በአጭር ጊዜ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በአፍሪካ ዋንጫው ማካተት አልተቻለም

የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከትናንት በስቲያ አመሻሽ ላይ ወደ አፍሪካ ዋንጫው የሚያመሩ ሃያ አምስት ተጫዋቾቻቸውን ዝርዝር ይፋ አድርገዋል፤ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከግብ ጠባቂ አንስቶ እስከ አጥቂ መስመር የተመረጡት ተጫዋቾች በአፍሪካ... Read more »

የተሳታፊዎች ቁጥር ማነስ ያላደበዘዘው ቻምፒዮና ጅማሬ

በአትሌቲክስ ስፖርት ስኬታማ ሆነው ትልቅ ስምና ዝና ካገኙ አገራት መካከል የምትመደበው ኢትዮጵያ፤ በተለይ በረጅም ርቀት ሩጫዎች ስኬቷ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች፡፡ ስፖርቱ ከሩጫ ባለፈ እርምጃ፣ ውርወራን እንዲሁም ዝላይን የሚያጠቃልል ቢሆንም ኢትዮጵያ የአጭር ርቀት ሩጫን... Read more »

ከ700 በላይ አትሌቶች የሚሳተፉበት አገር አቀፍ ቻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአጭር፣ መካከለኛ፣ 3ሺ ሜትር መሰናክል፣ የርምጃና የሜዳ ተግባራት ውድድሩን ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የማዘውተሪያ ስፍራ ላይ ያካሂዳል። ውድድሩ ዛሬ ሲጀመርም በተለያዩ ርቀቶችና የሜዳ ተግባራት... Read more »

«ለኮስታሪካው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ጥረት እያደረግን ነው»

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በስኬት ላይ ስኬት እየደረበ ጉዞውን ቀጥሏል። የመካከለኛውና ምሥራቅ አፍሪካ አገራት(ሴካፋ) ዋንጫን ከስድስት ሳምንታት በፊት ዩጋንዳ ላይ በማንሳት በኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ታሪክ የመጀመሪያ ድል ያሳካው... Read more »

የአፍሪካ ዋንጫ ሊሰረዝ የሚችልበት እድል እየሰፋ ሄዷል

በጉጉት የሚጠበቀውና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ከስምንት ዓመት በኋላ የሚሳተፉበት የ2022 የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ሊራዘም ወይም ሊሰረዝ የሚችልበት እድል ስለመኖሩ የተለያዩ ዘገባዎች ሲወጡ ከርመዋል። ካሜሩን የምታዘጋጀው ይህ 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ምእራብ አፍሪካዊቷ... Read more »

ማራቶንን ለማጠናቀቅ 54 ዓመታት የፈጀበት አትሌት

የስፖርቱ ዓለም ሁሌም በተአምራት የተሞላ ነው። አይሆንም የተባለ የሚሆንበት፣ ይሆናል የተባለው የማይሆንበት ዓለም ስፖርት ነው። ለማመን የሚከብዱ ክብረወሰኖች፣ ታሪክ የማይዘነጋቸው ጀግኖችና ከህሊና የማይጠፉ ድልና ሽንፈቶች የስፖርቱን ዓለም የሚያጣፍጡ ቅመሞች ናቸው። ከዚህ ባሻገር... Read more »

የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠናን ወደ ውጤት ለማምጣት እየተሠራ ነው

የኢትዮጵያን ስፖርት ለማሳደግና በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ውጤታማ ለማድረግ በተለያዩ ክልሎች የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ከዓመታት በፊት ተጀምሮ ሲሰራበት ቆይቷል። ይሁን እንጂ ይህ ፕሮጀክት መክሸፉ ወይም የታቀደለትን አላማና ግብ አለመምታቱ ተረጋግጧል። ይህንንም ተከትሎ... Read more »

ፈረሰኞቹ አሰራራቸውን ለማዘመን እያስጠኑ ነው

የአንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበርን የአስተዳደር፣ የማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ዘርፍን ለማዘመንና ለማሻሻል የሚያስችል ጥናት ለማስጠናት ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን ከቀናት በፊት የክለቡ ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀልና የድንቅ ኢትዮጵያ ብራንድ ኮንሰልታንት ኩባንያ ስራ አስኪያጅ አቶ... Read more »

ዛሬ በሚጀመረው የዓለም ውሃ ዋና ቻምፒዮና አራት ኢትዮጵያውያን ይሳተፋሉ

አስራ አምስተኛው የዓለም ውሃ ዋና ቻምፒዮና ዛሬ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አስተናጋጅነት ይጀመራል። ለስድስት ቀናት በሚካሄደው የዓለም ውሃ ዋና ቻምፒዮና ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ኢትዮጵያውያን የውሃ ዋና ስፖርተኞች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ታውቋል። በዓለም አቀፉ... Read more »

የቦክስ ስፖርት ከኦሊምፒክ ሊሰረዝ ይችላል

ተወዳጁ የቦክስ ስፖርት ከኦሊምፒክ ሊሰረዝ እንደሚችል የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህ አስጠነቀቁ። ከቦክስ ስፖርት በተጨማሪ የክብደት ማንሳትና ዘመናዊ ፔንታትለን ውድድሮች ከኦሊምፒክ የመሰረዝ አደጋ የተደቀነባቸው ስፖርቶች እንደሆኑ ቶማስ ባህ ሰሞኑን ለመገናኛ... Read more »