ክረምት ይወዳል..ክረምት የነፍሱ ደስታ ነው:: ሰማይ ሲደማምን ጉም ሲውጠው የቀዬው ትዝታ ይወስደዋል:: አብዛኞቹ የልጅነት ትዝታዎቹ በክረምት የተፈጠሩ ናቸው:: አድጎ እንኳን የክረምት ፀጋ አልሸሸውም:: ትላንትም ዛሬም በክረምት ፀጋ ውስጥ ነው…. እየዘነበ ነው..:: እጆቹን... Read more »
በሕይወት ፋራፋንጎ ላይ ከፍና ዝቅ እላለው..ሃሳቤን ማሸነፍ አቅቶኝ፣ እውነቴን መርታት ተስኖኝ። ፋራፋንጎውን የሳተው ጋላቢው ልቤ ከዚህ እዛ እየወሰደ በማላውቀው መሬት ላይ፣ በማላውቀው ዓለም ላይ ይፈጠፍጠኛል። በተስፋ ማጣት ነፍሴ ተመጦ እንደ ተጣለ ሎሚ..ታኝኮ... Read more »
ማንበብ ስወድ ለጉድ ነው። ከዕለት ተዕለት ሱሶቼ መሐል በኩሩ ሆኖ እንደቡናና ትንባሆ ያዳክረኛል። የእውቀት ማረፊያው አእምሮ ነው። በልብ በኩል ደግሞ ስር ይሰዳል። የአእምሮ ብቻ መሆንና የአእምሮና ልብ መሆን የተለያዩ ማንነቶች ናቸው። የአእምሮ... Read more »
ኩርፊያ መልክ ቢኖረው ቁርጥ ሩታን ይሆን ነበር። ጠይም ዘለግ ያለ፣ አይኖቹ ከከዋክብት የተዋለዱ የሚመስሉ፣ ጸጉሩን ቁጥርጥር የተሰራ ኩርፊያ ለንቦጩን ጥሎ ካያችሁ አትጠራጠሩ ሩታን ነው። በዳመነ ፊት ከንፈሩን በጥርሱ እየበላ በአንድ የሆነ ቦታ... Read more »
በተወለድኩ በአርባኛው ዓመት በሠላሳኛው ቀን ለዘመናት ካሸለብኩበት ሞት አከል እንቅልፍ የመጀመሪያውን መንቃት ነቃሁ:: በዚህች መከረኛ ምድር ላይ እንደ ሲራራ ነጋዴ አርባ ዘመን ስመላለስ ህሊና የሚባለውን ብልት ለምን ፋይዳ አውለው እንደነበር ባላውቅም ያን... Read more »
ከቤቴ ስወጣ አራት መንታ መንገዶች ያገጡብኛል። መሀል ላይ ክብ ቅርጽ ሰርተው ሃሳቤን ይቀሙኛል። አንዱ ወደመስኪድ፣ አንዱ ወደስላሴ ቤተክርስቲያን፣ የተቀሩት ሁለቱ ወደማፈቅራት ሴት ሰፈር እና መቼም ልሄድበት ወደማልፈልገው የሆነ ሰፈር። ወደማፈቅራት ሴት ሰፈር... Read more »
እዚህ ከተማ ውስጥ ጠጅን እንደ ጠንክር የሚጠጣት ሠው አለ ቢሏችሁ እንዳታምኑ፡፡ ጠጅ ራሷ ጠንክር ካልጠጣት የተጠጣችም አይመስላት፡፡ ‹‹ልብስ መስቀያውን አገኘ›› እንዲሉ ጠጅም ብርሌዋን አገኘች ከተባለ ጠንክር ሰቦቃ ነው፡፡ ታድያ ጠንክር ጠጅ ብቻውን... Read more »
ሹል አፍ.. ከስሟ ቀጥሎ፣ ሁሉም ከሚያውቀው ሰማያዊ ፈገግታዋ ቀጥሎ መታወቂያዋ ነው። ስም ከማንነት ጋር ልክክ ያለላት ሴት ናት። እድል ሳይሰጣት ባተሌ ሆና ቀረች እንጂ እግዜር ሲሰራት ለንግስትነት አስቦ ከመሰለኝ ሰንበትበት ብያለው። ባለሰማያዊ... Read more »
አዲስ የገዛሁት ጫማ አቧራ ቅሞ ሳየው መሀረቤን ከኪሴ መዥርጨ አበስ አደረኩት። ወደእሷና ወደእናቴ ስሄድ ተሽቀርቅሬ ነው። እናቴ ፊት ጎስቋላ እሷ ፊት መሀይምና የማይረባ መምሰል አልፈልግም። በቸምቸሞ ጥቁር ጸጉሬ መሀል ያገጠጡ ያለጊዜያቸው የበቀሉ... Read more »
ቶሎ ቶሎ የሚርበኝ ነገር አለ። ከክፉ ገመናዎቼ አንዱ በቀን ስድስት ጊዜ መመገቤ ነው። እንደአመጋገቤ ግን አልፀዳዳም… ከሰው የበዛ በልቼ ከሰው ያነሰ ነው የምፀዳዳው። አንዱ የሚገርመውም ይሄ ነው፤ ሰው እንዳበላሉ አይፀዳዳም ነው የሚባለው... Read more »