ሰርተው በድካማቸው የሚያድሩ፣ ቸርችረው ባገኙት ሽርፍራፊ ሳንቲም ኑሮዋቸውን የሚደጉሙ ታታሪ እናት ናቸው። ዛሬ ገበያ አልቀናቸውም፤ ያሰቡትን ሽጠው ጨርሰው የፈለጉትን መሸመት አልቻሉም። ድካም የበዛበት ውሎ አሳልፈው ምሽት ላይ ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ነው። ከገበያተኛ... Read more »
ሜክሲኮ ወደ ቄራ የሚወስደው መንገድ መታጠፊያ በታክሲ ጥበቃ በቆሙ ሰዎች ተሞልቷል። ሰልፍ ይዘው ወደየቤታቸው ሊያደርሳቸው የሚጠባበቁ ሰዎች አንገታቸውን አስግገው የታክሲ መምጣትን ይጠባበቃሉ። የያዝኳትን ላዳ ታክሲ ከታክሲ መጠባበቂያ ቦታው አለፍ አድርጌ አቆምኳት። ምን... Read more »
እሁድ ነው፤ የእረፍት ቀን:: እረፍት ለሀና ቅንጦት ነው:: ለእርሷ ዛሬን እቤት እንድትውል ህይወትዋ አልፈቀደላትም:: የልጆችዋን ቁርስ አሰናድታ ሲነሱ ማግኘት የሚችሉበት ቦታ ላይ አኑራ እየተጣደፈች ከቤት ወጣች:: ወደ ስራዋ ፈጥና መድረስ አለባት:: ማታ... Read more »
ሰርገኛውና የሙሽሮቹ አጃቢዎች በጭቃ በላቆጠው ጠባብ መንገድ ላይ እየተጋፉ ጭፈራውን ያስነኩታል።“ሀይሎጋ ..ሀይሎጋ ሆ.. አይሎጋ…. ኧረ ጎበዝ አህምነው” ይላሉ።እኔም አሻግሬ ውዴን እያየሁ በቀስታ እጓዛለሁ።የጓደኛዬ ሰርግ ነው።በተገኘሁበት ላይ ሁሉ ቀልቃላ የነበርኩት እኔ ያለወትሮዬ ጭር... Read more »
ጭርርር……ጭርር… እጅግ የምጠላው ነገር ግን ዘወትር ራስጌዬ እያደረኩት ደጋግሜ የምሰማው ማንቂያ ደወል ከሞቀው እንቅልፌ አባነነኝ። እንደ ምንም በእጄ አጥፍቼው እምር ብዬ በመነሳት መለባበሴን ጀመርኩ። በፍጥነት ወደ ስራ የሚያዳርሰኝ ሰርቪስ እንዳያመልጠኝ መሮጥ በስራ... Read more »
ፀሀይ ወገግታዋን ተነጥቃና በጉም ተሸፍና ብቅ ብላለች። አይኑ ብርሀን ካየ እንቅልፍ የሚባል ነገር አይወስደውም ። ጭለማ ያስፈራዋል። እሱን ለመሸሽ በጊዜ መተኛትና ጭለማው ሲገፈፍ መንቃት ተላምዶታል። እንደ ለመደው ሰማይ ሲገለጥ ከእነቅልፉ እንደባነነ ለሰዓታት... Read more »
ዘላለም የሳጥንወርቅ (የእፀሳቤቅ አባት) ለሊት ነው ሰባት ሰዓት..ጨረቃ በዳፍንት በትር ሰኮናዋን ተብላ ከህዋው ጉያ ውስጥ ተደብቃለች።የሰኔን የሚመስል ጥቁር ጽልመት ምድርን ውጧታል። ፍርዱ በእንቅልፍ ልቡ አልጋው ላይ ይገላበጣል..በህልሙ መላዕክ የምትመስል ቀይ ሴት እንደ... Read more »
ዘላለም የሳጥንወርቅ (የእፀሳቤቅ አባት) ሰማዩ ግርጌ ላይ አንድ ሀሙስ የቀራት እሳታማ ጀንበር ተንጠልጥላለች።በእሳታማው የብርሀን ፍንጣቂ የደማመቀው አድማስ ሁለት መልኩን ይዞ ከተራራው ጋር ተሳስሟል።ምድር በብርዳማው የጥቅምት ውርጭ እትት ትላለች። ከዳመነ ሰው ቀን ጋር... Read more »
ተገኝ ብሩ አካባቢው ሰው የማይላወስበት ምድረ በዳ ይመስል ጭር ብሏል። የፀሐዩ ንዳድ ሁሉንም ሰው በየቤቱ በየስርቻው ከቶታል። ንፋሱም እንደ እሳት ወላፈን ይጋረፋል። አንድ ጎልማሳ እንደ ነገሩ ከላዩ ላይ የጣለው ስስ ነጠላ ከሰውነቱ... Read more »
ዘለዓለም የሳጥን ወርቅ (የእፀ ሳቤቅ አባት) ታክሲ ውስጥ ነው፤ ወደ ሃያ ሁለት እየሄደ። ፊቱን ወደ ግራ አዙሮ በመስተዋቱ ወደ ውጪ ያያል። አዲስ አበባን ይመለከታል፤ ጉዷን፣ ቆነጃጅቷን..ትናንቱን ዛሬውን ሁሉ። ማየት ይወዳል። በተለይ ቆንጆ... Read more »