ኮንትሮባንድና ኮንትሮባንዲስት ተነጣጥለው የሚታዩ እንዳልሆኑ የጥምረት ግብራቸው ይመሰክራል፡፡ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት እነዚህ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ኢኮኖሚን ከማድቀቅና የሕዝቡን ድህነት ከማባባስ በተጨማሪ ለፖለቲካዊ ቀውስም ምክንያት ሲሆኑ ይታያል። በገነገነ ኔትወርክ የተሳሰሩ ጥቅመኞች ጠበቅ ያለ እርምጃ ሲወሰድባቸው እዚህም እዚያም እሳት በመጫር ለመንግሥት የፖለቲካ አጀንዳ ሲያቀብሉ ይታያሉ። ብሔርን በብሔር ላይ ማስነሳት ደግሞ ዋናው ክብሪታቸው ነው።
የእነዚህ የአገር ጠላቶች ፈርጣማ ጡንቻ ስር የሰደደ ስለሆነም ጭምር ከኬላ ጀምሮ እስከ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት ድረስ ያሉ የመንግሥት አካላትን እንዳሻው የሚያዝዝ እንደሆነ በተለያዩ መድረኮች ሲገለጽ ይሰማል። በተለይም በተለያዩ የጉምሩክ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች የሚመደቡ አንድ አንድ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ለዚሁ ሕገወጥ ሥራ እንዲመቹ ሆነው የሚመለመሉ መሆናቸው የጸረ ኮንትሮባንድ ሥራውን እጅግ አዳጋች አድርጎታል። በተለይም ከ2009 ጀምሮ የተለያዩ የዘመቻ ስያሜዎች እየተሰጠ ኮንትሮባንድን ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም ከችግሩ ስፋት አንጻር ተጠቃሽ የሆነ ለውጥ ማምጣት ሳይቻል ዛሬ ላይ ተደርሷል።
በአገሪቱ የወጪ ንግድ መስመሮች በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች በድንገት የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋረጠ ማለት ኮንትሮባንድ የጫኑ ተሽከርካሪዎች የመቆጣጠሪያ ኬላ ሳይፈተሹ እያለፉ ነው እስከማለት ተደርሷል። ኮንትሮባንዲስቶቹ የራሳቸው መጋዘን ያላቸው፣ በኔትወርክ የተደራጁ፣ በክትትል ሲደረስባቸውም ክትትል የሚያደርግባቸውን በግልፅና በስውር የሚያስወግዱ፣ የመንግሥት ጡንቻ ሲያርፍባቸውና እኩይ ተግባራቸው ሲስተጓጎል ደግሞ የኢኮኖሚ አሻጥር የሚፈጽሙ ሆነው ደንድነዋል።
በተጨባጭም ኮንትሮባንዲስቶች ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ልካ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ልታገኝ የምትችልባቸው የቁም እንስሳት፣ ቡናና የተለያዩ የቅባት እህሎች፣ ወርቅ፣ ኦፖልና ኤመራልድ የመሳሰሉት ውድ ማዕድናትን በሕገወጥ መንገድ ከአገር እያስወጡ፤ ኤሌክትሮኒክስ፣ ታክስ ሊከፈልባቸው የሚገቡ በርካታ የኢንዱስትሪ ምርቶች አደንዛዥ ዕፅ፣ ሲጋራና የትንባሆ ውጤቶች፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶች፣ ምግቦችና መጠጦች እንዲሁም የጦር መሳሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባሉ። ይህ በግልጽ በምክር ቤት ሳይቀር የተነገረን ሀቅ ደፈር ብሎ እርምጃ መውሰድ ላይ በተለይም ከለውጥ በፊት በነበረው የመንግሥት አስፈጻሚ ዘንድ ስንፈት ነበር። አሁን አገር ለውጥ ላይ ናት። በዚህ ዘርፍም አስገራሚ ለውጦች እየታዩ ናቸው። ባለፉት ወራት ብቻ 600 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ኮንትሮባንድ እቃ ተይዟል። ይሄ የተያዘው ነው ፡፡ አምልጦ የወጣውንና የገባውን ኮንትሮባንዲስቱ ይቁጠረው። የገቢዎች ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤም «ተቋሙ የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ አዲስ ዘመቻ ማካሄድ ጀምሯል።
