ጠቃሚ ሃሳቦችን በረቂቅ አዋጁ የማካተት ሥራ ይሠራል

አዲስ አበባ፡– የሪል ስቴት ልማትና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ላይ ገዥ እና ጠቃሚ የሆኑ ሃሳቦችን በማካተት አዋጁ እንዲጸድቅ የማድረግ ሥራ እንደሚሠራ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት... Read more »

 በተኪ ሕክምና ግብዓት አቅርቦት ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪን ማስቀረት ተችሏል

የሀገር ውስጥ የመድሃኒትና የህክምና መገልገያ አቅርቦት ሽፋኑ 36 በመቶ ደርሷል አዲስ አበባ፡- በ2017 በጀት ዓመት መጀመሪያው ሩብ ዓመት በሀገር ውስጥ ሕክምና ግብዓት የምርት አቅርቦት ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ወጪን ማስቀረት... Read more »

 “የኢትዮጵያ የመልማት እጣ ፈንታ የሚወሰነው በዓባይ ተፋሰስና ወደ ትልቁ ናይል በሚገቡ ወንዞቻችን ነው” – ፕሮፌሰር መኮንን አያና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምህንድስና መምህርና ተመራማሪ

አዲስ አበባ፦ የኢትዮጵያ የማደግና ያለማደግ፤ የመልማትና ያለመልማት እጣ ፈንታ የሚወሰነው በዓባይ ተፋሰስና ወደ ትልቁ ናይል በሚገቡ ወንዞቻችን እንደሆነ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር መኮንን አያና አስታወቁ።... Read more »

 “የኮሪደር ልማት ዋነኛ ግብ ለትውልድ የተሻለ ከተማና ሀገር መገንባት ነው” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፦ የኮሪደር ልማት ሥራ ዋነኛ ግብ ለትውልድ የተሻለ ከተማና ሀገር መገንባት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለውን ሁለተኛ ምዕራፍ የኮሪደር... Read more »

 ታሪክ ቀያሪዎቹ የቱሪዝም ዘርፉ ፈርጦች

ዜና ትንታኔ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበሰቃ ሀይቅ ላይ የተገነባውን “ቤኑና መንደር”ን መርቀው ከፍተዋል። በመዲናዋ በገበታ ለሸገር፣ በክልሎች ደግሞ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ታሪክ ቀያሪ የቱሪዝም ልማት ሥራዎች ተከናውነው ለአገልግሎት በቅተዋል።... Read more »

 ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የህክምና መሣሪያዎችን ለሆስፒታሎች አስረከቡ

አዲስ አበባ፡- ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው 41 የአእምሮ ሁኔታን በተለይም የሚጥል በሽታ ለመለየት እና ለመመርመር የሚያስችሉ የህክምና መሣሪያዎችን ለሆስፒታሎች በስጦታ ለግሰዋል። የህክምና መሣሪያዎቹን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙ... Read more »

የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራና አካባቢ ጥበቃ ሥራ የሚያሳይ መካነ-ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፡- በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ ባለው የኮፕ29 ጉባዔ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ እና አካባቢ ጥበቃ እየሠራች ያለችውን ሥራ የሚያሳይ መካነ-ርዕይ (ፓቪሊየን) በፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ተመርቆ ተከፍቷል። ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በታዳሽ... Read more »

በዓሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላቸውን እንዲለዋወጡና አንድነታቸውን እንዲያጠናከሩ እያስቻለ ነው

አዲስ አበባ፡- በየዓመቱ ህዳር 29 ቀን የሚከበረው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ባህላቸውን በመለዋወጥ ዴሞክራሲያዊ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ እንደሚረዳ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ። 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና... Read more »

 በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት የሀገሪቱ የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ከፍተኛ እምርታ አሳይቷል

-ኢትስዊች ካፒታሉን ከ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረስ ችሏል -ከአንድ ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ አስመዝግቧል አዲስ አበባ፡- በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የሀገሪቱ የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ከፍተኛ እምርታ አሳይቷል ሲሉ... Read more »

ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ሰብሎችን መሰብሰብ ይገባል

አዲስ አበባ፡- በህዳር ወር በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በመኸር ሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ አርሶ አደሩ ሰብሎችን የመሰብሰብና በአግባቡ የመከመር ተግባራትን ማከናወን እንደሚኖርበት የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስትቲዩቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት... Read more »