ጆሮ ጤና አያስፈልገውም?

የድምጽን ነገር (በተለይም ቅጥ ያጣ የተሽከርካሪ ክላክስ) እግረ መንገድ ብዙ ቀን አንስተን እናውቃለን። እስኪ ዛሬ የድምጽ ብክለትን ነገር ብቻውን እንየው፡፡ ስለሰለጠኑ ሀገራት ሳስብ፤ የረቀቀ ቴክኖሎጂ፣ ፈጣንና ምቹ መሰረተ ልማት ወይም ሌላ የሥልጣኔ... Read more »

 በግርግሩ መሐል …

አንዳንድ ቀን አለ። የቀን ጎዶሎ ይሉት ክፉ። ካላሉት ጥግ የሚያውል፣ ካላሰቡት መከራ የሚጥል። ካልገመቱት፣ የሚሰድ፣ ካላቀዱት ስር የሚወሽቅ። ይህን ቀን ደጋግመው ‹‹አይጣል! አያድርስ›› ቢሉት ከመሆን ይዘል አይመስልም። ደርሶ የነበረን ፀጋ ሲገፍ፣ ክቡር... Read more »

ሥልጡኖች በምን በለጡን?

ማህበረሰባዊ የአስተሳሰብና የአመለካከት መሰልጠንን፣ በአጠቃላይ ዘመኑ የደረሰበትን ንቃት በተመለከተ፤ በዚህ በትዝብት ዓምዳችን ብዙ ብለናል። መሰልጠንን ስናነሳ ማንፀሪያ የምናደርገው አሜሪካና አውሮፓውያንን መሆኑ ግልጽ ነው። ሥልጣኔ ሲባል፤ የግድ በእነርሱ ‹‹ስታንዳርድ›› ብቻ መሆን አለበት ማለት... Read more »

ከሱቆቹ ሆድ …

በሰው ልጆች ማንነት ውስጥ አንዳንዴ ራስን የመውደድ ልማዶች ጎልተው ይታያሉ። ይህ እውነታ ደግሞ የተፈጥሯዊ ሥብዕና መገለጫ ነው። ከዚህ አኳያ ማንም ራሱን ከፊት አስቀድሞ ስለሌሎች ችላ ብሎ ቢገኝ ለምን ብሎ መቃወሙ ተገቢ ላይሆን... Read more »

አስኳሉን ብቻ በልተን አልቀረንም አስኳላ ትምህርትም ገባን

ወንደላጤ ጓደኛሞች አብይ ጾምን ለመቀበል ከአንድ ታዋቂ ስጋ ቤት ተቀምጠናል፡፡ ብርንዷቸውን ለመቁረጥ ያላቸውን የብር መጠን ሲያሰሉ ጥብስ ነው የምንበላው ብዬ ራሴን ከቁርጡ አገለልኩ፡፡ ጦይሌው ደግሞ “ዛሬስ የትኛው መጽሐፍ ቅዱስ ብርንዶ እንዳይበላ ከልክሎ... Read more »

የሞተር ሳይክሎቹ ነገር…

ከቢሮዬ ብዙም በማይርቁ ህንፃዎች፣ በየፎቁ ማረፊያ ላይ ዘወትር የሚታየው የቡና አቀራረብ ይማርካል። እሱን ተከትሎ በወጉ ከሚቆላው ቡና ለአፍንጫ የሚደርሰው ልዩ መዓዛ ፣ የሻይ ቅመም ሽታ … ብቻ ምን አለፋችሁ ቦታውን አልፎ ለመሄድ... Read more »

‹‹መቀመጥ መቆመጥ››

ድርጅታችን ከጤና ተቋማት ጋር በመተባበር በየጊዜው ለሠራተኞቹ የጤና ምርምራ ዕድሎችን ያመቻቻል:: በቅርቡም ከአንድ የጤና ተቋም ጋር በመነጋገር የተለያየ አይነት የጤና ምርመራዎች ተደርገዋል:: ከዓመታት በፊትም የአካል ደህንነት (General Wellness) ላይ የሚያተኩር ሥልጠና ተሰጥቶ... Read more »

 የደብተር ሽፋን

ትምህርት በተጀመረበት ሳምንት ከአንድ የቤተሰብ አባል ጋር ሆነን ለዘመድ ልጆች ደብተር ለመግዛት በየሱቆች ዞር ዞር እያልን ነበር። ከአንደኛው ሱቅ ገዝቶ መጣ። የደብተሮችን ሽፋን እያየን እኛ ስንማር ከነበሩት ጋር እያነፃፀርን ነበር። እሱ የሒሳብ... Read more »

‹‹ እንኳንም ቀረብሽ … ››

መቼም ዘንድሮ ይህ ማኅበራዊ ሚዲያ ይሉት ጉዳይ አያሳየን የለም። ሰሞኑን ከአንዲት ወዳጄ ገጽ ደርሶ ያየሁት አንድ ወሬ በእጅጉ ሲያስደንቀኝ ከረመ። ነገሩ እንዲህ ነው። አንድ ከፍ ያለ ባለ ክሬም ኬክ ዙሪያው በቀለማት ደምቆ... Read more »

 ድንገተኛ ታዋቂነት ብቻውን ሲመጣ

‹‹አታሞ በሰው እጅ ያምር፤ ሲይዙት ያደናግር›› የሚባለው አባባል በየአጋጣሚዎች ልንጠቀመው የሚያስገድድ ገላጭ አባባል ነው። ‹‹ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው›› የሚለውም ይተካዋል። የእነዚህ ሁለት ምሳሌያዊ አነጋገሮች ትርጉም፤ እኛ ልናደርገው የማንችለውን ነገር፣ ሌላ ሰው ሲያደርገው... Read more »