የረፈደ ሩጫ

ጠባቧ ክፍል የተለያየ ቀለም ባላቸው አምፖሎች ደማምቃለች፣ ቦግ እልም በሚለው የብርሃን ፍንጣቂ ውስጥ አንዲት ተስፋ ቢስ ሴት ትታያለች። ፊቷ ላይ ሰላሳ ሁለተኛ ዓመቷን የሚያሳብቅ ሻማ ከነጭ ቶርታ ኬክ ጋር ተሰይሟል። የተለያዩ አይነት... Read more »

 መልኬ ውስጥ የበቀሉ ሳቅና እዬዬዎች

ከእናቴ ጋር ነው የምተኛው..የምነቃውም አብሬያት ነው። እሷ ጓዳ ጎድጓዳውን ስትንጎዳጎድ ቀሚሷን ይዤ በሄደችበት ሁሉ እከተላታለሁ። በልጅነቴ የእናቴ ጭራ ነበርኩ። ከጎኗ፣ ከስሯ፣ ከጉያዋ፣ ከቀሚሷ ስር ማንም ፈልጎ የማያጣኝ። ስንተኛ እጇን አናቴ ላይ ጥላ... Read more »

ከልጅነት ድርሳን..

ኦሎምፒክ ቁርስ ቤት ሠፈራችን አስፓልቱን ተሻግሮ ያለ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የተቀባ ብቸኛው ቁርስ ቤት ነው። የቁርስ ቤቱ ባለቤት አቶ አብዱቃድር ሁሴን ይባላሉ። ሰፈር ውስጥ ማንም አብዱቃድር ብሎ የሚጠራቸው የለም። ጋሽ አብዲ ነው... Read more »

ትንቅንቅ

ሕይወት ትንቅንቅ ናት፡፡ ከራስ ጋር፣ ከፈጣሪ ጋር፣ ከተፈጥሮ ጋር ከነዚህ ሁሉ ጋር፡፡ ከሁሉም ግን ከራስ ጋር የሚደረግ ትንቅንቅ ይከፋል፡፡ ከራስ ጋር ትንቅንቅ መልስን ደብቆ፣ እውነትን ሸሽጎ ነው። በማይገኝ መልስና በማይደረስ እውነት ውስጥ... Read more »

 የክረምት ፀጋ

ክረምት ይወዳል..ክረምት የነፍሱ ደስታ ነው:: ሰማይ ሲደማምን ጉም ሲውጠው የቀዬው ትዝታ ይወስደዋል:: አብዛኞቹ የልጅነት ትዝታዎቹ በክረምት የተፈጠሩ ናቸው:: አድጎ እንኳን የክረምት ፀጋ አልሸሸውም:: ትላንትም ዛሬም በክረምት ፀጋ ውስጥ ነው…. እየዘነበ ነው..:: እጆቹን... Read more »

 ከራስ ጋር ከፍና ዝቅ

በሕይወት ፋራፋንጎ ላይ ከፍና ዝቅ እላለው..ሃሳቤን ማሸነፍ አቅቶኝ፣ እውነቴን መርታት ተስኖኝ። ፋራፋንጎውን የሳተው ጋላቢው ልቤ ከዚህ እዛ እየወሰደ በማላውቀው መሬት ላይ፣ በማላውቀው ዓለም ላይ ይፈጠፍጠኛል። በተስፋ ማጣት ነፍሴ ተመጦ እንደ ተጣለ ሎሚ..ታኝኮ... Read more »

 ትንሽ ብቻ ዞር…

ማንበብ ስወድ ለጉድ ነው። ከዕለት ተዕለት ሱሶቼ መሐል በኩሩ ሆኖ እንደቡናና ትንባሆ ያዳክረኛል። የእውቀት ማረፊያው አእምሮ ነው። በልብ በኩል ደግሞ ስር ይሰዳል። የአእምሮ ብቻ መሆንና የአእምሮና ልብ መሆን የተለያዩ ማንነቶች ናቸው። የአእምሮ... Read more »

ጀምበር ግን ታድላ…

ኩርፊያ መልክ ቢኖረው ቁርጥ ሩታን ይሆን ነበር። ጠይም ዘለግ ያለ፣ አይኖቹ ከከዋክብት የተዋለዱ የሚመስሉ፣ ጸጉሩን ቁጥርጥር የተሰራ ኩርፊያ ለንቦጩን ጥሎ ካያችሁ አትጠራጠሩ ሩታን ነው። በዳመነ ፊት ከንፈሩን በጥርሱ እየበላ በአንድ የሆነ ቦታ... Read more »

 ወለፈንዲ

በተወለድኩ በአርባኛው ዓመት በሠላሳኛው ቀን ለዘመናት ካሸለብኩበት ሞት አከል እንቅልፍ የመጀመሪያውን መንቃት ነቃሁ:: በዚህች መከረኛ ምድር ላይ እንደ ሲራራ ነጋዴ አርባ ዘመን ስመላለስ ህሊና የሚባለውን ብልት ለምን ፋይዳ አውለው እንደነበር ባላውቅም ያን... Read more »

ከአፈር ወደአፈር

ከቤቴ ስወጣ አራት መንታ መንገዶች ያገጡብኛል። መሀል ላይ ክብ ቅርጽ ሰርተው ሃሳቤን ይቀሙኛል። አንዱ ወደመስኪድ፣ አንዱ ወደስላሴ ቤተክርስቲያን፣ የተቀሩት ሁለቱ ወደማፈቅራት ሴት ሰፈር እና መቼም ልሄድበት ወደማልፈልገው የሆነ ሰፈር። ወደማፈቅራት ሴት ሰፈር... Read more »