አርቲስት ደበበ እሸቱ «ቀያይ ቀምበጦች» ፊልም ላይ ባሳየው የሙያ ብቃት በቅርቡ በካናዳ ቫንኮቨር በተካሄደው «The Golden Leopard award» ሽልማት ሥነ-ስርዓት ላይ በምርጥ መሪ የትወና ዘርፍ አሸናፊ ሆኖ መሸለሙ በተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎች ተዘግቧል። የተወነበት ፊልሙም ጀርመንን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ አገራት ብሎም በሰሜን አሜሪካና አውስትራልያ ታይቷል። ይህንን ለአብነት አነሳን እንጂ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በሙያው ባበረከተው አስተዋፅኦ በርካታ ሽልማቶቹን ማግኘቱ ይታወቃል። ለመሆኑ አርቲስቱ ከአገሩ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና ማግኘት የቻለበት ሚስጥር ምንድን ነው? አሁን ያሉት አርቲስቶች ላይ በዚህ ረገድ የሚታየው ክፍተት ምንድን ነው? ለዚህና ለሌሎችም ጥያቄዎች ምላሽ አለው። እንደሚከተለው እናቀርበዋለን
አዲስ ዘመን፡- በምን አጋጣሚ ነበር የኪነጥበብ ዓለምን የተቀላቀልከው? አርቲስት ደበበ፡- እኔ ወደ ቴአትር በገባሁበት ጊዜ የቴአትር ሙያ በህብረተሰቡ ዘንድ ይህን ያህል ተቀባይነት አልነበረውም። ያው አዝማሪ ከሚባለው ቡድን ጋር ተደምሮ ይታይ የነበረበት ዘመን ነበር። እኔ ወደ ኪነጥበብ የገባሁት ፈልጌና ወድጄው ነው። ለምን ወደድከው? ያልሽኝ እንደሆነ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት በምማርበት ጊዜ ካናዳውያን አስተማሪዎቼ በትርፍ ሰዓታችን ቴአትር፣ ሙዚቃና ስነ ጽሁፍ ያስተምሩን ነበር። ቴአትር ለመስራት ግን ሁለተኛ ደረጃ መግባት ይጠበቅብን ነበር። ወጋየሁና እኔ ግን እድሉን አግኝተን ትልልቆቹ ሲሰሩ የመድረክ መጋረጃ እንይዝ ነበር። እዛ የሚሰሩትን እያየሁ እቤቴ እየመጣሁ ለእናቴና ቡና ለሚጠጡ ጓደኞቿ ቴአትር እንስራላችሁ እያልን ከወጋየሁ ጋር እንሞካክር ነበር።
እንግዲህ ከዚያ ከዚያ የጀመረ የቴአትር ፍቅር እያደገ መጣና ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል ውስጥ የሮክ ፌለር ፋውንዴሽን ባለሙያዎች ልኮ ማሰልጠን ሲጀምር እዛ ውስጥ እኔም ከሌሎቹ ጋር ተወዳደሬ ገባሁ። ሁለት ዓመት ከሰለጠንን በኋላ ሳንመረቅ ባጀት አለቀ ብሎ ፋውንዴሽኑ ተዘጋ። እኛም መድረሻ አጣንና ያንጊዜ የነበሩትን ፕሬዚዳንት ገብተን ብናነጋግራቸውም ምንም ሊያደርጉልን አልቻሉም። ከዚያ በኋላ ደግሞ የሃንጋሪ መንግሥት በሰጠን የትምህርት እድል ለመማር ወደ ሃንጋሪ ሄድን። ተምረን ስንመጣ ግን የኢትዮÉያ ቴአትርን እናዝበታለን ብለን ተኩራርተን ነበር። ይሁንና ስንመጣ እነ ጌታቸው ደባልቄ፣ እነ አስናቀች ወርቁ፣ እነ ተስፋዬ ሳህሉ፣ እነ ጀንበሬ በላይ ባሉበት መድረክ ላይ እኛ ወጥተን ቴአትር ቤቱን እንደማናዘው ተረዳን።
