የትናየት- ተስፋን የሙጥኝ የማለት ምልክት

የትናየት ሰለሞን ትባላለች። በመዲናዋ አዲስ አበባ ተወልዳ በጎዳናዎቿ ተመላልሳለች። ባለ ትዳርና የአንድ ልጅ እናት ናት። ታታሪና ፈጣን ከመሆኗም በላይ ጭንቅላቷ አዲስ ነገርን ለመማር አይቦዝንም። ተስፋ መቁረጥ ከእርሷ ጋር ትውውቅ የለውም። በቃ የሚል... Read more »

‹‹ሴትነት የፆታ መገለጫ እንጂ የአቅምና የብቃት ማሳያ አይደለም››  ዮሐና ረታ የጎልደን ስታርስ ኮሌጅ ባለቤት

የብዙ ውጤታማ ሰዎች የስኬት መነሻ ከወደቁበት ለመነሳት በሚታገሉበት በዚያ ስፍራ እንደሆነ ታምናለች። ገና በለጋ እድሜዋ ያጋጠማትን ወድቆ የመነሳት አጋጣሚ እዚህ ለመድረሷ መሠረት እንደሆናት ትገልፃለች። ከገባችበት የተስፋ መቁረጥ ጎዳና ለመውጣትና ሌላ የሕይወት መስመር... Read more »

‹‹ብቁዋ ሴት ማጀት እንዳትቀር በሴት አክባሪ ሴቶች ትደገፍ›› ወይዘሮ ሲና ጌታቸው የሚዲያ ማናጀር

በትምህርት እውቀት ያካበቱ፣ በተሰማሩበት የሙያ ዘርፍም ችሎታ ያዳበሩ ሰዎች የሀገር ባለውለታና የሕዝብ አለኝታ እንዲሆኑ ይታሰባል። ሀገርም በእውቀት ከመጠቁት በትምህርት ካደጉት ዜጎቿ ብዙ ትጠብቃለች። ይሁን እንጂ የመማር እድሉን አግኝተው በትምህርት ከፍተኛ ደረጃ ላይ... Read more »

 ከፖለቲከኛነት ወደ በጎ ተቋም መስራችነት

ወቅቱ በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ነበር። የጊዜው ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ባለቤት ናቸው። ወይዘሮ ሙሉ ግርማይ ይባላሉ። ይህችን ምድር የተዋወቁት በቀድሞው አጠራር በወሎ ክፍለ ሀገር በሰቆጣ ከተማ ነው። በዚያው ስፍራ ጭቃ... Read more »

የአንድ ወገን ሕመም

የወር አበባ ሕመምና የሚያስከትለው የስሜት መዛባት ብዙዎች ቀላል አድርገው ይመለከቱታል። በመሆኑም አንድ ሴት በወር አበባ ሕመም ምክንያት ታምሜያለሁ ብትል ‹‹አታካብጂ›› የሚለው መልስ በብዙዎች ዘንድ የተለመደ መልስ ነው። ይህም ጉዳዩን በልኩ ካለመረዳት የመጣ... Read more »

ባለማዕረጓ – ሻምበል ማዕረግነሽ

ከቀናት መካከል በአንዱ የሌሊት ተረኛ ጥበቃ ላይ ተሰማርታለች። ጊዜው ውድቅት ነው፤ ከባድ የሚሉት ዓይነት ዶፍ ዝናብ ይጥላል። ልጇን በጀርባዋ አዝላለች፤ ከፊት ለፊቷ ደግሞ መሳሪያዋን አንግባለች። ከጀርባዋ ያለው የነገው ትውልድ ትኩረቷን ይፈልጋል፤ ወዲህ... Read more »

 የቀይ ቦኔቱ ፍቅር የሰንደቅ ዓላማው አደራ

ገና የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች አስተውላው የማታውቀው ነገር በሃሳቧ ይከሰታል። ዕለቱ ትምህርት ቤታቸው የወላጆች ቀን የሚያከብርበት ጊዜ ነበርና በትምህርት ቤቷ ቅጥር ጊቢ ተገኝታለች። በዕለቱ ከአካባቢያቸው ጬንቻ ከተማ፣ መከላከያ ሠራዊትን የተቀላቀለ አንድ ሰው... Read more »

‹‹በምድር ላይ ትልቁ ደስታ ያለው ለሰው በማካፈል ውስጥ ነው››ዶክተር መክሊት ፊሊጶስ የጉድ ሰመሪታን ፋሚሊ ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን መስራችና ሥራ አስኪያጅ

ተወልደው ያደጉት በሃዋሳ ከተማ ውስጥ ነው። በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እንዲሁም በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ዲግሪያቸውን ሰርተዋል። በተጨማሪም በፈረንሳይ ከሚገኘው አሴንሺያ ቢዝነስ ስኩል ከሚባል ተቋም በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የዶክትሬት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። በተለያዩ መንግስታዊ... Read more »

 ‹‹ዓለም በዕልህ እና በጦርነት የምትታመሠው ሴት ባለመደመጧ ነው››  ወ/ሮ እየሩሳሌም ሹምዬ፣ በአፍሪካ ሕብረት የጥናት ትንተና ክፍል ዋና ሃላፊ አማካሪ

ወልቃይት ፀገዴ ማይአይኒ በምትባል መንደር ውስጥ የተወለደችው እየሩሳሌም ሹምዬ፤ ገና በጨቅላነቷ ከሞት ጋር ታግላለች። ከቤተሰቦቿ ጋር ከአውሮፕላን የሚዘንበውን ቦንብ ሸሽታ በዋሻ ለቀናት ውላለች። ጊዜው 1980 ዎቹ አካባቢ በመሆኑ መንደራቸው የነበረው ጦርነት ቤተሰቦቿን... Read more »

የሀረሪ ሴቶች የእጅ ጥበብ ሥራ ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆን

ሀረሪዎች ቤት በድንገት የገባ እንግዳ ዓይኑን ከቤቱ ግድግዳ ላይ መንቀል አይችልም። በተለያየ ቀለማት የተለያየ መጠን ያላቸው በግድግዳ ላይ የተሰቀሉ የተለያዩ የስፌት ጌጣጌጦች በእጅጉ ትኩረት ይስባሉ። ስፌቶቹ ለቤቱ ድምቀት ከመስጠታቸው በተጨማሪ ውብ በመሆናቸው... Read more »