እርግጥ ነው እኛው ልጆቿና የእኛው መሪዎች በፈጠሩት ችግር አገራችን ኢትዮጵያ በትልቅ ህመም ውስጥ ኖራለች። ህመሟ የህዝቦቿም ህመም ነበርና ዜጎቿ የህመሟ ተጋሪ ሆነው በበሽታዋ ጦስ ቁም ስቅላቸውን ሲያዩ መኖራቸውም አይካድም። የአገሪቱ ህመም የበለጠ ሲጸናም መፍትሄው የህመሙ መንስዔ የሆነውን አመራር መለወጥ ነው በሚል ህሳቤ በተለይም በወጣቱ ኃይል ግንባር ቀደም ተሳታፊነት በመላ አገሪቱ መራር ህዝባዊ አመጾች ተካሂደዋል። የአገሪቱ ህመም ዋነኛ ተጠቂ የነበረው ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍልም በትግሉ ውድ ህይወቱን ሰውቷል፤ አካሉ ጎድሏል፤ ታስሯል፤ ተሰቃይቷልም።
የልጇ ህመምና ስቃይ የእርስዋም ህመምና ስቃይ ሆኖባት እናትም ከልጇ ጋር አብራ ታግላ የህይወትና የአካል መስዋዕትነት ከፍላለች። ለአገር ህመም መፍትሄ ፍለጋ በተደረገ ትግልም ለፍቱንነቱ አገርና ህዝብ በአንድ ድምጽ የመሰከረለት የለውጥ አመራር ተወልዷል። በራሱ በኢህአዴግ ውስጥ የተነሳው የለውጥ ኃይል አገሪቱ በእውነትም በጽኑ ህመም ላይ መሆኗን ያመነና መፍትሄው በራሱ በኢህአዴግ መምጣት እንዳለበት ተገንዝቦ መከፈል ያለበትን ዋጋ ለመክፈል የቆረጠ ነበር። የአገሪቱ ህመም አገሪቱም ሆነች ህዝቦቿ ሊሸከሙት ከሚችሉት በላይ ነበርና በነበረበት ሊቀጥል አልቻለም።
ስለሆነም በዶክተር ዓብይ አህመድ መሪነት የለውጥ (የፈውስ) ኃይሉ አመራሩን ሊቆጣጠር ችሏል። ህዝቡም በዚህ ለውጥ ትልቅ ተስፋ በመሰነቅና አገሪቱን ከሁለንተናዊ ህመሟ እንዲፈውሱ አደራ በማለት ለለውጥ ኃይሉ ያለውን ድጋፍ እጅግ በሚደንቅ መንገድ ገልጿል። እጅግ ውስብስብ በሆነና ለዓመታት የተከማቸ የቤት ሥራ ባለበት ሁኔታ ሀገርን የመምራት ኃላፊነትን የተረከበው የለውጥ አመራርም በተለይም ለበርካታ ፖለቲካዊ ህመሞች ፈውስ የሆኑ ሁነኛ የመፍትሄ እርምጃዎችን ወስዷል።
መገናኛ ብዙሃን በነጻነት የሚንቀሳቀሱበትን ሁኔታ መፍጠር፣ ተሰደውና ተገፍተው የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች ወደአገራቸው ገብተው በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ፣ ከሚያራምዱት ፖለቲካ ጋር ተያይዞ ለእስር ተዳረገው የነበሩ ግለሰቦችን መፍታትና ምርጫ ቦርድን ተአማኒነትን በሚያሰፍን መልክ እንዲመራ ማድረግን የመሳሰሉ እርምጃዎች ለፖለቲካው ህመም በመፍትሄነት የተሰጡ ፍቱን መድሃኒቶች ሲሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥም ተስፋ ሰጪ ለውጥ ማምጣት ችለዋል ማለት ይቻላል። ይሁንና ለፖለቲካው ህመም ግሩም መፍትሄ የሰጠው የለውጥ አመራር የኢኮኖሚ ህመሙን መፈወሱ ላይ ግን እምብዛም እንዳልተሳካለት የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ።
ለማሳያም ያህል የውጭ ምንዛሪ እጥረቱን ለመፍታት አንድ ሰሞን በለብ ለብ የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ዘላቂ ለውጥ አለማምጣታቸው፤ ከዚህ በኋላ አከተመለት የተባለው ጥቁር ገበያም ይባሱኑ ጥርስና ጥፍሩን አሳድጎ አገሪቱን መገዝገዙን መቀጠሉ፤ ኢኮኖሚያዊ አሻጥሩ መፍትሄ ባለማግኘቱ ተገቢ ባልሆነ የኑሮ ውድነት ህዝብ ቁምስቅሉን እያየ መገኘቱ፤ በንግዱም በኮንስትራክሽኑም ሆነ በሌሎች ቢዝነሶች ከፍተኛ መቀዛቀዝ እንዳለ የሚገልጹ አቤቱታዎች መበራከታቸውን ማንሳት ይቻላል። ታክስ ስወራ፣ ህገወጥ በሆነ መንገድ የዶላርና የሸቀጦች ዝውውር በአጠቃላይ የጨለማ ኢኮኖሚ ሀገሪቱን እየዋጣት መሆኑም ከገቢዎች ሚኒስቴር ከሚሰጡ መግለጫዎች ይፋ እየሆኑ ነው።
ከሰሞኑ እንኳን በታክስ ስወራ አገሪቱን ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ ያሳጡ ድርጅቶች ይፋ መደረጋቸው በኢኮኖሚው መስክ ያለው ችግር ምን ያህል የገነገነ እንደሆነ ግልጥልጥ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ከላይ የተዘረዘሩት እውነታዎች ያለምንም መሸፋፈንና ማሽሞንሞን ኢኮኖሚያችን በጽኑ መታመሙን የሚጠቁሙ ናቸው። ይህ ደግሞ የህዝቡን ተስፋ እያጨለመና በለውጥ ኃይሉ ላይ ያለውን እምነት እየሸረሸረ ስለሆነ ፈጣንና ፍቱን ፈውስ የሚፈልግ ይሆናል። እናም ከጋዜጣዊ መግለጫና ከንቅናቄ ጋጋታ ተላቀን ተጨባጭ እርምጃዎችን በመውሰድ ኢኮኖሚያችንን እንፈውስ የዝግጅት ክፍላችን መልዕክት ይሆናል!
አዲስ ዘመን ቅዳሜ የካቲት 30/2011
mexican online pharmacies prescription drugs: mexican pharmacy – buying prescription drugs in mexico
mexican mail order pharmacies
Semaglutide pharmacy price https://rybelsus.tech/# Buy compounded semaglutide online
Rybelsus 7mg