ሥር የሰደደውን የኮንትሮባንድና የሕገወጥ ንግድ እንቅስቃሴ እናስቆመዋለን። ነገር ግን በምን ያህል ፍጥነት እንደምናስቆመው ነው እርግጠኛ መሆን የቀረን» በማለት እርግጠኛ ሆነው ተናግረዋል። ህዝብና መንግሥትም የሚፈልገው ይህንን ነው። ገቢዎች ሚኒስቴር መፍጠን አለበት። አገርና ህዝብ እየተዘመበሩ ግለሰቦች እየበለጸጉ ወደ ሁለተኛ አገራቸው የሚያሸሹት ሀብት ወደትክክለኛ ባለቤቱ መመለስ ይገባዋል። ይህ የገቢዎች ሚኒስትሯ ቁርጠኛና በተግባር የተደገፈ እርምጃ ይበል የሚየሳኝ ነው። ነገር ግን ከኮንትሮባንድ ንግዱ ጀርባ ያሉትን ትልልቅ ዝሆኖች ወደ ህግ ማምጣቱ ላይ እስካሁን የታየ እርምጃ የለም። ከኮንትሮባንድ እቃው ጋር የሚያዙት ወጣቶች የንብረቱ ባለቤት ዋና ተዋናይም ናቸው ብሎ መከራከር ተቀባይነት የለውም። እነዚህ ቅጥረኛ አስተላላፊ ትናንሽ ዝሆኖች እንጂ ዋናዎቹ ትላልቅ ዝሆኖች አይደሉም።
ስለሆነም የጸረ ኮንትሮባንድ ዘመቻው «አህያውን ፈርቶ ዳውላውን» እንዳይሆን እርምጃው ከላይ እስከታች ይሁን። እነዚህ ህገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪዎች አቀባባዮችን በማደራጀት የውጭ ምንዛሪ በሕጋዊ መንገድ አገር ውስጥ እንዳይገባ ውጭ አገር የሚገኙ ዜጎችን አገር ውስጥ ካሉት ጋር በማገናኘት የገንዘብ ልውውጡ ከባንክ ውጭ እንዲሆን በማድረግ የአገር ኢኮኖሚን የማድቀቅ ስልትም አላቸው። ይሄንን ኬላ ላይ እቆጣጠራለሁ ማለት አይቻልም። ስለሆነም ክትትልና ቁጥጥሩ ከድንበርም ተሻግሮ ከአገራት ጋር በመቀናጀት ሊሆን ይገባል። ለዚህ ደግሞ ኢንተርፖልን መጠቀም ያስፈልጋል። ተቆጣጣሪ ፖሊስ በማቆም ብቻ በሚሠራ የቁጥጥር ሥራ ብቻ የሚፈለገው ደረጃ ላይ መድረስ የሚቻል ስለማይሆን የወንጀሉን ረቂቅነት የሚመጥን የነቃና የበቃ እርምጃ መውሰድ የግድ ይላል፡፡ በአፋር ክልል ሃባላ በምትባልና 2000 የማይበልጡ ነዋሪዎች በሚገኙባት ከተማ ውስጥ 55 ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ሆቴሎች ለመገንባት በሚል ሰበብ በቀረቡ የታክስ ነፃ ጥያቄዎች መሰረት በርካታ ብረት፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ያለቀረጥ በሕገወጥ መንገድ እየገቡ ሲቸበቸቡ መቆየታቸው ታውቋል። የሚያሳዝነው ግን አንዱም ለተባለው አላማ አለመዋሉ ነው።
ይህንን አይነት ግልጽ ወንጀል የፈጸሙ አካላት አይታወቁም ማለት ዓይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ ስለሚሆን መንግሥት የዚህ አይነት ድርጊት ተዋንያንን አንድ ሁለት ብሎ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል። ይህንን አለማድረግ ተመሳሳይ ድርጊት ላለመፈጸሙ ምንም ዋስትና አይኖርም። ይህንን መሰሉን ሕገወጥ ድርጊት ፈፅመው በቁጥጥር ስር ውለዋል የሚባሉት ግለሰቦች ሹፌሮችና አገናኝ ደላሎች ናቸው። ለተጠያቂዎች የሚሰጠው ዋስትናና ቅጣትም ለዛቻ ከሚሰጠው ቅጣት ጋር እኩል መሆኑና የሚያስተምር ከበድ ያለ የቅጣት ርምጃ ያለመወሰዱ ለኮንትሮባንድ መባባስ አንድ ምክንያት ስለሆነ በጊዜ የለንም መንፈስ ግራ ቀኙ ይታይ፤ ላይ ታቹ ይፈተሽ።
