ኃይለማርያም ወንድሙ
የካዛኪስታን ሜዳዎች መገኛ የሆነው አልማቲ ክልል እምብዛም ጎብኚዎችን የሚጋዝ ቦታ አይደለም። በተለይ በበጋ ወቅት ፤ነገር ግን በአካባቢው አንድ እንግዳ የሆነ ክስተት ታይቶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ብዙ ጎብኚዎችን መሳብ ችሏል።
በካዛኪስታን ከገን እና ሽይርጋንካ በሚባሉ መንደሮች መካከል የሚገኘው አካባቢው በበረዶ ግግር መሐል 14 ሜትር ከፍታ ካለው የበረዶ ማማ ላይ ያለማቋረጥ ውሃ የሚረጭ ሲሆን፤ በቅጽበት ደግሞ ወደ በረዶነት ሲቀየር ይታያል። የበረዶው ልዩ ቅርጹ የበረዶ ግግር ሥዕል የሚመስል ነው። ከላዩ ላይ ከገሞራ ቅላጭ ድንጋይ ፈንታ የፏፏቴ ውሃ የሚረጭ ነው። በዚህም ቦታው በአካባቢው ዝነኛ በመሆኑ ነዋሪዎች ታዋቂነቱንና ልዩ መነሻውን ተንተርሰው ኢንስታግራምን ጨምሮ የማህበራዊ ሚዲያዎች ደጋፊዎችንና ተፅዕኖ ፈጣሪዎቹ የፎቶ ምስሎችንና መልዕክቶችን እየለጠፉ ነው ሲል የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ ይገልፃል።
በቅርቡ እንደ ኢንስታግራም ልጥፍ ዘገባ ከሆነ የበረዶ ገሞራ የምድር ሥር ምንጭ ዓመት ሙሉ ሲረጭ የነበረ ውሃ ውጤት ነው ይላል። በክረምት አካባቢው አሥር ሜትር ዙሪያ አረንጓዴ ልምላሜ በአበባ ያሸበረቀ ሥፍራ ሲመስል ነገር ግን በበጋ ወቅት የሙቀት መጠኑ ዜሮ በታች ሲወርድ ውሃው የረጋ በረዶ ሆኖ የበረዶ ገሞራ ልቃቂት (ከመሬት ወደ ላይ እየፈነዳ የሚጋገርና የሚከመር በረዶ)። ውሃ ርጭቱም በዙሪያው እየቀጠለ ተፈጥሯዊ የበረዶ ግግር ይከሰታል።
በአልማቲ ያለውን በጭንጫ መሬት ላይ የተከሰተ የበረዶ ገሞራ ፎቶዎችና የቪዲዮ ምስሎች በቅርቡ የተለቀቁ የማኅበረሰብ ሚዲያዎች እንደሚያሳዩት በብዙዎች የሚቆጡ ጎብኚዎችን እየሳቡ ነው። አንዳንዶቹ ብዙ ሰዓቶችን ወስደው በቀጥታ እንግዳ የሆነው የተፈጥሮ ሁነት በግል ለማየት ይሄዳሉ።
ሁነቱን በሀሴት የአካባቢው ነዋሪዎች ሲገልጹት ገሞራ ውሃ እያፈለቀ የታየው ይህ ክስተት በዚህ ዓመት የመጀመሪ ነው፤ ቀደም ባሉት ዓመታት አነስተኛ ሲሆን፤ የበረዶ ልቃቂት ብቻ ነበር።
“ባለፈው ዓመት እንደዚህ እንደ የፏፏቴ ከላይ የሚወርድ የውሃ ፍሰትም አልነበረውም፤ የበረዶ ልቃቂት ብቻ ነበር ስትል ሳማል ዝሃይንካ ለተንገር አስጎብኚ ድርጅት መናገሯን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል። የበረዶ ገሞራው ከካዛኪስታን ዋና ከተማ ከሆነው ቀደሞ አስታና ከሚባለው ኑር ሱልጣን ከተማ 4 ሰዓት ይርቃል።
ሳማል ዝሃናክ ለወሬ ምንጩ እንዳሉት ባለፈው ዓመት እንዲህ ያለ የውሃ ፋውንቴን ያልነበረ ምድረበዳ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ይህ ሁኔታ ተፍጥሯል። ይህ የበረዶ ጎመ ከካዛኪስታን ዋና ከተማ ኑር ሱልጣን ከቀድሞዋ አስታና የአራት ሰዓት መንገድ ርቀት አለው።
አዲስ ዘመን የካቲት 02/2013