«በዓሉን የምናከብረው ስለሰላም በማስተማርና የተቸገሩትን በመርዳት ሊሆን ይገባል»  – ሼህ አብዱልሃሚድ አሕመድ(በኢትዮጵያ አስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት የመውሊድ በዓል ዋና አስተባባሪ)

የነቢዩ መሐመድ የልደት ቀን በበርካታ ሀገራት በሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ የሚከበር ሀይማኖታዊ በአል ነው። በዓሉ በሀገራችን ኢትዮጵያም በአስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ ነው። የዘንድሮውን የኢድ አለ... Read more »

 “አዲሱን ዓመት መቀበል ያለብን በአዲስ እይታ እና በአዲስ ተነሳሽነት ነው” ዘሪሁን ገብሬ (ዶ/ር) የሊድስታር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

የዛሬው የዘመን እንግዳችን ዘሪሁን ገብሬ (ዶ/ር) ይባላሉ። ዘሪሁን (ዶ/ር) የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የሰሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው። በሊድስታር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በማኅበረሰብ ልማት ‘Community Development’ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሰርተዋል። ትምህርታቸውን በአገር ቤት ብቻ... Read more »

 “ኢትዮጵያ የመስኖ ልማትን የትኩረት ማዕከሏ ማድረግ አለባት”በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የመስኖ ኤክስፐርት

የዛሬው የዘመን እንግዳችን በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር) ናቸው፤ ተወልደው ያደጉት አዲስ አበባ ነው። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በእርሻ ምህንድስና ትምህርት በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው ተመርቀዋል፤ ከተመረቁም በኋላ አነስተኛ ግድቦችን ሰርቶ ለመስኖ ልማት ማዋል ላይ ተግባራዊ አድርገዋል።... Read more »

‹‹አደጋን እየተከላከልን ማልማት፤ እያለማን አደጋን መከላከል የግድ ነው›› – በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ እና አስተማሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር መሣይ ሙሉጌታ ( ዶ/ር)

የትናንቱ የገጠር ተማሪ የዛሬው ተባባሪ ፕሮፌሰር እና ተመራማሪ ዶ/ር መሣይ ሙሉጌታ የተወለዱት፤ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ከገርበ ጉራቻ ከተማ በ5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሃሌሉ ጫሪ በምትባል የገጠር ቀበሌ... Read more »

‹‹ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ፤ በጋምቤላ ክልል በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል›› – አቶ ኡመድ ኡጁሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

ጋምቤላ 1899 ዓ.ም የተቆረቆረች ከተማ እንደሆነች የታሪክ ድርሳናት ይጠቅሳሉ፡፡ በክልሉ ሦስት የብሔረሰብ ዞን አስተዳደር ማለትም የአኙዋክ፣ የኑዌር እና የማጃንግ ብሎም የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር፣ የኢታንግ ልዩ ወረዳ እና ሌሎች አሥራ ሁለት ወረዳዎች ይገኛሉ፡፡... Read more »

 የኢድ አልአድሃ በዓል የመረዳዳት እና የመደጋገፍ በዓል ነው›› – ሀጅ ጦሃ ሃሩን -የአንዋር መስጊድ ኢማም

በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የኢድ አልአድሃ (አረፋ) በዓል አንዱ ነው። ኢድ አል አድሃ ወይም አረፋ ነብዩ ኢብራሂም ልጃቸው እስማኤልን በአላህ ትእዛዝ ለመስዕዋት ሲያዘጋጁ በምትኩ ሙክት በግ መቅረቡን የሚያስታውስ... Read more »

‹‹በክልላችን የሰለጠነ ፖለቲካ እንዲለመድና ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ መሰረት እየጣልን ነው›› – ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ መሃመድ

የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ከለውጡ በፊት የልማት እና የዲሞክራሲ ጥያቄ የሚነሳበት፤ የሰላም እና የጸጥታ ችግር የሚስተዋልበት ክልል ነበር፡፡ ክልሉ ሊታረስ የሚችል ሰፊ መሬት፣ ከፍተኛ መጠን ያለው የገጸ-ምድርና የከርሰ-ምድር ውሃ፣ የእንስሳት ሃበትና ማዕድናትን... Read more »

‹‹የማዕድን ዘርፉ አዳዲስ ዕድሎችንና ተጨማሪ ሀብት ይዞ እየመጣ ነው›› -አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ -የማዕድን ሚኒስቴር ድኤታ

ኢትዮጵያ እምቅ የሆነ ያልተካ የምድር ውስጥ በረከት ያላት ሀገር ነች።ይሁን እንጂ ለዘመናት ያህል የተፈጥሮ ፀጋዋን ሳትጠቀምበት ኖራለች።ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ማዕድን ከግብርና ቀጥሎ የኢትዮጵያን ብልጽግና እንደሚያረጋግጥ ታምኖበት በብዙ ተግዳሮቶችም ውስጥ ቢሆን ውጤት... Read more »

‹‹ለሀገራችን ከምክክር የተሻለ አማራጭ የለም››- አቶ እውነቱ አለነ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

የፖለቲካ ቁርጠኝነት ከሚታይባቸው ነገሮች መካከል የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ አንዱ ነው:: ለግንባታው ደግሞ ነፃና ገለልተኛ እንዲሁም ጠንካራ ተቋማት መገንባት የሚጠይቅ ተግባር መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ መንግሥት በአሁኑ ወቅት በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን... Read more »

‹‹አርሶ አደሩ ሲደገፍ ፤ሀገር ትደገፋለች›› – ጌታቸው ድሪባ ዶ/ር- የግብርና ሚኒስቴር አማካሪ

ተወልደው ያደጉት በገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍል በቀድሞው አሩሲ ክፍለ ሀገር ከአሰላ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው ዶሻ የገበሬ ማህበር ውስጥ ሲሆን በወቅቱም በነበረው የስውዲን ሚሲዮን ትምህርት ቤት የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በትምህርታቸው በጣም ጎበዝ... Read more »