አዲስ ዘመን፡- ከአንጋፋዎቹ አርቲስቶች ጋር የመስራት እድሉን እንዴት አገኘኸው? አርቲስት ደበበ፡- በአንድ አጋጣሚ ላይ ጋሽ ጸጋዬ የሼክስፒርን የበግ አሊሊትራይ የተባለው ቴአትር ሲዘጋጅ ወጋየሁና እኔን ተጋባዥ ተዋናይ አድርጎ ወሰደን። እዚያ ስንደርስ ግን ከጠበቅነው በላይ በቀደሙት ተዋናያን አቅምና ጉልበት ተደናገጠን እንደ ትርዒት ነበር የምናያቸው። የአቅማቸው መጠን መድረክ ላይ ሲጨምር ስንመለከት በጣም ተገረምን። ልክ እረፍት ተብሎ ስንወጣ እኔና ወጋየሁ ምን ይሻላል ተባባል። በቃ አሁን ገና ትምህርት ቤት አገኘን ብለን መማር እንዳለብን ወሰንን። እነሱ ግን መጀመሪያ ላይ እነዚህ ፈረንጅ አገር ተምረው የመጡ ብለው አግለለውን ነበር። በኋላ ግን የእኛን ሁኔታ ሲያዩ አቀረቡን።
ከዚያ ጋሽ ፀጋዬ አንድ ቀን ልምምድ ላይ እያለን ምሳ ጋበዘንና «እንዴት ነው?» ብሎ ጠየቀን። እኛም «ጥሩ ነው» አልነው። እሱ ግን ስላላመነን «ልካችሁንስ አወቃችሁ?» ብሎ ጠየቀን። «አዎ አሁን ልካችንን አውቀናል» አልነው። ልካችሁ የትነው ሲለን እነሱ እግር ስር መሆኑንና ትምህርት ቤት አሁን ገና መግባታችንን እንደተረዳን ስንነግረው በጣም ደስ አለው። «በሉ በርቱና ተማሩ» ብሎ መከረን። አሁን አሁን ግን ከቀደሙት የመማር ልምድ በወጣቶቹ ዘንድ አላይም። ካለፈው መማር አስፈላጊ መሆኑን ወጣቱ ትውልድ መገንዘብ ይኖርበታል። እኔ በበኩሌ ያለኝን ተሞክሮ ያለኝን እውቀት ያሳለፍኩትን ሁኔታ ከወጣቶቹ ጋር አሁንም እየሰራሁ ነው።
ዩኒቨርስቲም ተጠርቼ የማስተምርበት ጊዜ አለ። አንዳንድ ጊዜ ከእነሱ ጋር ሙሉ ቀን የማጠፋበት ጊዜ አለ። እናም በዚህ ደስተኛ ነኝ። ምክንያቱም የእነ ጋሽ አውላቸው ደጀኔ እዳ አለብኝ። ለእኔ የእነሱን እዳ መክፈል ማለት የህሊና ነፃነት ማግኘት ማለት ነው ። ከዚህም ባሻገር ባለሙያ መፍጠር ማለት በመሆኑ ይህንን ሳደርግ በሙሉ ፈቃደኝነት ነው። አንዳንዶች እስክሪፕት ያመጡልኛልአርሜ እሰጣቸዋለሁ። አብዛኞቹ እርማቴን ይቀበላሉ፤ አንዳንዶቹ ግን ቶሎ ገንዘብ ለማግኘት ይቸኩላሉ። ይህም ያሳዝነኛል። አሁንም ቢሆን ግን ከእኔ ጋር አብረው ለመስራት ለሚፈልጉ ወጣቶች በጣም ፈቃደኛ ነኝ።
አዲስ ዘመን፡- በእናንተ ዘመን ለሙያው የነበረው ፍቅርና ስነምግባር አሁን አለ ብለህ ታምናለህ? አርቲስት ደበበ፡- የሙያ ስነምግባር ችግር አለ። በኪነጥበብ ሰዎች ላይ የሚስተዋለው የሙያ ችግር ከኑሮ ችግር ጋር ዝምድና አለው። አሁን ያለው ወጣቱ ለቤት ኪራይ ሁለትና ሶስት ሺህ ብር ይጠየቃል። ምግብና ሌሎችም ወጪዎች አሉበት። ትዳር መያዝና ቤተሰብ መገንባት ይፈልጋል። በቴአትር ቤት የሚከፈላቸው ገንዘብ ያንን ወጪያቸውን አይሸፍንላቸውም። ስለዚህ ሌሎች አማራጮችን ይፈልጋሉ። በተለይ ወደ ፊልሙ ለማዘንበል ይገደዳሉ። መንግሥት አሁንም ትኩረት አድርጎ ቴአትር ቤት ያሉ ሰዎችን ነፃ አድርጎ መደገፍ መቻል አለበት። በሌላ በኩል ግን የትም የማይገኝ አንድ እድል እዚህ አገር መኖሩ አይካድም። ያም ምንድነው አርቲስቶች በቋሚነት የሚቀጠሩበት አገር ኢትዮጵያ ብቻ መሆኑ ነው።
