እየተባባሰ የመጣው የአየር ንብረት ለውጥ

ከአላርም (አጣዳፊ የድረሱልኝ ጥሪ) በስተቀር በዚህ ጽሑፍ ምንም አዲስ ነገር ይዘን አልመጣንም። ጉዳዩ የዝሆን ጆሮ ይሰጠኝ ሆነና ነው እንጂ፣ በችግሩ ዙሪያ ያልተባለ ነገር የለም። በዓለማችን የችግሩ መኖር ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ በአየር ጸባይ... Read more »

ሀገራዊ ፈተና ሆኖ የቀጠለው ሕገ ወጥ ስደት ፤

 ፍልሰት እንበለው ስደት ሰፊና ውስብስብ የሰው ልጆች ታሪክ ነው። በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ዓመታትን ያስቆጠረ ሰብዓዊ ክስተትም ነው። ሰዎች ከቅድመ ታሪክ አንስቶ በተለያዩ ገፊ ምክንያቶች ማለትም በአየር ንብረት ለውጥ፣ በሕዝብ ብዛት፣ በኢኮኖሚያዊ ዕድሎች፣... Read more »

 በመኸሩ ወቅት የግብርናችን ፈተናዎች

ከሰማኒያ በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኑሮው በግብርና ላይ የተመሰረተ መሆኑ ይነገራል። አርሶ አደሩ በልቶ የመኖር ሕልውናውን ከማረጋገጥ አልፎ በከተሞች አካባቢ በንግድ፣ በወር ደመወዝተኝነትና በሌሎች ሥራዎች የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የመመገብ ኃላፊነትም ትከሻው... Read more »

 “ሕጉን በሕግ አምላክ!”

 የመነሻችን ትዝብት፤ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የሀገራችንን የፍትሕ ሥርዓት አስመልክቶ ሰፋ ያለና በርካታ ታዳሚያን የተጋበዙበት አንድ ውይይት ተደርጎ ነበር፡፡ በዕለቱም ይህ ጸሐፊ በስብሰባው ላይ ለመገኘት ዕድል አጋጥሞት ነበር፡፡ በመርሃ ግብሩ መሠረት በተጠቀሰው ርዕሰ... Read more »

 ራሳችንን ከፅንፈኛ መገናኛ ብዙኃን እንጠበቅ!

 መገናኛ ብዙኃን በዋነኝነት አመሠራረታቸው ለህብረተሰቡ መረጃ ከማድረስ ባሻገር ለማስተማርና በአንድ ሀገር ውስጥ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር የበኩላቸውን ለመወጣት ጭምር ነው፡፡ ይህንንም ማድረግ የሚያስችል ኤዲቶሪያል ፖሊሲ አላቸው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ መገናኛ ብዙኃን የሀገሮቻቸውን... Read more »

 ሥልጣኔ ራስን መተው፣ ራስን መርሳት… ማንነትን መቀየር አይደለም !

ወርሀ ነሀሴ የመስከረም መባቻ..የአዲስ ዓመት መዳረሻ ከመሆኑም በተጨማሪ በኢትዮጵያ አሁናዊና ትናንታዊ ታሪክ ውስጥ የራሱ የሆነ ሰፊ የታሪክ ዐሻራ ያለው ወር ነው።ዳግማዊ አጼ ምኒልክን ጨምሮ ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱም ወደዚች ዓለም የመጡት በዚህ ወር... Read more »

ሰላምን በማጽናት ፤ የተረጋጋ ኢኮኖሚን ማዋለድ !!

ከሰሞኑ ወደ በረሃዋ ንግስት ድሬዳዋ ከተማ አቅንቼ ነበር። ድሬ ከስድስት ዓመት በፊት ከማውቃት በላይ በእጅጉ ተነቃቅታለች። በ1890ዎች መጨረሻ አካባቢ የተመሰረተችው ድሬዳዋ ከተማ በ1902 ደግሞ የራሷ ማዘጋጃ ቤት እንደነበራት ታሪካዊ መዛግብት ያስረዳሉ። ይህች... Read more »

 መፍትሔ የሚያሻው የኤሌክትሪክ ኃይል በተደጋጋሚ መጥፋትና መቆራረጥ ፤

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ባስጠናው አንድ ጥናት በተደጋጋሚ በሚከሰት የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ሀገራችን በአንድ ዓመት ብቻ 95.5 ቢሊየን ብር ታጣለች ። በዓመት በአማካኝ ለ162 ሰዓታት መብራት ይጠፋል። ይቅርታ አድርጉልኝና እኔ... Read more »

 አዕምሯችን የጥላቻ ንግግርና የሐሠት መረጃ ሸቀጥ ማራገፊያ እንዲሆን አንፍቀድ

አሁን አሁን መቀያየሙ፣ መገፋፋቱና መራራቁ እየበረታ የመጣ ይመስላል። አለመተማመኑም የዚያኑ ያህል ላቅ ብሎ ይስተዋላል። ጠዋት አካባቢ አግኝታችሁት ሰላምታ የተለዋወጣችሁት ጎረቤታችሁ አሊያም የስራ ባልደረባችሁ ረፋድ ላይ ከለበሰው አልባስ ውጪ ባህሪው ሲቀያየር ታስተውላላችሁ። አንዳንዴም... Read more »

 የሕዝብንና የሀገርን አደራ በኃላፊነት መንፈስ እንወጣ!

ዊልያም አርተር ዎርድ የተባለ ምሁር እንደሚገልጸው፤ የተማሩ ሰዎች ግልጽ በሆነ እና አመክንዮን መሠረት ባደረገ መልኩ ያስባሉ፤ ክብሩን የጠበቀ ኑሮን ይኖራሉ፤ድፍረትን ያንፀባርቃሉ፤ በሙሉ ፈቃደኝነት እና በለጋስነት ይሰጣሉ፤ ፍቅር እና ፀጋ በተሞላበት መንገድ ምህረትን... Read more »