በጃንጥላው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስር ካሉት ተቋማትና ከአብዝተውም ተጠቃሾቹ አንዱ ነው- ዩኔስኮ። በመሆኑም ውሳኔዎቹ ገዢ ናቸው፤ ምክረ ሀሳቡም እንደዛው። በመሆኑም፣ በቅርቡ ባስተላለፈው ያልተጠበቀ ውሳኔ ብዙዎች ተደናግጠዋል፤ በርካቶች እንደ ገበቴ ውሃ በመዋለል ላይ... Read more »
በከተማችን አንዳንድ ስፍራዎች በመኪና ጉዞ ሲጀምሩ ሁሌም በምቾት ላይሆን ይችላል። አንዳንዴ የመንገዱ ደህንነት ከሥጋት ይጥላል። በተለይ የተሳፈሩበት መኪና ታክሲ ከሆነ መሳቀቁ አያድርስ ነው። ደርሶ በአየር ላይ ይበር የሚመስለው መኪና ያሉበትን ያስረሳዎታል፡፡ በፍጥነቱ... Read more »
ለመስክ ሥራ ከአዲስ አበባ ውጭ ቆይቼ ስመለስ የሚያጋጠመኝ ችግር ነው። የመስክ ጉዞ ጣጣ ስለሚበዛበት አዲስ አበባ ስንገባ ይመሻል። የአዲስ አበባ መንገድ ደግሞ የተዘጋጋ ስለሆነ ቤት ለመድረስ የበለጠ ይመሻል። ከቤቴ አካባቢ ስደርስ ሱቅ... Read more »
የሰለጠነ ተቋምን የሚፈጥረው የሰለጠነ ዜጋ ነው። እንዳለመታደል ሆኖ የሰለጠነ ዜጋም የሰለጠነ ተቋምም የለንም። የሰለጠነ ተቋም ባለመኖሩ ምክንያት ብዙ ብልሹ ነገሮች ይታያሉ። አገልግሎቱን የሚሰጡ አገልጋዮችም ሆኑ ተገልጋዮች ላይ ያልሰለጠኑ ምልክቶች ይታያሉ። ነገሩን ያስታወሰኝ... Read more »
ተማሪና ትምህርት እንደማይነጣጠሉ ሁሉ፤ ተማሪና እረፍትም የሚለያዩ አይደሉም። የዚህ ምክንያቱ ደግሞ “ተፈጥሯዊ” ሲሆን፣ ሰርቶ ማረፍ እንዳለ ሁሉ አርፎ መሥራትም ያለ በመሆኑ ነው። አሁን ያለንበት ወቅት ክረምት ሲሆን ወሩም ሐምሌ ነው። የሚቀጥለው ደግሞ... Read more »
ከጥቂት የዕረፍት ቆይታ በኋላ ወደሥራ ገበታዬ ተመልሻለሁ። ብዙ ጊዜ ይህ መሰሉ እረፍት ንቁ መንፈስ ያላብሳል፣ ለአዲስ ሥራ ያዘጋጃል። በእኔ ውስጠት የነበረው እውነታም ይኸው ነበር። ለሚዘጋጀው ሳምንታዊ የጋዜጣ ዓምድ ‹‹ይበጃል›› ባልኩት ዕቅድ ከራሴ... Read more »
የማህበራዊ ትስስር ገጾች ከዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን (ሜይንስትሪም ሚዲያዎች) ጋር ቦታ እየተቀያየሩ ነው። ማህበራዊ ገጾች ሊሰሩት የሚገባውን እንቶ ፈንቶና ዋዛ ፈዛዛ የሆኑ ነገሮችን ዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን ላይ፤ በተቃራኒው ደግሞ ጠንካራ የሆኑ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና... Read more »
በአንድ ወቅት የተከራየሁበት ግቢ ውስጥ ባልና ሚስት ተጣሉ:: ሲነጋገሩ የነበረው በጣም ተራ በሚባሉ ሀሳቦችና ቃላት ነበር:: እንኳን ሕይወትን ያህል ነገር የተጋራ ባለትዳር ይቅርና መንገድ ላይ በመተላለፍ የተጋጨ እንኳን በእንደዚያ ዓይነት ተራ ነገሮች... Read more »
ፒያሳ በድምፅ ማጉያ በታጀበ የህክምና እርዳታ ተማፅኖ፣‹‹የሙዚቀኛና ዘማሪ እገሌና እገሊት አዲስ ስራ ተለቀቀ›› በሚል ጆሮ የሚበጥስ ማስታወቂያ፣ በመንገድ ላይ ነጋዴዎች ‹‹የግዙን››ጥሪ ድምፅ ታውካለች፡፡ የሚያስተናንቅ የሃሳብ ልዩነት ከሌለን አንድ ጓደኛዬ ጋር አንድ ካፌ... Read more »
ከአንድ ወር በፊት አካባቢ ይመስለኛል። ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ ቆሜ የሰርቪስ ትራንስፖርት እየጠበቅኩ ነው። ከአውቶቡስ መጠበቂያ ማረፊያው ላይ ቢጫ ፌስታል የያዙ አንድ ሦስት ሴቶች ተቀምጠዋል። ከኋላዬ አንድ በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኝ ሰው መጣ።... Read more »