ምንአልባት በችሎታቸው የሚታመኑ በጣት ከሚቆጠሩ ሰዎች ውጪ በአፍሪካም ሆነ በአሜሪካ ተቀጥሮ የሚሰራ የኪነጥበብ ባለሙያ አታገኝም። በሌሎች አገሮች ቴአትር ቤት ለመቀጠር ብዙ ውጣ ውረዶችን ማለፍ ይጠበቅባቸዋል። እኛ አገር ብሄራዊ ቴአትር ቤት ለመቀጠር ምንም መመዘኛ የለም። ሄደሽ ማመልከት ብቻ ነው የሚጠበቅብሽ። ከቀናሽና ያመለከትሽበት ቦታ ክፍት ከሆነ መግባት ትችያለሽ። የሙያ ጥራትና ደረጃ መመዘኛ ስርዓት የለም። ስለዚህ አሁን ያለው ነገር መስተካከል አለበት የሚል እምነት አለኝ። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ባለሙያዎችን ዝም ብለን መውቀስ አይገባንም። በእርግጥ ባለሙያዎች ቢሆኑ ታሪክ ያጡ ይመስል ተመሳሳይ የሆነ ታሪክ ያለው ፊልም በመስራት ተመልካቹን በማሰልቸታቸው ሊወቀሱ ይገባል። ኢትዮጵያ እኮ የባህል ሀብታም ነች። የትውፊትአገር ነች። ይሄ ባለሙያ ይህንን ቱባ ታሪክና ባህል በፊልምና በቴአትር መልክ እንዲሰራው ከተፈለገ ግን የክፍያውን ነገር ማስተካከል ያስፈልጋል። ምክንያቱም አሁን እየተከፈለው ያለው ከወጪው ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ።
አዲስ ዘመን፡- መንግሥት ለሌሎች ዘርፎች የኢንቨስት መንት ማበረታቻ እንደሚሰጠው ሁሉ ለኪነጥበብ ዘርፉ አለመሰጠቱ ኪነጥበቡ ላለማደጉ ምክንያት እንደሆነ ይነሳል። አንተ በዚህ ሃሳብ ትስ ማማለህ?
አርቲስት ደበበ፡- በትክክል፤ እኔ ለኪነጥበብ ዘርፉ ኢንቨስትመንት ማበረታቻ ያለመሰጠቱ ጉዳይ የጥበቡን ኃይልና ጥቅም ካለማወቅ የመነጨ ይመስለኛል። አሁንም እኮ ስራ እየተሰራ ያለው በጥበብ ባለሙያዎች ነው። አሁንም እኮ ስለ ሰላም ኑ እና ዘምሩልን እየተባሉ እየተለመኑ ነው። ስለ ሰላም ቴአትር ፃፉልን እየተባሉ ነው። ይሁንና ዘርፉን ለመደገፍ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እንኳን የለም። በዚህም ምክንያት ምንም ድጋፍ አይደረግለትም። እኔ አሁን ቴአትር ቤት ልስራ ብዬ ብነሳ ቦታ አላገኝም። መሳሪያዎች ከቀረጥ ነፃ እንዳስገባ አይፈቀድልኝም። ይሄ መለወጥ አለበት ብዬ አምናለሁ። መንግሥት ትኩረት አልሰጠውም የሚባለው ለዚህ ነው እኮ።
አዲስ ዘመን፡- ወደ አንተ ጉዳይ ስንመለስ ቴአትር የመፃፍ ትዕግስት እንደሌለህ ከዚህ ቀደም አጫውተኸኝ ነበር።ይሁንና አንድ «የእምነቴ ፈተና» የምትል መጽሐፍ ፅፍህ አሳትመሃል። መጽሐፍን ያህል ነገር ለመፃፍ ታዲያ ፅናቱን ከወዴት አመጣኸው?
