እስራኤል በየመን ወደቦች ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች

እስራኤል በየመን ሁቲዎች በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች የሚገኙ ሶስት ወደቦች እና የኃይል ማመንጫ ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች። እስራኤል በሁዳይዳህ፣ ራስ ኢሳ እና ሳይፍ ወደቦች ላይ የፈጸመቻቸውን ጥቃቶች ተከትሎ፤ ሁለት ሚሳኤሎች ከየመን መወንጨፋቸውን የእስራኤል መከላከያ... Read more »

ትራምፕ የቀድሞ ወዳጃቸውን ፓርቲ አጣጣሉት

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሊየነሩ ኢሎን መስክ የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋሙን ‹‹የማይረባ›› ተግባር እንደሆነ በመግለጽ አጣጥለውታል፡፡ ትራምፕ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ‹‹ሦስተኛ የፖለቲካ ፓርቲ መመሥረት የማይረባ ተግባር ነው፡፡ እስካሁን ያለን የሁለት ፓርቲ የፖለቲካ ሥርዓት ነው፡፡... Read more »

ሃማስ ለተኩስ አቁም ዕቅዱ አዎንታዊ ምላሽ መስጠቱን አስታወቀ

የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሃማስ፤ አሜሪካ ላቀረበችው የ60 ቀናት የጋዛ የተኩስ አቁም እቅድ አዎንታዊ ምላሽ መስጠቱን አስታውቋል። ቡድኑ ባወጣው መግለጫ፣ በተኩስ አቁም እቅዱ ያለውን አቋም ለአሸማጋዮቹ ግብጽና ኳታር አሳውቋል። ‹‹ንቅናቄው ምላሹን ለአደራዳሪዎቹ ገልጿል።... Read more »

 በአሜሪካ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ24 ሰዎች በላይ ሞቱ

በአሜሪካ፣ ቴክሳስ ግዛት አርብ ዕለት ባጋጠመ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 24 ሰዎች ሲሞቱ በካምፕ ውስጥ የነበሩ ወደ 25 የሚጠጉ ሴት ታዳጊዎች መጥፋታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በነጻነት ቀን ያጋጠመውን ይህንን የጎርፍ... Read more »

ሩሲያ ኪዬቭን በድሮን ደበደበች

የዩክሬን ባለስልጣናት ሩሲያ ሌሊቱን በሰው አልባ አውሮፕላን ኪዬቭን ስትደበድብ ማደሯን ገለፁ። ሩሲያ ሌሊቱን በኪዬቭ በፈፀመችው ከፍተኛ የድሮን ድብደባ የተነሳ ከፍተኛ ፍንዳታዎች መሰማታቸውን እና አካባቢው በጭስ መሸፈኑን ተናግረዋል። ዩክሬን፣ ሩሲያ 550 ሰው አልባ... Read more »

የጦርነቱ መሠረታዊ ምክንያት ካልተወገደ ሰላም እንደማይሰፍን ፑቲን ተናገሩ

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከዩክሬን ጋር ወደ ጦርነት ያስገባት መሠረታዊ ችግር ካልተወገደ ጦርነቱን እንደማታቆም ተናግረዋል፡፡ ፑቲን ከአሜሪካው አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት፣ ሞስኮ ከኪዬቭ ጋር ወደ ጦርነት ያስገቧት መሠረታዊ... Read more »

በአሜሪካ የወንጀል ጥናት ተማሪው አብረውት የሚኖሩ ተማሪዎችን መግደሉን አመነ

የ30 ዓመቱ ግለሰብ እንደ አውሮፓውያኑ በ2022 በአሜሪካዋ ኢዳሆ ኮሌጅ ከተማ አራት አብረውት የሚኖሩ ተማሪዎችን መግደሉን አመነ። ግለሰቡ ጥፋቱን ያመነው የሞት ቅጣትን ለማስቀረት ከአቃቤ ሕግ ጋር የገባውን ስምምነት ተከትሎ ነው። ብርያን ኮህበርገር የተባለው... Read more »

አሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር ልማት ለዓመታት ወደ ኋላ እንደመለሰችው ገለፀች

  አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ የፈፀመችው ጥቃት የሀገሪቱን የኒውክሌር መሣሪያ ልማት ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ወደ ኋላ እንደመለሰው ገልፃለች፡፡ የአሜሪካ የመከላከያ መሥሪያ ቤት (Penta­gon) አሜሪካ የፈፀመቻቸው ከባድ ጥቃቶች የኢራንን የኒውክሌር ጣቢያዎች... Read more »

አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገውን የተወሰነ የጦር መሣሪያ ድጋፍ ማቋረጧን አስታወቀች

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትፈጽመው ጥቃት እየተባባሰ በመጣበት በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ለኪዬቭ የምትሰጠውን የተወሰነ የጦር መሣሪያ ማቆሟን ዋይት ሐውስ አስታወቀ። የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ አና ኬሊ ማክሰኞ ዕለት እንዳስታወቁት ውሳኔው ላይ የተደረሰው የመከላከያ... Read more »

እሥራኤል ለ60 ቀናት በጋዛ ተኩስ ለማቆም መስማማቷን ትራምፕ አስታወቁ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እሥራኤል በጋዛ የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነትን ለማድረግ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን ለማሟላት እንደተስማማች ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ በ‹ትሩዝ ሶሻል› (Truth Social) አድራሻቸው፣ ‹‹ጦርነቱን ለማቆም ከሁሉም አካላት ጋር በትብብር እንሠራለን። ሰላም... Read more »