በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ የሚገኘው የሸቀጦች ዋጋ መናርና የኑሮ ውድነት ለብዙዎች ፈተና እየሆነ መምጣቱ እየተነገረም እየታየም ያለ ሃቅ ነው። የእያንዳንዱ ሸቀጥ ዋጋም አይን ጨፍኖ ሲነቃ ያህል ሽቅብ እየወጣ ነው። የኑሮ ውድነቱን... Read more »
ዛፍ በለጋነቱ ካልተቃና፤ ሰው በልጅነቱ የሰውነት እሴትን እንዲላበስ ካልተደረገ፤ ሁለቱም ካደጉና ከጠነከሩ በኋላ ለማቃናት የሚደረገው ጥረት ከንቱ ድካም ነው:: ምክንያቱም ዛፉም ይሰበራል፤ ሰው ሲሆን ደግሞ ከመቃናት ይልቅ እኩይ ባህሪው የበለጠ እየጎላ ይሄዳል::... Read more »
እግር ኳስ ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ስለስፖርቱ ፍቅር የማይታገሰውና የማያልፈው ፈተና የለም። ዶፍ ቢወርድበት የጸሃይ ሃሩር ቢያነደው፣ ጨዋታው ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ድንበር ቢሻገርም፣ የሽንፈት አዘቅት ቢውጠውም ተስፋ አይቆርጥም። ይልቁንም ከሰዓት በኋላ ለሚደረግ ጨዋታ... Read more »
አለቃ ገብረ ሃና ቀልድ አዋቂ ስለመሆናቸው አገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ስለመሆኑ ለእናንተ አላወጋም። አለቃ በጣም አጭር ሰው ናቸው ይባላል። ሚስታቸው ወይዘሮ ማዘንጊያሽ ደግሞ ሲበዛ ረጅም ናቸው። መንገድ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ ወይዘሮ ማዘንጊያሽ... Read more »
ፖለቲካ ማለት በቡድን ያሉ ግለሰቦች የጋራ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችላቸው ሂደት ነው። በዚህ ምክንያት ምንም እንኳ ፖለቲካ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ከአገርና ከመንግሥት ጋር የተገናኘ ቢሆንም በሌላ አንጻር የሰው ልጆች በቡድን ሆነው... Read more »
አሜሪካ ካሏት አንሰላሳዮች ቀዳሚ የሆነው፤ የዝነኞቹ ሀርቫርድና የል ዩኒቨርሲቲዎች ምሩቅ፤ ትውልደ ሕንድ አሜሪካዊ፤ የአለማቀፍ ጉዳዮች ሊቅ፣ ጉምቱ ጋዜጠኛ፣ ደራሲና አንደበተ ርዕቱ ተናጋሪ ፋሪድ ዘካሪያ፤ የተወዳጁ የሲኤንኤን ቴሌቪዥን Global Public Square/GPS/ አዘጋጅ፤ የዋሽንግተን... Read more »
አንዳንድ ሰዎች ሰሞኑን መነጋገሪያ ያደረጉት ነገር ቢኖር የሕወሓት አካሄድ አስገራሚ፣ እብደት የተሞላው፣ አለማወቅ የበዛበት…. ነው እያሉ ሃሳብ ሲለወዋወጡ ለመመልከት ሞክሬ ነበር። ይህ ሐሳብ ለምን መነጋገሪያ ሆነ ሲባል የትግራይን ወጣት ለስልጣኑ ሲል አገርና... Read more »
“ዳዴ”፡- ጨቅላ ሕጻናት ቆመው ለመሄድ የሚውተረተሩበት ተፈጥሯዊ የዕድሜያቸው ባህርይ ነው። “ወፌ ቆመች!” እየተባሉ ሲውተረተሩ ማየት እንኳን ለወላጆች ቀርቶ ለተመልካችም ቢሆን ደስታው እጥፍ ድርብ ነው። ሕጻናቱ አጥንታቸው ጠንክሮ ያለ ድጋፍ መቆም እስከሚችሉበት ጊዜ... Read more »
ግጥም የስነ ውበት ምስጢር በመሆኑ ስሜታዊ ግንዛቤን የሚመረምር የፍልስፍና ዘርፍ ነው ይላሉ ሊቃውንቶቹ። ለኔ ግን የንስሀ ፀሎት ይመስለኛል። ምክንያቱም ጥበብ እንደ ተገለፀ ቅርፅና ፅንሰ-ሀሳብ መኖሩ ውስብስብ ታሪክ ቢኖረውም ከጥንት ጀምሮ እስከ ሰው... Read more »
ኢትዮጵያ ባህር ተሻግረውና ድንበር ጥሰው ሊያስገብሯት ሊወሯትና ቅኝ ሊገዟት አልመው ለመጡ ጠላቶቿ በየትኛውም ወቅት ሸብረክ ብላ፣ እጇን ሰጥታ አታውቅም። ጠላቶቿን በሙሉ እያሳፈረች ዘመናትን በድል ተሻግራለች። ኢትዮጵያውያንም ወራሪዎችንና ተስፋፊዎችን በአንድነት በመመከት አንፀባራቂ ታሪክ... Read more »