አርቲስት ደበበ፡- የለም፤ ቴአትር አልፎ አልፎ እሞክራለሁ ግን ከአንድ ገቢር አላልፍም። እንዳልኩሽ ግን ሙሉ ተውኔት ጽፌ አላውቅም። መጽሐፉን ስፅፍ ግን የነበረውን እውነታ ነው ዝም ብዬ ያስቀመጥኩት። ከጨረስኩት በኋላ እንዲያርምልኝ ለአንዳርጋቸው ፅጌ ላኩለት። እሱ ከአነበበው በኋላ ግን እውነታውን በቀጥታስላስቀመጥከው ምንም አትንካው ብሎ አስተያየት ሰጠኝና ምንም ሳይነካ አሜሪካን አገር ታተመ። ከፍተኛ ተቀባይነት አገኘ። እዚህም ለሁለተኛ ጊዜ ታተመ። አሁንም የሚጠይቁኝ ሰዎች አሉ። እኔ ግን መፃፍ የምፈልገው አዲስ ነገር ነው። አሁን መጨረሻ ላይ ደግሞ «የባሩድ በርሜል» የምትል መጽሐፍ ተርጉሚያለሁ። እሱም በጣም ታዋቂ ሆኗል። አንዳንድ ሰዎች በኦሮምኛና በትግርኛ ይተርጎም የሚል ሃሳብ እየሰጡ ነው። አሳታሚውም እያሰበበት ይመስለኛል።
አዲስ ዘመን፡- ከአገር አልፈህ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና ካገኙ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለህ።ምን የተለየ ተሰጥኦ ስላለኝ ነው ለዚህ የበቃሁት ትላለህ?
አርቲስት ደበበ፡- እኔ አለም አቀፍ ፊልም ላይ ለመሳተፍ የረዳኝ ዋነኛው ጉዳይ ቋንቋ መቻሌ ነው ብዬ ነው የማምነው። ለሁሉም ሰዎች የምላቸው ነገር ወደ ዓለም አቀፍ እውቅና ለመግባት ከፈለጋችሁ የቋንቋ ችሎታ ለሙያው በጣም አስፈላጊ መሆኑን ነው። ለእኔ መጀመሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በር የከፈተልኝ የቋንቋ ችሎታዬ ነው። ከቋንቋ ችሎታዬ በተጓዳኝ ደግሞ አዘጋጆቹ ያዩበት ምልከታ ይኖራቸዋል። ፎቶ ጀኒክ ነህ ይሉኛል። በተጨማሪም ጥረት ማድረግና አካሄዱን ማወቅ ያስፈልጋል። ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች ቢጠይቁኝ መንገዱን ላሳያቸው ሙሉ ፈቃደኛ ነኝ።
ደግሞም እኮ እኛ አገር ወኪል የሚባል ነገር የለንም። እኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወኪል አለኝ። እሱ ነው ስራ የሚፈልግልኝ። ደግሞ አንድ ጊዜ ዓለም አቀፍ መስመር ውስጥ ከገባሽ በዛው ነው የምትቀጥይው። በእርግጥ መታሰሬ ብዙ ስራዎችን አደናቅፎብኛል። ግን እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ ከእስር እንደወጣሁ ለአንድ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ፊልም ሰርቻለሁ። የምርጥ መሪ ተዋናይነት ሽልማት እንዳገኝ አድርጎኛል። ስለዚህ ሌሎች የኪነጥበብ ሰዎችን የምመክረው እውቅና ማግኘት የራስንም ጥረት እንደሚጠይቅ ነው። ይሁንና ዝም ብሎ ተቀምጦ አማርኛ ቴአትር ብቻ በመስራት ዓለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት አስቸጋሪ ነው።
አዲስ ዘመን፡- እስከአሁን ምንያህል ፊልሞች ላይ ተሳትፈሃል? ያገኛቸውስ ዓለም አቀፍ ሽልማቶች አስገኝቶልሃል?
