
በቶኪዮ የሚካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሊጀመር ዛሬ 64 ቀን ይቀረዋል። በዚህ ትልቅ የአትሌቲክስ መድረክ በመካከለኛና ረጅም ርቀት እንዲሁም በማራቶን ውጤታማ ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁ ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነች። ለዚህም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ... Read more »

የ2025 የቶኪዮ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሊካሄድ ከሁለት ወር ያልበለጠ ጊዜ ይቀረዋል። ከመካከለኛ እስከ ረጅም ርቀት እንዲሁም ማራቶን ለውጤት ከሚጠበቁ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያም በዓለም ሻምፒዮናው በተለያዩ ርቀቶች የሚወክሏትን አትሌቶች ከወዲሁ እየለየች ትገኛለች።... Read more »

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ የሀገር ውስጥ ውድድሮች ታሪክ አንጋፋ ከሆኑ መድረኮች አንዱ በጀግናውና ታሪካዊው አትሌት የተሰየመው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ተጠቃሽ ነው። በርካታ የረጅም ርቀት አትሌቶችን በማፎካከር የሚታወቀው ይህ ዓመታዊ የአርባ ሁለት ኪሎ ሜትር... Read more »

የሂውጂን ዳይመንድ ሊግ ዛሬ ሲካሄድ በተለያዩ ርቀቶች በርካታ ክዋክብት አትሌቶችን ያፋልማል። በሴቶች 5ሺ ሜትር የሚደረገው ፉክክር ግን ከሁሉም በላይ የርቀቱን በርካታ ክዋክብት አትሌቶች በማፋለም ይበልጥ ትኩረት አግኝቷል። የ5ሺ ሜትሩ ፍልሚያ የርቀቱን አምስት... Read more »

የአትሌቲክሱ ዓለም ነገ ሙሉ ትኩረቱ ወደ አሜሪካ ኦሪገን ግዛት ሂውጂን ዳይመንድ ሊግ ይሆናል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከአርባ ሀገራት የተውጣጡ ከ300 በላይ ክዋክብት አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች በሀይዋርድ ፊልድ በሚካሄደው የሂውጂን ዳይመንድ ሊግ መፋለማቸው... Read more »

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከትናንት በስቲያ ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ አስር ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎች ማሳለፉ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ውዝግቦች የተነሱ ሲሆን፣ ፌዴሬሽኑም ትናንት በጋዜጣዊ መግለጫ ምላሽ ሰጥቶባቸዋል። የፌዴሬሽኑ... Read more »

የጃፓኗ ከተማ ካሳማ ለአዲስ አበባ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ የቅርጫት ኳሶች ድጋፍ አበረከተች። የጃፓን ኤምባሲ በኢትዮጵያ ከትናንት በስቲያ ከካሳማ ከተማ የተበረከቱትን የዊልቼር ቅርጫት ኳሶች ተረክቦ ለአዲስ አበባ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ ማስረከቡን ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ... Read more »

ከጊዜ ወደ ጌዜ ተወዳዳሪነት እያየለ በመጣበት የስፖርት ዓለም፣ በሕዝብ ዘንድ አድናቆትንና ዝናን ያተረፉ ንጹህ ላባቸውን ጠብ አድርገው ለውጤት ዘወትር የሚታትሩ በድንቅ ሥነ ምግባር የታነፁ ስፖርተኞች በርካቶች ናቸው። ከዚህ በተቃርኖ በተለያዩ ምክንያቶች ዝናን፤... Read more »

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ለስምንተኛ ዙር በስምንት የስፖርት ዓይነቶች ያሠለጠናቸውን ስፖርተኞች ከትናንት በስቲያ አስመርቋል። የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ባለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት በስምንት ስፖርት ዓይነቶች ያሠለጠናቸውን 43 ሴት እና 57 ወንድ በድምሩ 100 ተተኪ... Read more »

የኦሊምፒክና መላ አፍሪካ ጨዋታን ፅንሰ ሃሳብ አንግቦ የሚካሄደው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ተቋርጦ በመቆየቱ ብዙዎች ይቆጫሉ። አንዱ የቁጭታቸው ምክንያት ደግሞ እንደ ሀገር ተተኪ ስፖርተኞችን ማግኘት የሚቻልበት እድል በመቅረቱ ነው። በእርግጥም... Read more »