1ኛው ዙር የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ አበይት ክስተቶች

የ2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አንደኛ ዙር ውድድር በባህርዳር ስቴድየም ተከናውኖ ባለፈው ሳምንት በስኬት ተጠናቋል። ሁለተኛውን ዙር ውድድር የተረከበችው ድሬዳዋ ከተማም ከትናንት ጀምሮ ጨዋታዎችን እያስተናገደች ትገኛለች። ካለፈው የውድድር አመት በተለየ በግቦች ተንበሽብሾ የተጠናቀቀው... Read more »

ተቋርጦ የነበረው የ30 ኪሎ ሜትር ውድድር እሁድ በቢሾፍቱ ይካሄዳል

ተቋርጦ የቆየው የ30 ኪሎ ሜትር ጎዳና ላይ ሩጫ ከነገ በስቲያ በቢሾፍቱ ከተማ ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ላይም በዓለም አቀፍ ውድድሮች ስኬታማ መሆን የቻሉ ታዋቂ አትሌቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ... Read more »

ሙክታር ኢድሪስ በነገው የዴልሂ ግማሽ ማራቶን ለአሸናፊነት ይጠበቃል

የረጅም ርቀት የምንጊዜም ምርጡ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በአለም ምርጥ ከተባሉት የጎዳና ላይ ውድድሮች አንዱ የሆነው የዴልሂ ግማሽ ማራቶን አምባሳደር ተደርጎ መመረጡ ይታወቃል። ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አምባሳደር ሆኖ በመመረጡ ደስተኛ መሆኑን የገለጸ... Read more »

አፄዎቹ ወሳኙን የመልስ ጨዋታ ነገ በቱኒዚያ ያደርጋሉ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2014 ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ በሱዳኑ አል ሂላል በደርሶ መልስ ውጤት ተሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ሳያልፍ መቅረቱን ተከትሎ ኢትዮጵያን በአፍሪካ መድረክ የሚወክለው የፋሲል ከነማ... Read more »

በሳምንቱ መጨረሻ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ስኬታማ የሆኑባቸው የጎዳና ላይ ውድድሮች

 በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም እንዲሁም ሌሎች ደረጃዎች የተሰጣቸው ውድድሮች እንደተለመደው በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ተከናውነዋል። በእነዚህም ውድድሮች ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በውጤታቸው የራሳቸውንና የሃገራቸውን ስም ማስጠራት ችለዋል። የፕላቲኒየም ደረጃ ባለው የቺካጎ ማራቶን ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች... Read more »

የአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች መሻገር የተሳናቸው የእድሜ ጣጣ

አፍሪካ በእግር ኳስ ትልቅ አቅም ያላት አህጉር ብትሆንም እንደ ሌሎቹ አህጉራት ትልቅ ደረጃ መድረስ አልቻለችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ለአፍሪካ እግር ኳስ እንቅፋት ብለው ባለሙያዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ከሚጠቅሱት ምክንያት አንዱ በትክክለኛው እድሜ... Read more »

በግቦች የደመቀው የመጀመሪያ ሳምንት የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ

የ2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ባለፈው አርብ በባህርዳር ስቴድየም ተጀምሯል። ባለፉት ቀናትም የአንደኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተካሂደው ከትናንት በስቲያ ተጠናቀዋል። የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ይቀጥላሉ። ከዓምናው የውድድር ዓመት በተለየ በበርካታ ግቦች... Read more »

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በጎዳና ላይ ውድድሮች የደመቁበት ሳምንት

እየተገባደደ በሚገኘው የመስከረም ወር በተለያዩ የዓለማችን ታላላቅ ከተሞች በርካታ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሮች መካሄዳቸው የተለመደ ነው:: ባለፈው ሳምንት መጨረሻም በተመሳሳይ ከ5ኪሎ ሜትር አንስቶች እስከ ማራቶን በቁጥር በዛ ያሉ ውድድሮች ተካሂደዋል:: በእነዚህ ውድድሮች... Read more »

ያለምዘርፍ የኋላው የለንደን ማራቶንን በድንቅ ብቃት አሸነፈች

በየአመቱ በተለያዩ የአለማችን ከተሞች ከሚካሄዱ ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች ግንባር ቀደም በሆነው የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ ወጣት አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው ጣፋጭ ድል ተቀዳጅታለች። በደመናማና ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ታጅቦ ትናንት ውድድሩ ሲካሄድ ያለምዘርፍ በአስደናቂ ብቃት... Read more »

ቀነኒሳ በቀለ በነገው የለንደን ማራቶን የአሸናፊነት ግምት አግኝቷል

ከአለማችን ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች አንዱ የሆነው የለንደን ማራቶን ነገ ይካሄዳል። በዚህ ውድድር በርካታ የአለማችን የርቀቱ ከዋክብት አትሌቶች በሁለቱም ጾታ የሚያደርጉት ጠንካራ ፉክክር ይጠበቃል። በወንዶች መካከል በሚካሄደው ውድድር ጀግናው ኢትዮጵያዊ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ... Read more »