ድስት ጠጋኙ አባ ጎሹ የአይኖቻቸውን እዳሪ በእጃቸው እያባበሱ የማለዳዋን ጀምበር ተከትለው ከቤት ወጡ።ለአንድም ቀን ከጎባጣ ጀርባቸው ላይ ወርዶ የማያውቀው አሮጌ ማዳበሪያ በስብርባሪ ብረታ ብረት ተሞልቶ ዛሬም እንደታዘለ ነው።የሁልጊዜም ጸሎታቸው የማዕድ ቤት ድስቶች... Read more »
ከእኔና ከእማዬ ማን እንደሚበልጥ በቅርብ ነው ያወኩት ። እማዬ እናቴ እንደሆነች የገባኝ ብዙ ዘግይቼ ነው ። ታላቅ እህቴ ነበር የምትመስለኝ ። ጡቷን እየጠባሁ አድጌ፣ በክንዷ ታቅፌ፣ በጀርባዋ ታዝዬም እናቴ አትመስለኝም ነበር ።... Read more »
በህይወት ፋራፋንጎ ላይ ከፍና ዝቅ እላለው..ሀሳቤን ማሸነፍ አቅቶኝ፣ እውነቴን መርታት ተስኖኝ። ፋራፋንጎውን የሳተው ጋላቢው ልቤ ከዚህ እዛ እየወሰደ በማላውቀው መሬት ላይ፣ በማላውቀው ዓለም ላይ ይፈጠፍጠኛል። በተስፋ ማጣት ነፍሴ ተመጦ እንደ ተጣለ ሎሚ..ታኝኮ... Read more »
አባቴ ባርኔጣ ሲያደርግ አልወድም። አንድም ቀን ግን የአባቴን ራስ ያለባርኔጣ አይቼው አላውቅም። ተወልጄ እቅፉ ውስጥ ቦርቄ፣ ዩኒቨርሲቲ እስከላከኝ ቀን ድረስ አባቴን የማውቀው በባርኔጣ ነው። ለብሶና ዘንጦ በዛ ሽቅርቅርነቱ ላይ ባርኔጣውን ሲደፋ ሞገሱ... Read more »
የትም ቦታ ምንም ነው፡፡ ሞልቶ ከፈሰሰ እልፍ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ልብ የሚወደውን ያክል መጥላትም እንደሚችል ቆይቶ ነው የገባው፡፡ አንዳንድ እድሎች አሉ፣ አንዳንድ ቀኖች አሉ፣ አንዳንድ አጋጣሚዎች አሉ የሚደገሙ መስለው ከታሪክ የሚሰወሩ፡፡ ስንስቅ..ስቀን ስንሰነብት... Read more »
በመዶሻና በኩርንችት ሚስማር ተከብቤ፣ የሰባት ሰዐቷ ጸሀይ አንጸባርቃብኝ፣ በላብ ቸፈፍ ተጠምቄ፣ መሬቱን በጥፍሮቼ ቆንጥጨ፣ ተረከዜ ላይ ተደላድዬ ቁጢጥ ብያለው..ባለፈው ሁለት ሳምንት ቅናሽ ሆኖ ሳገኘው ጥሩ መስሎኝ የገዛሁትን ሶሉ የለቀቀብኝን የቻይና ጫማ እየጠገንኩ።... Read more »
ኦሎምፒክ ቁርስ ቤት ሰፈራችን አስፓልቱን ተሻግሮ ያለ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የተቀባ ብቸኛው ቁርስ ቤት ነው። የቁርስ ቤቱ ባለቤት አቶ አብዱቃድር ሁሴን ይባላሉ። ሰፈር ውስጥ ማንም አብዱቃድር ብሎ የሚጠራቸው የለም። ጋሽ አብዲ ነው... Read more »
ከእናቴ ጋር ነው የምተኛው..የምነቃውም አብሬዐት ነው:: እሷ ጓዳ ጎድጓዳውን ስትንጎዳጎድ ቀሚሷን ይዤ በሄደችበት ሁሉ እከተላታለው:: በልጅነቴ የእናቴ ጭራ ነበርኩ:: ከጎኗ፣ ከስሯ፣ ከጉያዋ፣ ከቀሚሷ ስር ማንም ፈልጎ የማያጣኝ:: ስንተኛ እጇን አናቴ ላይ ጥላ... Read more »
ዘመኔን የጨረስኩት ከእናቴ ጋር እየተኛሁ ነው። አድጌና ትዳር ይዤ እንኳን ከሚስቴ ቀጥሎ ከእናቴ ጋር የምተኛ ነኝ። አንድ እህት አለችኝ..ሽንታም እህት። ለእናቴም አንድ ለእህቴም አንድ ስለሆንኩ እናትና እህቴ እኔን መሀል አድርገው ነው የሚተኙት።... Read more »
‹ትሁት..አንቺ ትሁት..› በእንቅልፍ ልቤ የእናቴን ድምጽ ሰማሁት:: እናቴ በእውኔ ብቻ አይደለም በህልሜም ያለች ሴት ነች:: በህይወቴ የትም ቦታ አለች:: በሴትነቴ ጉራንጉር፣ በሰውነቴ እንጦሮጦስ ውስጥ የትም አገኛታለው:: ብዳብሳት የትም የማላጣት ሴት ናት:: ከእማዬ... Read more »