መሪዎቹ ለቀጠናው ሰላም እና ትብብር በጋራ እንደሚቆሙ አስታወቁ

. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በኤርትራ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ አዲስ አበባ ፡- የኢትዮጵያ ፣የኤርትራና የደቡብ ሱዳን መሪዎች የቀጠናውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ ፡፡ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ... Read more »

ከሦስት ዓመት በኋላ የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ መላክ ይጀመራል

አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ ከሦስት ዓመት በኋላ እ.አ.አ በ2021 የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ መላክ እንደምትጀምር በማዕድንና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የነዳጅ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አስታወቁ። የተፈጥሮ ጋዙ በዓመት እስከ አንድ ቢለዮን የአሜሪካ ዶላር ያስገኛል... Read more »

የክትባት መርሐ ግብሩ በአማራ ክልል ተቃውሞ አልገጠመውም

አዲስ አበባ፡- በአማራ ክልል የተካሄደው አንደኛው ዙር የማህፀን በር ካንሰር ክትባት ከሦስት ወረዳዎች በስተቀር በስኬት መጠናቀቁን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወይዘሮ ፀጋነሽ ገድሉ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤... Read more »

ተፈናቃዮችን በዘላቂነት የማቋቋሙ ሥራ በቂ አይደለም

አዲስ አበባ፡- የኢፌዴሪ እንባ ጠባቂ ተቋም በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ ያለው ሥራ በቂ አለመሆኑን አስታወቀ፡፡ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለመታደግ የሚደረገውም ኢኮኖሚያዊና ሥነ ልቦናዊ ድጋፍ... Read more »

የእስራኤል ምርጫና የኔታኒያሁ ፈተና

የእስራኤል አገራዊ ምርጫ ሊካሄድ የአምስት ሳምንታት እድሜ ብቻ ቀርተውታል። በአሁኑ ወቅትም የምርጫው ተፋላሚዎች በይፋ ታውቀዋል። ቀጣዩ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ቤኒያሚን ኔታኒያሁ አሊያም ቤን ጋንቴዝ መሆናቸው እርግጥ ሆኗል። ከሁሉም በላይ የዘንድሮው ምርጫ ፍልሚያው... Read more »

የኬንያ ዜጎች የግል መረጃ በህግ የተጠበቀ አይደለም

እአአ 2017 በኬንያ በተካሄደው የፕሬዚዳንት ምርጫ ተጭበርብሯል በመባሉ የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገውን ውጤት ባስገራሚ ሁኔታ መሻሩ ይታወሳል፡፡ በኬንያ በተካሄደው ምርጫ ውጤቱ ይፋ ከመሆኑ አስቀድሞ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ እያሰራጩ... Read more »

የዓድዋ ድል በዓልን ምሁራን በሚገባው ልክ እንደማያከብሩት ተገለጸ

አዲስ አበባ፡- የዓድዋ ድል በዓልን ምሁራን ከመደበኛ ማህበረሰቡ በተለየ መልኩ እንደማያከብሩት የአፍሪካን ጥናትና ምርምር ባለሙያዎች ማህበር አስታወቀ፡፡ ማህበሩ የተለያዩ የፓናል ውይይቶችን በማድረግና ጥናቶችን በማቅረብ በዓሉን በትናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መሰብሰቢያ አዳተሰብ... Read more »

አገልግሎቱ የእቅዱን 81 በመቶ መፈጸሙን ገለጸ

አዲስ አበባ:- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወር እቅዱን 81 በመቶ ማከናወኑን አስታወቀ። የመስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ መላኩ ታዬ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ መስሪያ ቤቱ የአገልግሎት አድማሱን... Read more »

የልዩ ፍላጎት ፖሊሲ ልዩ ተሰጥኦን አላካተተም

አዲስ አበባ፡- ልዩ ፍላጎትን አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር ደረጃ ፖሊሲ ተቀርጾለት እየተሰራ ቢሆንም በአካል ጉዳት ላይ የተመሰረተውን ብቻ እንጂ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ያካተተ እንዳልሆነ ተገለጸ፡፡ በመንግስት ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመው የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ... Read more »

ከተሞች ያልተሻገሯቸው ተግዳሮቶች

በአገሪቱ የሚገኙ ከተሞች በየጊዜው እየጨመረ የሚገኘውን ህዝብ ለማስተናገድ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመኖርያ ቤቶች ግንባታና በልዩ ልዩ የስራ እድል ፈጠራ ላይ የሚታዩ ለውጦች ማሳያ ናቸው፡፡ ነገር... Read more »