ዘመን በአዲስ ዘመን

አዲስ ዘመን ጋዜጣ የዘመን መስታወት ነው:: ዛሬ 21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ሆኖ የ20ኛውን ክፍለ ዘመን ሁነቶች የሚናገር ነው:: የዓመታት ብቻ ሳይሆን የክፍለ ዘመንም መስታወት ነው:: ሰዎች ያልኖሩበትን ዕድሜ እንዲኖሩ ያደርጋል:: አዲስ ዘመን... Read more »

 ወደ ራሳችን እንመልከት!

ወሳኙና ትኩረታችንን ልንጥልበት የሚገባው ነገር የሌላው ሰው ጉዳይና ደካማ ጎን ሳይሆን የራሳችን ጉዳይ ላይ ነው። በየዕለት ከዕለት ኑሯችን ከዋናው ዓላማችን የሚያስወጡንን ተጽእኖዎች ስለማስወገድ ማሰብ እና መተግበር እንዳለብን ሁሉ ስለሌሎች ሰዎች ከማውራት ይልቅ... Read more »

 ጥናቶች ይጠኑ

በብዙ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ ‹‹ጥናቶች እንደሚጠቁሙት›› የሚል መረጃ መስማት የተለመደ ነው:: ጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ የሚጻፉ የግለሰብ አስተያየቶች ሀሳባቸውን ለማጠናከር ‹‹ጥናቶች እንደሚጠቁሙት›› ይላሉ:: ሀሳባቸውን ታማኝነት ያለው ለማድረግ ነው:: ‹‹ጥናቶች…›› ተብለው የሚጠቀሱት ደግሞ... Read more »

ሰኔ መጣ በጀት ይውጣ?!

 የመንግስት ተቋማት የበጀት አጠቃቀም ሁሌም ከወቀሳ ድኖ አያውቅም። ይህ ወቀሳ ግን በብዛት በጀታቸውን አላግባብ ከመጠቀም ወይም ከማባከን ጋር የተያያዘ ነው። ይህንን በተመለከተ የፌዴራል ኦዲት መስሪያ ቤት ከቅርብ አመታት ወዲህ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ... Read more »

የቤታቸው ኑሮ እንዴት ይሆን?

በዚሁ በትዝብት ዓምድ ደጋግሜ እንዳልኩት በሰለጠኑ አገሮች መኖርን የምመኘው በመሰረተ ልማቱ ወይም ባላቸው የረቀቀ ቴክኖሎጂ አይደለም፤ በሰዎች ጭንቅላት ነው። በሰዎች የሰከነ፣ የተረጋጋና የሰለጠነ አመለካከት ነው። ትልቁ ሥልጣኔያቸው ለህግና ደንብ ተገዢ መሆን ነው።... Read more »

ክፍያ የትምህርት ቤቶችና ወላጆች መፎካከሪያ

ሰሞኑን ከማህበራዊ ገጾች እና በአቅራቢያዬ ካሉ ወላጆች የግል ትምህርት ቤቶች ዋጋ ለመጨመር ከወላጆች ጋር እየተወያዩ እንደነበር አስተዋልኩ:: አንዳንዶቹም ‹‹ትምህርት ቤቱን ወደ ኮሌጅ ልናሳድግ ነውና….›› በማለት ወላጆች ዋጋ መጨመር እንዳለባቸው የሚናገሩ አሉ:: ይሄ... Read more »

አንድ ወደፊት – አሥር ወደ ኋላ

ነዋሪው ዓመታትን በጥያቄ የተጋበት ጉዳይ ዘንድሮ ዕልባት ማግኘቱ አስደስቶታል። አብዛኛው በወጣ በገባ ቁጥር ዓይኑን ከመንገዱ አይነቅልም። በየቀኑ የግንባታውን ለውጥ በአትኩሮት ይቃኛል። የታከለውን አዲስ ነገር እያስተዋለ ቀጣዩን በጎነት ይመኛል። ማልደው በስፍራው የሚደርሱ ሠራተኞች... Read more »

 ትምህርት ሸቀጥ ወይስ ማኅበራዊ ኃላፊነት?

የትምህርት ጉዳይ ከአንድ ማኅበረሰብ አልፎ ለአገር ያለውን ጥቅም ማብራራት ለቀባሪው የማርዳት ያህል ነው። የትምህርት ጉዳይ በተለይም በዚህ ዘመን የእያንዳንዱን ቤት የሚያንኳኳ እንደመሆኑ ማንም በቀላሉ የሚመለከተው አይደለም። በዚህ ዘመን ተፈጥሮ ፊደል አለመቁጠር ወይም... Read more »

 ዛሬ የሚለምኑ ሕጻናት ነገ ምን ይሆናሉ?

በምንም አይነት መንገድ ይሁን በአገራችን ሰላም መስፈን አለበት፤ አለበት ብቻ ሳይሆን በጣም የግድ ነው። አለበለዚያ የትውልድ ክፍተት ይፈጠራል። አሁን የምናየው ሁኔታ ከዚህ በላይ ከቀጠለ የማይተዋወቅ ትውልድ ይፈጠራል፤ ከአንድ ትውልድ በኋላ የሚኖረው ማህበረሰብ... Read more »

 አንዳንዴ በጉዟችን …

በቀኑ የሥራ ውሎ የተዳከመው ሠራተኛ ወደ ሰፈሩ የሚያደርሰውን ትራንስፖርት መጠበቅ ይዟል:: አብዛኛው የመንግሥት ሠራተኞችን አውቶቡስ የሚጠብቅ ነው:: የተቀረው የታክሲ ሰልፍ ይዞ ከወረፋው በተጠንቀቅ ቆሟል:: የሰሞኑ ዝናብ እንደልማዱ ‹‹መጣሁ›› እያለ ማስፈራራት ጀምሯል:: በስፍራው... Read more »