አዲስ አበባ፡- የዓድዋ ድል በዓልን ምሁራን ከመደበኛ ማህበረሰቡ በተለየ መልኩ እንደማያከብሩት የአፍሪካን ጥናትና ምርምር ባለሙያዎች ማህበር አስታወቀ፡፡ ማህበሩ የተለያዩ የፓናል ውይይቶችን በማድረግና ጥናቶችን በማቅረብ በዓሉን በትናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መሰብሰቢያ አዳተሰብ ክፍል በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት ከማክበር ባለፈ የተለያዩ ጥናቶችንና ለአገር የሚበጁ ተግባራትን እየፈጸሙ በዓሉን ሲያከብሩ አይታይም።
በፓናል ውይይቱም ሆነ በቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፎች እንደተነሳው የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካ ድል የሆነውን ዓድዋ ድል በዓል በሁሉም ልቦና ውስጥ ያለ ነው።
ሆኖም ምሁራኑ ከድሉ በመማር በተለያዩ ጥናቶች በማስደገፍ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች መጠራሽ በአካሄደበት ወቅት የማኅበሩ ሊቀመንበር አቶ ወርቁ በላቸው በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ምሁራኑ እንደ ማንኛውም የህብረቀም ሲቻል ይህንን ቸል እንዳሉት ተናግረዋል፡፡ “እኛ ኋላቀር ነን ብለን ስለምንጀምር በአገራችን ያለውን አገር በቀል እውቀት በጭቃ እንለውሰዋለን። እንደዛ ማለቱ ደግሞ ያለን ሀብት ያሳጣል።
ስለሆነም ዛሬ ለሚያስፈልገን ነገር ምሁራኑ መስራት ይጠበቅባቸዋል» ያሉት ሊቀመንበሩ፤ ከራስ ስሜት በመነጨ አስተሳሰብ መጓዝ ላልተፈለገ ንትርክ ይዳርጋልና ይህንን በመፍታት በኩል ምሁራን የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል። በዓሉን እንደ አፍሪካዊነት ሳይሆን እንደ ግል እየተከበረ እንዲመጣ የሆነበትን ችግር በመፍታቱም ሊሳተፉ እንደሚገባ ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጥናትና ምርምር የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ አቶ ፍስሃ ሞረዳ እንደተናገሩት፤ አፍሪካዊ እውቀት አለ፤ ከአፍሪካዊ እውቀታችን ግን እየተጠቀምንበት አይደለም፡፡
በመሆኑም ከአድዋ መማር ያለብን አፍሪካዊ ክብርን እንደተላበስን አፍሪካዊ ዕቀትንም በዚው ልክ ተላብሰን ማደግ ነው፡ ፡ ከዚህ አልፈን ሁሉንም ከውጭ የምናመጣ ከሆነከቅኝ ግዛት ተላቀቅን የምንልበት ምንም ማንነት አይኖረንም፡፡
በመሆኑም ይህንን በመፍታት በኩል የምሁራኑ ድርሻ የላቀ ነውና ሊሰሩበት ይገባል። አባቶቻችን ቅኝ እንዳንገዛ የተቻላቸውን ያደረጉት ለዛሬ ነጻነት የሰጡን በብዙ ትግል ውስጥ አልፈው ነውና የአድዋ ልጆችም ይህንኑ ያለመገዛት ወኔ ይዘን መቀጠል አለብን የሚሉት አቶ ፍስሃ፤ በተለይ ምሁራን ዛሬ ላይ ሰከን ብለው የአገርን አድነት የሚገነባ ሀሳብ ላይ መስራት አለባቸው፡ ፡
የሃሳብ ልዕልናን ከማስፋት አንጻር ከስሜት በዘለለ እና ብሔር ተኮር ያልሆነ ተግባር መከወን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጥናትና ምርምር የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ አቶ ብሩክ ሸዋደግ በበኩላቸው በዓድዋ ድል ምክንያት በአካል አልተገዛንም፤ በቅኝ ግዛት ካልተያዘው ግን የሚለየን ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም በትምህርት ስርዓታችን፣ በቋንቋ፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች ተገዝተናል፡፡
ለዚህ ደግሞ ያለንን አገር በቀል እውቀት ያለመጠቀማችን ነው ይላሉ። በተለይ የተማረው ሐይል ጉራማይሌ ቋንቋ ከመናገር ጀምሮ እስከ አስተሳሰብ ልዕልና ልክ የሆነው የውጪው ነው ብሎ ያመናል፡፡ ይህ ደግሞ ተተኪውም ከቅኝ ግዛት እንዳይወጣ አድርጎታል ብለዋል፡፡ እንደ አቶ ብሩክ ገለጻ፤ የአድዋን ድል ማስቀጠል የሚቻለው አገር በቀል እውቀቶች ላይ ምሁራን መስራት ሲችሉ ነው፡፡ ከማንኛው ግለሰብ በተለየ መልኩ ምሁራዊ ትንታኔ እየሰጡ ያለመገዛታችንን አንድምታ ሊያጎሉ ይገባል፡፡
በተጨማሪም ከቤት ያለፈ፣ ከስሜት የራቀ እና ግላዊነት ያልተጸባረቀበት ኢትዮጵያነትን የተቀዳጀ እውቀትን ለትውልድ ማውረስ ላይ መስራት አለባቸው፡፡ በፓናል ውይይቱ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ጥናታዊ ጹፎች የቀረቡ ሲሆን በጽሁፎቹ ከተወሱ ጉዳዮች መካከል ከአድዋ ድል በመማር ሰላምን አንድነትን በማስፈን፣ አገርን በማስቀደም ኢትዮጵያን ወደቀድሞ ክብሯ መመለስ አለብን የሚል ሃሳብ የሚገኝበት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ አፍሪካዊ ሰላም አለን እሱንም መጠቀም አለብን የሚለው ይገኝበታል፡፡
አዲስ ዘመን የካቲት 24/2011
በአብርሃም ተወልደ