መላጦች በማበጠሪያ ሲጣሉ…

ያለነው ጸጥ ባለ ባህር ላይ አይደለም፤ ገና የሚሰክኑ፣ ገና የሚታረሙና ገና የሚረጋጉ ነገሮች አሉን። ይህ የለውጥ ህግ ነው። በለውጥ ውስጥ አንድ ዓይነት ገጽ የሚባል የለም። ለውጥ፣ ልዩ ልዩ ገጾች አሉት። ይህ ለኢትዮጵያችን፣... Read more »

የሰው ልጅ ክፉ ነውን?

የአሜሪካ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን፣ ኔልሰን ማንዴላ ከእስር ተለቅቀው፣ ፕሬዚዳንት በሆኑበት በዓለ ሲመት ላይ ከተገኙ በኋላ አብረው የሮብን ደሴት እስር-ቤትን ጎብኝተው ነበር:: ለማንዴላ የ27 ዓመት ሙሉ መኖሪያቸው ነበረና ጉብኝት ሳይሆን የመጨረሻ ስንበት... Read more »

ሐሜትና ሐሜተኞች

ሐሜት ጠባያዊ ነጸብራቅ ነው። ሐሜት የሚያማውን ሰው እያዋራ ታሚው ሰው መልስ በማይሰጥበት ርቀት ላይ የሚገኝበት አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎች፣ በሹክሹክታ የሚከውኑት የአፍ ሥራ ነው። አዎ አፋቸው ነው፤ ሥራውን የሚሰራው፤ መቆያ... Read more »

ተዉን ስላልን ይተዉን ይሆን?

 በህይወታችን ውስጥ፣ የሚያጋጥመንን ፈተና ተው፤ ብንለው እንደማይሰማን እናውቃለን፤ ፈተና አግቢዎቹን እንዲሁ ተዉን ብንላቸውስ ይተዉን ይሆንን ?እንዲህ እያሰብኩ ያለሁት እም ኀበ-አልቦ አይደለም። በአሁኑ ሰዓት በዓለም ዙሪያ እየሆነ ያለውን ድርጊትም በሉት ክንውን ከማየት በመነሳት... Read more »

ጥላቻ የሚቀጣጠል ገለባ ነው !

ፖለቲከኞች ምን ይደስኩሩ…ሰባኪያንስ ምን ይስበኩ….ንግግር አዋቂዎች ምን ይናገሩ? ብለን ሰሞኑን ከጠየቅን አቻ የሌለውን ገንቢ ቃል ፍቅርን ይስበኩ፤ ይደስኩሩ፤ ይናገሩ። እንደእርሱ ለሰው ልጆች ፣ የሚያዋጣን ነገር እንደሌለ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ በአሜሪካ የተፈጠረውና እስካሁን... Read more »

በማይቻል ጊዜ የሚቻል አንዳንድ ነገር

ይህ ወር በተለይም ግንቦት 9/1945 ዓመተ ምህረት ተስፋፊውን የናዚ ጀርመን ጦር ድባቅ በመምታት የተባበሩት ሃይሎች የድል ብስራት ያሰሙበት ወር ነው። የማይቻል የሚመስለውን ጦርነት እንዴት በድል ተወጡት? ብለን በመጠየቅ መልስ የምናገኝበት ታሪክ ነው፤... Read more »

መጋጋልና ማጋጋል ወይስ መስከንና ማስከን

መጋጋልና ማጋጋል ወይስ መስከንና ማስከን  በሰው ልጅ የአኗኗር ባህል ውስጥ ነገር እንደያዥው መሆኑ የታመነ ነው። ሰው በህይወት አጋጣሚ በሥራው በትዳሩ፣ በተሰጥኦው፣ በሙያው፣ ከሰዎች ጋር መገናኘቱ እውነት ነው። ሁሉም ነገር ፣ ቢኖርህ ያለሰው... Read more »

መተኛትና ማንቀላፋት

አሁን በቀደም እለት፣ በአንድ የንግድ መደብር ውስጥ ሶስት ሜትር በሁለት ሜትር የሚያክል፣ ትልቅ አልጋ ተንጣልሎ አየሁና ዋጋውን ስጠይቅ 32 ሺ ብር ነው፤ አሉኝ። እኔ የምለው… በዚህ አልጋ ስተኛ አባብሎ እንቅልፍ ይወስደኛል ወይስ... Read more »

ጨው ለራስህ ስትል…

የሚያናግረን፣ የሚያስጽፈን፣ የሚያስዘምረን፣ የሚያነጫ ንጨን፣ የሚያስቆጣን፣ የሚያስደስተን የሚያሳዝነንና የሚያቆላጨን የሰው ልጅ ነገር ነው። የራሳችን ነገር! በዚህ ጉዳይ እውነት እውነቱን እንድንነጋገር ነው፤ ይህንን ርእስ ያነሳሁት። የሰው ልጆች፣ በተለይም በዕድሜ ከፍ ያልን ነን ብለን... Read more »

የሞራል ድጋፍ እንጂ ለምን ስብራት እንሁን?

የእኛ የኢትዮጵያውያን የአኗኗር ስልት እርስ በእርሱ የተጎናጎነ ነው። በሰፈር በጉርብትና፣ በእድር፣ በእቁብ፣ በሀዘንና በደስታ፣ በሥራ ቦታ፣ በቤት አሰራራችን ብቻ በሁሉም መስክ ትስስራችን የበረታ ነው። ይህ መልካም መስተጋብራችን የአንዱ ቤት ሀዘን ለሌላው ቤት፣... Read more »