲያ ከዚህ በላይ የተቀደሰ ማሻገር ምንስ አለ? ዳሩ... Read more »

“መቼ ነው? ዛሬ ነው? ነገ ነው? ድምጿን የምንሰማው?” የእርሷን ሙዚቃ ያጣጣሙ ሁሉ ዘወትር የሚሉት ይህንን ነው። ብዙዎች ያንን መረዋ ድምጽ፣ የአዕዋፍ ዝማሬ የመሰለውን ዜማ ለመስማት ናፍቀዋል። እንደ ሰሊሆም ወንዝ ልብን የሚያረሰርሱትን፣ እንደ... Read more »

አንተ ማነህ? ብለው ይጠይቁታል። እርሱም ሌላ ምላሽ የለውም፤ ሁልጊዜም መልሱ “እኔ የሥነ ጽሑፍ ወዛደር ነኝ” የሚል ነው። ከስሞች ሁሉ መርጦ ይህን ስም ለራሱ ሰየመ። የከፋው ሆድ የባሰው ዕለት ስሜቱን መቋጠሪያ፣ ለእንባው ማጀቢያ፣... Read more »

ሕይወት ሸክላ ናት። አንድም ድንገት ከዓለም እጅ አምልጣና ከምድር የሞት ወለል ላይ ተጋጭታ የምትሰበር ናት። ሁለትም ደግሞ፤ እሷም እንደ ሸክላ ስሪቷ ከአፈር ነውና ድንገት ብን ብላ አፈር መግባቷ ነው። “ሰው ክፉም ሠራ... Read more »