አርቲስት ደበበ፡- በ12 ፊልሞች ላይ ተሳትፊያለሁ። ያገኘኋቸው ሽልማቶች አንድ ጊዜ አትላንታ ላይ November 24 በየዓመቱ የደበበ እሸቱ ቀን እንዲከበር ምክር ቤቱ ባፀደቀው መሰረት ለአፍሪካና ለዓለም ቴአትር ባደረገው አስተዋፅኦ ተብሎ የተሰጠኝ ነው። ሌላው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ካውንዳና የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ኔሬሬ ሸልመውኛል። በአገር ውስጥ ደግሞ ጉማ፣ እዮሃ፣ ኢትዮ ኢንተርናሽናል ፊልም የተባሉ ድርጅቶች ያበረከቱልኝ ሽልማቶች ተጠቃሽ ናቸው። በቅርቡም ደግሞ የሰራሁት «ቀያይ ቀንበጦች» የሚል ፊልም ውድድር ውስጥ ገብቶ ምርጥ መሪ ተዋናይ የሚል ወርቃማ ፕላቲኒየም ሸልሞኛል።
አዲስ ዘመን፡- የአፍሪካ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ማህበራት መሪም ሆነህ ታውቃለህ ይህ የሆነበት አጋጣሚ ምን ነበር?
አርቲስት ደበበ፡- የአፍሪካ የመድረክ ባለሙያዎች ማህበር 1983 ዓ.ም ዙምቧቡዌ በተደረገ የዩኒስኮ ስብሰባ ላይ ነበር የተመሰረተው። እዛ በተደረገው ስብሰባ ላይ እኔ የሄድኩት ለመሳተፍ ብቻ ነበር። እዛ ስብሰባ ላይ እያለሁ የአፍሪካ ተጠሪ ተብዬ ተመረጥኩ ሌላ ምንም ምክንያት ስለነበረ ሳይሆን በስብሰባው ላይ የነበርኩት እኔ ብቻ ስለሆንኩ እና ዩኒስኮ ከአፍሪካ የግድ ሰው መወከል ስለነበረት ነው። ወዲያውም ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ መድረክ የመምራት ልምዱ ባይኖረኝም በዚያው ተጠሪነቴ ዝምቧቡዌ ውስጥ ወርክሾፕ ሲካሄድ ለመምራት ሄድኩ።
ከዚያ በፊት ግን አልጄሪያና ናይጄሪያ በተካሄዱት የጥቁር አፍሪካውያን ፌስቲቫል ላይ እዛ የአፍሪካ ባለሙያዎች ማህበር ለማቋቋም ተሞክሮ አልተሳካም። ሃሳቡ የነበረን ሰዎች ዝምቧቡዌ ላይ ስንገናኝ ይህ ሀሳብ ተነስቶ ፕሮግራሙን ስናካሄድ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ገጠመን። ምክንያቱም ፕሮግራሙን የሚመሩት ሰዎች ከእንግሊዝ፣ ከጀርመን፣ ከፈረንሳይ የመጡ ሰዎች ናቸው። ትምህርቱን ግን የምንሰጠው እኛ ነን። ይህ መሆን እንደማይገባ ተነጋግረን በዚህ ምክንያት ማህበሩ እንዲቋቋም ተወሰነ። እኔም አስመራጭ ኮሚቴ ነበርኩ። 19 አገሮች ወኪሎቻቸውን እንዲያመጡ ሲደረግ ከዝምቧቡዌ የመጡት ነጮች ነበሩ። እኔየአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ስለነበርኩ እናንተ ነጮች ከየት የመጣችሁ አፍሪካውያን ናችሁ ብዬ ጠየኳቸው። ከዝምቧቡዌ መሆኑን ሲነግሩኝ ዝመቧቡዌ ነጭ ዜጋ የላትም የእናንተን ውክልና አልቀበልም አዳራሹን ለቃችሁ ውጡልን አልኳቸው። እኛ ፕሬዚዳንት እንዲሆን የፈለግነው ሰው ሌላ ጥቁር የሆነ ዝምቧቡዌያዊ ነጮቹ ሲወጡ እሱም አብሮ ወጣ።
