
“ባለ ትዳርና የመንግስት ሠራተኛ ነኝ። ልጅ የወለድኩት የመውለጃ ጊዜዬ ሊያልፍ በተቃረበበት ወቅት ነው። ሰው ባይረዳኝም ዘግይቼ የወለድኩበት የራሴ ምክንያት ነበረኝ” ሲሉ የእናትነት ተሞክሯቸውን ያካፈሉን ወይዘሮ ሣራ ገብረማርያም ናቸው። ወይዘሮዋ እንደሚናገሩት ዘግይተው የወለዱበት... Read more »

በጎ ሥራ በመስጠትና መቀበል ስሌት ባይለካም መታየትና ለሌሎች ምሳሌ መሆን ግን አለበት።ምክንያቱም አድራጊዎቹ ይበረታታሉ፤ ድጋፉን የሚያገኙ ሰዎችም ይበራከታሉ።እናም ዘንድሮ ለመጀመርያ ጊዜ በአገር ደረጃ በተከበረው የበጎ ፈቃደኞች ቀን ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር... Read more »

ጾታዊ ጥቃት ፈርጀ ብዙ ሲሆን ዓይነቱ ሴት ልጅን ወሲባዊ ወይም ጾታዊ ድርጊቶችን እንድትፈፅም ከማስገደድ ይጀምራል። ጾታዊ ወይም ወሲባዊ ምስሎችን እንድትመለከት ማስገደድ፤ የሰውነት ክፍሎቿን መነካካት፤ ድብደባ፤ ለከፋ ስድብ፤ ሌሎች ጥቃቶችን ይጨምራል። የፀረ ፆታዊ... Read more »

አዳማ አያቴ ጋር ለተወሰነ ጊዜ ኖሬያለሁ። ትምህርቴንም እዛው የመከታተል አጋጣሚውም ነበረኝ። ከከተማዋ ከወጣሁ በኋላም ቢሆን ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ ትምህርት በማይኖረኝ ሰዓት እየሄድኩ ጊዜን አሳልፍ ነበር። በዚህ አጋጣሚ አያቴ ጊቢ ካሉት ተከራዮች አንዱ... Read more »

ሕይወቷን ሙሉ ለጥበብ የሰጠች ነች። ይሄን ሕይወቷን የሚያጣፍጥላትን ሰላም አጥብቃ በመሻቷ በሰላም ግንባታ ዙርያ ሳታሰልስ ስትሰራ ቆይታለች። መላውን ኢትዮጵያውያን ስትደርስ የቆየችበትና‹‹ኢንተርሬይዝ ፒስ ፒውልዩጋግ›› የተሰኘው ተቋም ምስክር ይሆናታል። በተለይ በህፃንነቷ ስታገለግል ካደገችበት ሰንበት... Read more »

ሃውለት ሁሴን በአጣዬ ከተማ ሰላማዊ በተሰኘች ሰፈር ትኖራለች። ለዓመታት ሁለትና ሶስት ሰዓታትን በእግሯ ተጉዛ የመጠጥ ውሃ ስትቀዳ ቆይታለች። ውሃውን በጀሪካን ቀድታ በጀርባዋ አዝላ አንዴ ዳገቱን አንዴ ቁልቁለቱን ስትል ደክሟት ከቤት ትደርሳለች። አንዳንዴ... Read more »

ዛሬ ላይ ለመድረስ በሴትነቷ በርካታ ፈተናዎችን አልፋለች። ሆኖም የገጠሟትን ፈተናዎች በራሷ ጥረት ታግላ ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ከሚያስተምሩ ምሁራን መካከል አንዷ ለመሆን በቅታለች። ስሟ ዶክተር ትርሲት ሳህለድንግል ይባላል። በአዲስ... Read more »

ብዙዎቻችን ‹‹ ጎሽ ለልጇ ስትል ተወጋች›› የሚለውን አባባል ከእናቶቻችን ማንነት ጋር ማያያዛችን የተለመደ ነው። የአብዛኞቻችን ምክያታችንም ተመሳሳይ ይመስለኛል። እናት ለቤተሰቧ ስትል የማትከፍለው ነገር እንደሌለ ለማሳየት አባባሉ ተስማሚ ነው። አዎ እናት ስለቤተሰቧ ብዙ... Read more »

የጦርነት ወሬ ሽው ሲል ቅድሚያ ተጠቂዋም ተጎጂዋም ሴት እንደሆነች ሁላችንም እንስማማለን። ነገር ግን ጀብዱ ፈጻሚነቷን ለመቀበልና ለመናገር አንደበታችን ይያዛል። ስለጀግንነትና ጀብዱ ሲነሳ ሴቷ ትዘነጋለች። ለዚህ ደግሞ ዋነኛ ምክንያቱ ሚዛናዊ የሆነ አመለካከት ስለሌለን... Read more »

ስለ ‹‹ጠላ ቤት›› ሲነሳ በአብዛኞቻችን አዕምሮ ውስጥ ቀድሞ የሚመጣው የሴቶች ልፋትና ውጣውረድ ሊሆን ይችላል። አለፍ ስንል ደግሞ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚተዳደሩበት የሥራ መስክ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ከፍ ያለ ዋጋ ያላቸውን... Read more »