«ከመጋቢት እስከ መጋቢት» የፎቶ ዐውደ ርዕይ ዛሬ ይከፈታል
«ከመጋቢት እስከ መጋቢት» የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን የአንድ ዓመት ቆይታ የሚያሳየው የፎቶ ዐውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት ይከፈታል። በዓውደ ርዕዩ ጠቅላይ ሚንስትሩ በዲፕ ሎማሲ፣ በማህበራዊ፣ በፖለ ቲካዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያከና ወኗቸው አበይት ተግባራት በፎቶ የሚታዩ ይሆናል።
የፎቶ አውደ ርዕዩ በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄደ ሲሆን፤ ለአራት ተከታታይ ቀናት ለጎብኝዎች ክፍት ይሆናል። የፎቶ አውደ ርዕዩ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተዘጋጀ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
‹‹ኢትዮጵያዊው ሱራፊ» መጽሐፍ የማጠቃለያ ምርቃት ነገ ይካሄዳል
በሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት የተዘ ጋጀው፤ ከአስር ዓመታት በላይ የተደከመበትና በቅርቡ ለንባብ የበቃው «ኢትዮጵያዊው ሱራፊ» የተሰኘው በፃድቁ አቡነ ተክለሐይማኖት ታሪክ ላይ የሚያተኩረው ታላቅ መጽሐፍ የማጠቃለያ የምርቃት ሥነ ሥርዓት ነገ መጋቢት 23 ቀን 2011ዓ.ም ማምሻውን በብሔራዊ ቴአትር ይከናወናል።
በዕለቱ ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ፣ ዶክተር ዳዊት ወንድምአገኝ፣ ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፣ ቀሲስ ዶክተር መዝገቡ፣ መምህር ግርማ ባቱ፣ መምህር ቀለመወርቅ ሚደቅሳ፣ ቀሲስ ዘማሪ ምንዳዬ ይገኛሉ፤ የሲሳይ በገና ትምህርት ቤት የበገና ድርደራ ይቀርባል ተብሏል።
«ማምሻ» ጥበባዊ የምሽት ክዋኔ ልደቱን ያከብራል
ከአንድ ዓመት በፊት የተጀመረው «ማ ምሻ»ባለዐይነት የመድረክ ትዕ ይንት ማክሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2011ዓ.ም ማምሻውን ከ11፡ 00 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር አንደኛ ዓመቱን ያከብራል። «ነገረ ማምሻ» ባሉት በዚህ መድ ረክ ግጥሞች ይቀርባሉ፤ ሙዚቃና የተለያዩ ጨዋታዎችም ይኖራሉ። «ማምሻ» በየወሩ የመጨረሻ ማክሰኞ ቀን የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት በሥነ ግጥም፣ በወግና በትወና መሰል ጥበባዊ ክዋኔዎችን ለታዳሚ ሲያቀርበ መቆየቱ ይታወሳል።
ጎህ የኪነጥበብ ዝግጅት የፊታችን ረቡዕ ይካሄዳል
ለሦስተኛ ጊዜ የሚደረገው ወርሐዊው ጎህ የኪነ ጥበብ ዝግጅት የፊታችን ረቡዕ መጋቢት 25 ቀን ከቀኑ በ11 ሰዓት 30ይካሄዳል።
ዝግጅቱ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል የሚከናወን ሲሆን፤ በእለቱ ገጣሚ ምንተስኖት ማሞ፣ ህሊና ደሳለኝ፣ መልዕቲ ኪሮስ፣ መስፍን ወለተሰናይ እን ዲሁም ሌሎችም ይገኛሉ ተብሏል። የአንድ ሰው ተውኔት በተስፋሁን ከበደ ፣ ወግ በእንዳልካቸው ዘነበ እና በፍቅር ይልቃል እንደሚቀርብም ሰምተናል። በተጨማሪ ሙዚቃ መሳይ ተፈራ ካሳ ከመሶብ ባህላዊ ባንድ ጋር እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡ የኪነጥበቡ ምሽት አዘጋጆች ሄኖክ የእታገኝ ልጅ እና ተወዳጁ ገጣሚ በላይ በቀለወያ ናቸው፡፡
16ኛው ሰምና ወርቅ የኪነጥበብ ምሽት ሐሙስ ይካሄዳል
በየወሩ ማብቂያ ዕለተ ሐሙስ የሚካሄደው ሰምና ወርቅ የኪነጥበብ ምሽት መጋቢት 26 ቀን 2011ዓ.ም ማምሻውን ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ በቫምዳስ መዝናኛ ማዕከል ይካሄዳል።
በዚህ መርሐ ግብር ዶክተር አሉላ ፓንክ ረስት፣ ዶክተር አዲል አብደላ፣ ዶክተር ሙላቱ በላይነህ፣ ኮኔል ደራርቱ ቱሉ፣ አርቲስት ኃይሉ ፀጋዬ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ፍሬው፣ ኤፍሬኽ ለማ፣ መምህርት እፀገነት ከበደ፣ መምህር ኤልያስ መዳ እንዲሁም ገጣሚ ቴዎድሮስ ነጋሽ የገኛሉ፤ የተለያዩ ሃሳቦችንና ኪነጥበባዊ ሥራዎቻቸውን ያጋራሉ ተብሏል።
በቀጣይ ሳምንት የሚካሄዱ የመጻሕፍት ምርቃት መርሐ ግብራት
«ባዶ ሰው በባዶ ቤት» የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነገ ይመረቃል በአንዱ ጌታቸው የተዘጋጀና «ባዶ ሰው በባዶ ቤት» የተሰኘ የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ነገ መጋቢት 23 ቀን 2011ዓ.ም ማመሻውን ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ በቫምዳስ የመዝናኛ ማዕከል ሲኒማ አዳራሽ ይመረቃል።
አርቲስት ሻንበል ለማ ጉያ የህይወት ታሪክ መጽሐፍ ተመረቀ
በስዕል ሥራቸው የሚታወቁት አርቲስት ሻን በል ለማ ጉያ የህይወት ታሪካቸውን በመጻፍ ትልልቅ የአርትኦት ሥራ በሠሩ ምሁራን አሳርመው ለንባብ ይበቃ ዘንድ ከትናት በስተያ በስካይ ላይን ሆቴል አስመርቀዋል።
284 ገጾችን የያዘው ይህ መጽሐፍ ዘጠኝ ምዕራፎችን የያዘ ሲሆን፤ የባለታሪኩን ሽልማ ቶችና ትልልቅ ሥራዎችንም ያካተተ ነው። በ200 ብር ዋጋም ለገበያ ቀርቧል። በምረቃው ወቅትም የተለያዩ የውጭ አንባሳደሮች ተገኝተው ስለእርሳቸው ምስክርነቶችንም ሰጥተውበታል።
የንባብ ሳምንት በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ከጅማ ዮኒቨርሲቲ እና ጅማ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የንባብ ሳምንት በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው። «ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል» በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው በዚህ የንባብ ሳምንት፤ የመጻሕፍት ሽያጭና አውደ ርዕይ እንዲሁም የሥነጽሑፍ ምሽቶች ይከናወናሉ። በተጨማሪም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በሚቀርቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ላይ የውይይት መርሐ ግብራት ይኖራሉ። ትናንት መጋቢት 21 ቀን 2011ዓ.ም የተጀመረው ይህ የንባብ ሳምንት እስከ መጋቢት 25 ቀን 2011ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 22/2011