ይህንን ሰው ብዙ ለምነነው እንደገና አስገባነው ግን ያቺ ጉዳይ ጥቁር ነጥብ ሆና ምርጫውን ሳያሸንፍ ቀረ። እንደገና ሌላ አስመራጭ ኮሚቴ ተዋቅሮ እኔ የማህበሩ ፕሬዚዳንት ሆኜ ተመረጥኩ። የተመረጥኩበት ዋነኛ ምክንያት ነጮቹን ውጡ ስላልኩና በራስ መተማመኔን አይተው ይመስለኛል። ለዚያ ማህበር ለ12 ዓመታት አገልግያለሁ፤ አሁንም ይህ ረድፍ የአንድ አካባቢ ወይም ቦታ ለምን እንደተባለ የሚገለጽበት ንዑስ ዓምድ ነው። በአገራችን ውስጥ የሚገኙ ቦታዎችን እናስተዋውቃለን። እነዚህ ቦታዎች ለምን እንደተባሉ ከታሪክ ሰነድ አጣቅሰን ምላሽ እንሰጣለን። ለምን ተባለ ዛሬ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን አቅጣጫ ወጣ እንበል። እንጦጦን፣ ሱሉልታን እንዳለፍን ጫንጮን እናገኛለን። ጫንጮ ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ? ላይ ትገኛለች።
ጫንጮ ለምን ተባለች? ‹‹ጫንጮ›› ማለት ጨው ጨው የሚል ማለት ነው፤ በሌላ በኩል ጨዋማ ውሃ ማለትም ነው። ከዚህ በመነሳት ከተማዋ ጫንጮ ተብላለች። ደብረ ሊባኖስ አሁን ደግሞ ከጫንጮ አለፍ ብለን ከአዲስ አበባ 104 ኪሎ ሜትር ርቀት እንሂድ። የደብረ ሊባኖስ ገዳምን እናገኛለን። ደብረ ሊባኖስ ለምን ተባለ? አባ ሊባኖስ የተባሉ የግብጽ ጳጳስ ነበሩ። ጳጳሱ በዚህ ቦታ ላይ ስለተቀበሩ ቦታው በእርሳቸው ስም ተሰይሞ ‹‹ደብረ ሊባኖስ ገዳም›› ተባለ። ገርበ ጉራቻ አሁንም በዚሁ መስመር ከአዲስ አበባ 154 ኪሎ ሜትር እንራቅ። ገርበ ጉራቻን እናገኛለን። ብዙ ጊዜ ገብረ ጉራቻ እየተባለ ይጠራል፤ ትክክለኛ መጠሪያው ገርበ ጉራቻ ነው። ገርበ ጉራቻ ለምን ተባለ? ‹‹ገርበ›› ማለት የኦሮምኛ ቃል ሲሆን ባህር ማለት ነው፤ ‹‹ጉራቻ›› የኦሮምኛ ቃል ሲሆን ጥቁር ማለት ነው። ገርበ ጉራቻ ማለት ጥቁር ባህር ማለት ነው። በአካባቢው ጥቁር ባህር እንደነበር ይነገራል። «የፆም ምግብ» መስራች ፕሬዚዳንት እያሉ ይጋብዙኛል።
አዲስ ዘመን፡-እስቲ ትንሽ አንተ በመሪ ተዋናይነት ስለሰራህበት ቀያይ ቀንበጦች ፊልም አውጋን?
አርቲስት ደበበ፦ ቀያይ ቀንበጦችን አዘጋጆቹ ለሁለተኛ ጊዜ ከመታሰሬ በፊት ነው ሲፈልጉኝ የነበረው። ለረጅም ጊዜ ፈልገው ሊያገኙኝ አልቻሉም ነበር። መጨረሻ ላይ ቺጋጎ በሚባል የአሜሪካ ግዛት ውስጥ ይኖር ለነበረ ግለሰብ ስለእኔ ይነግሩትና ለሚያውቃቸው ሰዎች ነግሮ በፌስቡክ ያፈላልጉኝ ያዙ። በኋላ ፀደይ ደበበ እሸቱ የሚባል ስም ያገኙና አንቺ የደበበ እሸቱ ልጅ ነሽ ወይ ይሏታል። እሷም ብሆንስ ምንችግር አለው ትላቸዋለች። ለስራ ፈልገውኝ እንደሆነ ይነግሯትና በእሷ በኩል ነው የተገናኘነው። በዚያ መሰረት የፊልሙን ስክሪፕት ላኩልኝና ሳነበው ወደድኩት። ታሪኩ የሚያጠነጥነው ከተለያዩ አገራት የተመለሱ የፈላሻ ወይም የእስራኤል ዘር ያለባቸውን ሰዎች ችግር የሚያነሳ ነው። ስለዚህ ዓለም አቀፋዊ ይዘት አለው።
