የሐረርጌው የሙዚቃ ፈርጥ- ቀመር ዩሱፍ

 ያኔ ለብዙ ኢትዮጵያውያን “ማነው?”ያስባላቸውና በድምጹ፣ በእንቅስቃሴውና በሙዚቃ ቪዲዮቹ ጥራት የተደነቁበት፣ የአፋን ኦሮሞ ድምጻዊው ቀመር ዩሱፍ የሙዚቃ ቪዲዮ ከወጣ 17 ዓመታትን ተሻገረ። በሙዚቃ ቪዲዮው ላይ “ሄሎ”፣ “ኦሮሚያ”፣ “ነነዌ” እና ሌሎችም ተወዳጅ ሙዚቃዎቹ ተካተዋል፡፡... Read more »

በቴሌቪዥን መስኮቶች

አዕምሮ በሥራ ሲጨናነቅ አልያም በሃሳብ ሲወጠር ለአፍታ ዘና የሚያደርገውን ቢያገኝ አይጠላም። እንዲህ በሆነ ጊዜ የምርጫው ጉዳይ እንደየ ሰው ፍላጎትና አቅም ሊለያይ ይችላል። አንዳንዱ ከከተማ ወጣ ብሎ ከባህር ዳርቻው አሸዋ ጋደም ማለት ፍላጎቱ... Read more »

 ጥላ

 ነፍስ ጥላ ናት… ከዚህ ወደዛ መራመጃ፡፡ ብዙ ደክሞኝ የማርፈው በፈገግታዋ ጥላ ውስጥ ነው፡፡ ማንንም የሚያሳርፍ የደግነት ጥላ አላት፡፡ ምን እንደሆንኩ አልነግራትም መከራዬን ላጋባባት ስለማልፈልግ ደህና መስዬ እታያታለሁ፡፡ መኖር አባዝኖኝ፣ ሕይወት አንከራቶኝ እየሳኩ... Read more »

የሀገር ፍቅር በጥላሁን ገሰሰ አንደበት

ተፈጥሮ ሳትሰስት ያለልክ በለገሰችው ድምፁ የተቹትን ሁሉ ሳይቀር በዙሪያው አሰባስቦ በሃሴት ያስጨፈረ የመድረክ ላይ ንጉስ እንደነበር ይነገርለታል። የሃገሪቱን ዘመናዊ ሙዚቃ በምርኮው ውስጥ ያዋለ ጀግናም እንደሆነ ምስክርነታቸውን ይሰጡለታል። ከሁሉም በላይ ግን ሀገር ወዳድነቱን... Read more »

 ትኩረት ያጡት የሙያ ትምህርቶች

የመስከረም ወር የትምህርት መጀመሪያ ወር ነውና ትምህርታዊ አጀንዳዎች ይበዛሉ፡፡ በተለይም በዚህ ዓመት ደግሞ የተለመደው የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ እንዲሁም የቅድመ ምረቃ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ብቻ አይደለም አጀንዳ የሆነው። የድህረ ምረቃ ትምህርትም በዚህ... Read more »

 አዲስ ዘመን ድሮ

አዲስ ዘመን ድሮ ዛሬም ተመዘው የማያልቁ ብዙ የትናንት ትውስታዎች አሉት። ከእነዚህም መካከል ለዛሬ ቆየት ያሉና በይዘታቸው ወጣ ያሉ አስገራሚ ክስተቶችን ከጋዜጣው የዘገባ ማህደሮች መዘን እናስታውሳለን። በአለቃው አይን ሚጥሚጣ ጨምሮ በጩቤ የወጋው ግለሰብ... Read more »

 ኢትዮጵያውያን የደመቁበት የዓለም የጎዳና ላይ ቻምፒዮና

በተያዘው የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት የቀናት ልዩነት ሶስተኛው የዓለም ክብረወሰን በሴቶች የአንድ ማይል ውድድር ተመዝግቧል። በቡዳፔስቱ የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ1ቨሺ500 ሜትር የብር ሜዳሊያ በማጥለቅ በርቀቱ ያላትን ተስፋ ያሳየችው ወጣቷ አትሌት ድርቤ ወልተጂ ደግሞ... Read more »

 የተባባሪዎቹ ጉዞ እስከ የት?

ጊዜው ሳብ ቢልም አብዛኛው ሰው ያስታውሰዋል ብዬ አስባለሁ። በአንድ ወቅት ድንገት ደርሶ በተዛመተ ጭምጭምታ ጨው ከሀገር ሊጠፋ ነው የሚል ወሬ ተወለደ። ይህ እንደዋዛ ሽው ያለ መረጃ ታዲያ ውሎ አድሮ እየገዘፈ ከአብዛኞች ጆሮ... Read more »

 በሞዴሊንግ ሙያ ባለሙያዎችን ከማፍራት ባሻገር

በዓለም ላይ በርካታ ታዋቂ ሞዴሎችን በሞዴሊንግ ሙያ ማፍራት ተችሏል:: በአገራችንም እንዲሁ በራሳቸው ጥረት ነጥረው የወጡ ሞዴሎች አሉ:: ከእነዚህም መካከል ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኙ እንደ ሊያ ከበደ፣ገሊላ በቀለ እና ሀያት አሕመድ ተጠቃሽ የሞዲሊንግ... Read more »

በሙዚቃው ‹‹ኦሴ ባሳ›› የሚጠራው አቀንቃኝ

እናቱና አባቱ ተስማምተው በሀገር ወግ መጠሪያ እንዲሆነው ያወጡለት ሥም ጸጋዬ ይሰኛል። ሙሉ መጠሪያው ጸጋዬ ሥሜ። ድምጻዊ የግጥምና ዜማ ደራሲነት ደግሞ የተሰጠው መክሊቶቹና መተዳደሪያው ናቸው። በቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በቅርቡ በአዲስ... Read more »