የሀሳብ ገጾች

ዘንቦ አባርቷል..። ስስ ለጋ ፀሐይ በምሥራቅ አድማስ ላይ አቅላልታለች። እንዲህ ሲሆን ደስ ይለዋል..እንዲህ ሲሆን መኖር ያረካዋል። በዘነበ ሰማይ ላይ ያቅላላች እንቡጥ ፀሐይ ሲመለከት..በተሲያት አለም ላይ ሊዘንብ ያለ ጉሩምሩምታ ሲያደምጥ ተፈጥሮና ፈጣሪ በአንድ... Read more »

ሞትን መግደል..

እንደ ትናንቱ ናት.. እንደዛ ቀደሙ። አንገቷ ተሰብሮ፣ አይኖቿ አዘቅዝቀው ከመሬት ተወዳጅተዋል። ቀና የሚያረጋት ክንድ ትሻለች። ግን የነኳት ክንዶች ሁሉ ለዝቅታዋ ምክንያት ሆነው ያለፉ ናቸው። ሰው ለሌሎች የሚተርፈው ለራሱ ሲበቃ ነው ትላለች ግን... Read more »

መታዘዝ ከሰነፍ መስዋዕት ይበልጣል

ሰፈራችን ውስጥ ለቤታችን የቀረበ አንድ አጥቢያ አለ። ጠዋት አይሉ ማታ ቄሱ በማይክራፎኑ ውስጥ ለዛ ሁሉ ለተሰበሰበ መዕምን ‹መታዘዝ ከሰነፍ መስዋዕት ይበልጣል› ሲሉ እሰማለው። በቅስናቸው ውስጥ የያዙት አንድ ቃል እሱ ይመስል ተኝቼ በነቃሁ... Read more »

እሺ ይበልጣል ከሺ..

 እማ! አልኳት ወዳለችበት ራመድ ብዬ። እማ ነው የምላት..ተሳስቼ በስሟ ጠርቻት አላውቅም። እንዲህ እንደ አሁኑ እንድታስቸግረኝ ፊቷ ቆሜ አውቃለሁ። ‹ወዬ ጌታዬ! አለችኝ..ፊቷን በትንሽ ፈገግታ ሞልታ። በእሷ አፍ ጌታዬ ስባል ነፍሴ በደስታ በልቤ ውስጥ... Read more »

የፍቅር ነፍሰ ገዳዮች

ማታ ሊሆን ትንሽ ሲቀረው..አስራ ሁለት ግድም ላይ ከቤት ወጣሁ ሳሮንን ላገኝ:: ሳሮን ከብዙ የእንገናኝ ውትወታ በኋላ ቃሏን የሰጠችኝ የመጀመሪያዋ ሴት ነች:: ደሞ እኮ አታምርም..ቆንጆ ሆና ብታለፋኝ አይቆጨኝም ነበር:: አስቀያሚ ናት..የሌለ:: በአስቀያሚ ሴት... Read more »

አመልና ፍቅር

ልማድ አለብኝ ክፉ ልማድ..ጥፍሬን እበላለው፣ ጸጉሬን እቆነድዳለው። እኚህ ልማዶቼ በሰው ፊት አላሳነሱኝም። አንዳንድ ጊዜ እናቴ ‹እጅህን ከራስህ ላይ አውርድ ብላ በማማሳያ ከመማታቷና ጥፍርህን ለምንድነው የምትበላው? ከማለት ባለፈ ያን ያክል ሰው አፍ ላይ... Read more »

 ከሕይወት እልፍኝ ውስጥ

ሕይወት በእሾህ የታጠረች እንደሆነች የገባኝ አስራ ስምንት ዓመቴን ካከበርኩ በኋላ ነበር። ከዛ በፊት የነበረው ሕይወቴ እንደ ማር የጣመ ነበር። በድሎት የተኖረ። በሕይወት እሾህ እየተወጉ እኔን የሚያሞላቅቁ ወላጆች ነበሩኝ። ከእማዬ ካመለጥኩ አባዬ ጉያ... Read more »

ጥቁር አምልኮ

አያቴ ጥቁር ቀለም አትወድም..ጠይም መሆኔ በጀኝ እንጂ እኔንም ልጄ አይደለም ብላ ልትክደኝ ትሞክር ነበር። ከቤታችን ውስጥ ለጥቁር የቀረብኩት ጠይሙ እኔ ነኝ..አብሬያት ስሆን ሌላ ወሬ የላትም ‹እንዳው በማን ወጥተህ ነው እንዲህ የጀበና ቂጥ... Read more »

መኖር ባይኖር

አስባለው..ባለማሰብ ውስጥ። ላለማሰብ አስባለው..ለማሰብ አስባለው። ላለማሰብ ማሰብ ለማሰብ ከማሰብ በላይ አስጨናቂ እንደሆነ በእለት ተእለት ኑሮዬ ተለማምጄዋለው። አልጫ በጨው ይጣፍጣል፣ ቡና በስኳር ይጥማል የህይወት ማጣፈጫ ምንድነው? ህይወት ምን ጠብ ቢደረግባት ነው ስኳርና ጨው... Read more »

ዓለም በቃኝ

 ከአምስት ዓመት በኋላ ከሮዛ ጋር ተጋባን።ያን ወፍ ዘራሽ ወንድነቴን ባሏ አደረገችው።ያን በተለያዩ ሴቶች ያደፈ ገላዬን አቅፋው ልትተኛ ነው..ያን በብዙ ሴት የተሳመ ከንፈሬን ልትስመው ነው። ወፍ ዘራሽ ነበርኩኝ እኮ..አብረን የሚያዩን አንዳንድ ሰዎች ወደ... Read more »