ከዚያ በኋላ ደግሞ እስቲ ስክሪን ቴስት እናድርግ አሉና ካሜራማኑ መጥቶ አንስቶ ሄደ ግን ለረጅም ጊዜ ተጠፋፋን። እኔም ለስራ ካናዳ ሄጄ እያለው አንድ ቀን ስልክ ተደወለልኝና እንግሊዝ አገር መጥተህ ኮንትራንት እንፈራረም አሉኝ። እኔ ግን መፈራረም ያለብን እስራኤል ወይም ኢትዮጵያ መሆን አለበት አልኳቸው። ምክንያቱም ውሉ ቢፈርስ እንኳ ልዳኝበት በምችልበት አገር መሆን ስለሚገባው ነው። ከዚያም እስራኤል እንዲሆን ተስማምተን ወደዚያው ሄድኩ። እዛ ስደርስ ግን ዳይሬክተሩ ነጭ መሆኑን ሳውቅ አሻፈረኝ አልኩ። ምክንያቱም ደግሞ ባህሉንም ሆነ ቋንቋችንን የማያውቅ በመሆኑ ነው። በኋላ እኔ ባመጠሁት ሃሳብ መሰረት የፊልሙን ታሪክ የፃፈውን የኢትዮጵያ ፈላሻ እንዲሆን ተስማማንና በዚያው ቀጠለ።
ፊልሙን ከመስራቴ በፊትም አንድ ወር ያህል ከፈላሻዎቹ ጋር ኖሬ አኗኗቸውን ባህላቸውን አጠናሁ። ፊልሙን ለመቅረፅም ስድስት ወር ፈጅቶብን ነበር። ፊልሙ በመከፈቻው ላይም ተሸለመ። እኔም ቤስት ክሪቲክ አዋርድ የተባለ ሽልማት ተሰጠኝ። ከዚያ በኋላ ፊልሙ ካናዳ ላይ ባንኮበር ውስጥ ዓለምአቀፍ ውድድር ውስጥ ገብቶ ቤስት ሊዲንግ አዋርድ ተሻለሚ ሆኛለሁ። በዚህም ፈጣሪን ማመስገን እፈልጋለሁ። አዲስ ዘመን፡- በጣም የምትታወቅበት ሌላው ጉዳይ ደግሞ ለሌሎች አርአያ መሆን በሚችለው የትዳር ህይወትህ ነው። ለመሆኑ ሚስጥሩ ምንድን ነው? አርቲስት ደበበ፡- እውነት ነው፤ እኔ በትዳሬ በጣም ደስተኛ ነኝ። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ሚስጥር ብዬ የማምነው ተግባብተን በመጋባታችን ነው። እኔና ባለቤቴ ከመጋባታችን በፊት ወደ ሰባት ዓመት በፍቅረኝነት አሳልፈናል። ከተጋባንበት እለት ጀምሮ ችግር ሲመጣ እንነጋገራለን። እና ያን ችግር ስንፈታና በሚቀጥለው ጊዜ ስንገናኝ ይሄ ችግር መልሶ አይነሳም፤ እንደሞተ ነው የምንቆጥረው። በመጀመሪያ ጊዜ በደርግ ስታሰር የመጀመሪያ ገፈት ቀማሽ የሆነችውና መከራ የጣልኩባት እሷ ላይ ነው። ከዛም በኋላ ባጋጠሙን ችግሮች ሁሉ ግንባር ቀደም ሆና አይዞህ የምትለኝ እሷ ናት። ለነገሩ ባለቤቴ በአስተሳሰብ የበሰለች በመሆኑ በጣም ትረዳኛለች። እናም የሁለታችን መግባባትና መተሳሰብ ነው እዚህ ያደረሰን ብዬ አምናለሁ። ተግባብቶ መግባባት ማለት ዘላለማዊ መተሳሰብ መሆኑን አምነንበትም ነው የተጋባነው። መጥፎዬን አውቃ፣ ደካማ ጎኔን ተረድታ እኔም እንደዚሁ። ከተጋባን አሁን እንግዲህ 45 ዓመት ሆኗል። በዚህም አራት ልጆችን ያፈራን ሲሆን ሰሞኑን የተወለደችው ልጅ ስምንተኛ የልጅ ልጃችን ነች። አሁን ወደ 75ኛ ዓመቴ እየገሰገስኩ ቢሆንም ሚስቴን እንደገና ባገባት ደስ ይለኛል።
አዲስ ዘመን፡- ሰፊ ጊዜ ሰጥተህ ሃሳብህን ስላጋራኸን በዝግጅት ክፍሉና በአንባቢዎቼ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።
አርቲስት ደበበ፡- እኔም አመሰግናለሁ።
አዲስ ዘመን መጋቢት 28/2011 ማህሌት አብዱል