«ተቋሙ የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ አዲስ ዘመቻ ማካሄድ ጀምሯል። ሥር የሰደደውን የኮንትሮባንድና የሕገወጥ ንግድ እንቅስቃሴ እናስቆመዋለን። ነገር ግን በምን ያህል ፍጥነት እንደምናስቆመው ነው እርግጠኛ መሆን የቀረን» በማለት እርግጠኛ ሆነው ተናግረዋል። ህዝብና መንግሥትም የሚፈልገው ይህንን ነው። ገቢዎች ሚኒስቴር መፍጠን አለበት። አገርና ህዝብ እየተዘመበሩ ግለሰቦች እየበለጸጉ ወደ ሁለተኛ አገራቸው የሚያሸሹት ሀብት ወደትክክለኛ ባለቤቱ መመለስ ይገባዋል። ይህ የገቢዎች ሚኒስትሯ ቁርጠኛና በተግባር የተደገፈ እርምጃ ይበል የሚየሳኝ ነው። ነገር ግን ከኮንትሮባንድ ንግዱ ጀርባ ያሉትን ትልልቅ ዝሆኖች ወደ ህግ ማምጣቱ ላይ እስካሁን የታየ እርምጃ የለም።
ከኮንትሮባንድ እቃው ጋር የሚያዙት ወጣቶች የንብረቱ ባለቤት ዋና ተዋናይም ናቸው ብሎ መከራከር ተቀባይነት የለውም። እነዚህ ቅጥረኛ አስተላላፊ ትናንሽ ዝሆኖች እንጂ ዋናዎቹ ትላልቅ ዝሆኖች አይደሉም። ስለሆነም የጸረ ኮንትሮባንድ ዘመቻው «አህያውን ፈርቶ ዳውላውን» እንዳይሆን እርምጃው ከላይ እስከታች ይሁን። እነዚህ ህገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪዎች አቀባባዮችን በማደራጀት የውጭ ምንዛሪ በሕጋዊ መንገድ አገር ውስጥ እንዳይገባ ውጭ አገር የሚገኙ ዜጎችን አገር ውስጥ ካሉት ጋር በማገናኘት የገንዘብ ልውውጡ ከባንክ ውጭ እንዲሆን በማድረግ የአገር ኢኮኖሚን የማድቀቅ ስልትም አላቸው። ይሄንን ኬላ ላይ እቆጣጠራለሁ ማለት አይቻልም። ስለሆነም ክትትልና ቁጥጥሩ ከድንበርም ተሻግሮ ከአገራት ጋር በመቀናጀት ሊሆን ይገባል። ለዚህ ደግሞ ኢንተርፖልን መጠቀም ያስፈልጋል። ተቆጣጣሪ ፖሊስ በማቆም ብቻ በሚሠራ የቁጥጥር ሥራ ብቻ የሚፈለገው ደረጃ ላይ መድረስ የሚቻል ስለማይሆን የወንጀሉን ረቂቅነት የሚመጥን የነቃና የበቃ እርምጃ መውሰድ የግድ ይላል፡፡
በአፋር ክልል ሃባላ በምትባልና 2000 የማይበልጡ ነዋሪዎች በሚገኙባት ከተማ ውስጥ 55 ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ሆቴሎች ለመገንባት በሚል ሰበብ በቀረቡ የታክስ ነፃ ጥያቄዎች መሰረት በርካታ ብረት፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ያለቀረጥ በሕገወጥ መንገድ እየገቡ ሲቸበቸቡ መቆየታቸው ታውቋል። የሚያሳዝነው ግን አንዱም ለተባለው አላማ አለመዋሉ ነው። ይህንን አይነት ግልጽ ወንጀል የፈጸሙ አካላት አይታወቁም ማለት ዓይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ ስለሚሆን መንግሥት የዚህ አይነት ድርጊት ተዋንያንን አንድ ሁለት ብሎ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል። ይህንን አለማድረግ ተመሳሳይ ድርጊት ላለመፈጸሙ ምንም ዋስትና አይኖርም። ይህንን መሰሉን ሕገወጥ ድርጊት ፈፅመው በቁጥጥር ስር ውለዋል የሚባሉት ግለሰቦች ሹፌሮችና አገናኝ ደላሎች ናቸው። ለተጠያቂዎች የሚሰጠው ዋስትናና ቅጣትም ለዛቻ ከሚሰጠው ቅጣት ጋር እኩል መሆኑና የሚያስተምር ከበድ ያለ የቅጣት ርምጃ ያለመወሰዱ ለኮንትሮባንድ መባባስ አንድ ምክንያት ስለሆነ በጊዜ የለንም መንፈስ ግራ ቀኙ ይታይ፤ ላይ ታቹ ይፈተሽ።