አዲስ አበባ፡- የአሉቶ ላንጋኖ የጂኦተርማል ኃይል ማመንጫን አቅም በአሥር እጥፍ ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የሚገኘው የአሉቶ ላንጋኖ የእንፋሎት ኃይል ከ7 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት ሀይል ሲያመነጭ የነበረ ሲሆን፣ይህን አቅሙን ወደ 70 ሜጋ ዋት ለማድረስ እየተሰራ ነው።
የሀይል ማመንጨት አቅሙን ለማሳደጉ ስራም 192 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አቶ ሞገስ ጠቁመው፣ ለፕሮጀክቱ ከተመደበው ከዚህ ገንዘብ 183 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላሩ ከዓለም ባንክ በብድርና እርዳታ መገኘቱን ገልጸዋል። የአይስላንድ መንግሥት ለፕሮጀክቱ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ርዳታ ማድረጉን ተናግረው፣ የኢትዮጵያ መንግሥትም 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን
ዶላር መመደቡን አስረድተዋል ።በአሁኑ ወቅትም የማስፋፊያ ሥራው እየተካሄዱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
እንደ አቶ ሞገስ ገለጻ፤ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ለመካከለኛው የኢትዮጵያ አካባቢ አስተማማኝ የኃይል ምንጭ እንደሚሆን ይጠበቃል ።ሀገራችን ታላቁ የምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ የሚያልፍባት መሆንዋ በዚህ ሀይል ተጠቃሚ እንድትሆን ያስችላታል።
የእንፋሎት ኃይሉን የማመንጨት ስራ ከ2ሺ እስከ 2 ሺ500 ሜትር ወደ ታች በመቆፈር የሚካሄድ ሲሆን፣ ለዚህም ወደ 22 ጉድጓዶች ይቆፈራሉ። ለቁፋሮው እና ዕቃዎች አቅርቦት አንድ የኬንያና ሁለት የቻይና ኩባንያዎች ስምምነት ፈረመዋል።
ከሚቆፈሩት 22 ጉድጓዶች ውስጥ ስምንቱ እስከ ሰኔ ወር እንደሚጠናቀቁ አቶ ሞገስ ጠቅሰው፣ በአንድ ዓመት ከአራት ወር ውስጥ ሁሉም ቁፋሮ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል።በአካባቢው የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ተያይዘው እንደሚካሄዱም ጠቅሰው፣ በፕሮጀክቱም 124 ኢትዮጵያውያን እና ሰባት የውጪ ሀገር ዜጎች የሥራ ዕድል አግኝተዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በልዩ ልዩ መልኩ ተጠቃሚ
አዲስ ዘመን መጋቢት 10/2011
በኃይለማርያም ወንድሙ