ጽጌረዳ ጫንያለው
ጸባየ ሸጋ እና ጠንካራ ሰራተኛ ከሚባሉ ሴቶች መካከል ይመደባሉ። በተለይ አራት ለምግብ እንጂ ለስራ ያልደረሱ ልጆቻቸውን ጥለውባቸው ባለቤታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩዋቸው ብዙዎች «ሰማይ ተደፋባቸው » አይነት አዘኔታ አዝነውላቸው ነበር ። እሳቸው ግን ለችግር አልተንበረከኩም።
ያለምንም የገቢ ምንጭ ልጆችን ይዘው ኑሮን መግፋት ተራራን እንደመግፋት ቢሆንባቸውም ሁሉንም ተቋቁመው ለውጤት በቅተዋል። በሥራም ቢሆን የወንድ የሴት ብለው ሳይመርጡ የሚሰሩ፤ እናትነትን ከአባትነት አስተሳስረው የተወጡ ብርቱ ሴት ፣ መንፈሰ ጠንካራ በመሆናቸው ብዙዎች ይቀኑባቸዋል። እኚህ በአድናቆት ያሞካሸናቸው እንስት ወይዘሮ በቀለች ከበደ ይባላሉ።
በአካባቢው ባህል አንዲት ባሏ የሞተባት ሴት ልጆቿን እናትም አባትም ሆና ታሳድጋለች ተብሎ አይታመንም። በዚህም ልጆቿን በዘልማድ እንደሚባለው ‹‹የሴት ልጅ›› ላለማስባል ሲባል ሌላ ባል ለማግባት ይገደዳሉ። እንግዳችን ግን ይህንን አላደረጉም። ልጆቼን በእንጀራ አባት አላሳድግም ፤ ከዚህ በኋላ ወንድ ለምኔ በማለት ዛሬን ደርሰዋል።
በዚህ ደግሞ የቀደመ ሕይወታቸውን ዞር ብለው ሲያዩ ቁልቁለት የሆነው የትላንቱ የፈተና ተራራ በአካባቢያቸው ተምሳሌትነት አንቱ የተባሉ ስላደረጋቸው ደስተኛ ሆነውበታል። «እንደ በቀለች መሆን ይቻል የለ እንዴ? » እንዲባልላቸውም መንገድ ጠርገዋል።
ወይዘሮ በቀለች ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለአካባ ቢው ልጆችም የሥነምግባር መምህር ናቸው። ከእናት በላይ የሰፈሩን ልጅ ቆንጥጠው አሳድገዋል። ዛሬ ድረስ «ለዚህ ያበቃሽኝ አንቺ ነሽ» የሚሏቸውም ብዙ ናቸው።
እናቶችም ቢሆኑ ለልጆቻቸው እናት ስለሆኑላቸው ያመሰግኗቸዋል። ምክንያቱም እዚያ ሰፈር ውስጥ አድጎ በእርሳቸው ተቆንጥጦ ዋልጌ የሆነ ልጅ የለም። ለቁምነገር ያልበቃም እንዲሁ። ስለዚህ እናቴ የሚሏቸው ብዙዎች ናቸው።
ባለታሪካችን ከዚህ አለፍ ሲልም ድህነትን በሀብት መኖርን በሚገባ ያዩ፤ ከትልልቅ ሱቅ እስከ ሻይና ቡና እንዲሁም ከሰልና አረቄ ሸጠው ያደሩ በመሆናቸው ምሳሌነታቸው የጎላ ነው። እናም ብዙ ሊዘከሩና አርአያነታቸው ሊቀሰም የሚገባቸው፣ ታዋቂ ሳይሆኑ አዋቂ የሆኑ እናት በመሆናቸው፤ ባላደራነት የሆነላቸው የተፈጠሩለትን አላማ በአግባቡ የከወኑ ናቸውና ለዛሬ ‹‹ የሕይወት ገጽታ›› አምድ እንግዳችን አድርገናቸዋል።
ስምን መላክ ያወጣዋል
የወይዘሮ በቀለች እናት ሰማችኝ ማርያም ጠገናው የሚባሉ ሲሆን፤ የስለትና ብቸኛ ልጅ ናቸው። በዚህም ነው ሰማችኝ የተባሉት። ይህ ደግሞ ቤተሰቡ የልጅ ጠኔ እንዲይዘው አድርጎታል። ሆኖም ከሰማችኝ ማርያም በኋላ አምላክ ቤታቸውን በልጅ በረከት ሞላውና ስምንት ልጆች ተወለዱ። ቤቱም በልጅ አሸበረቀ።
ይህ የሆነለት ቤተሰብም ለእያንዳንዱ ልጅ የተለየ ስም እየሰጠ ነበር የአምላኩን በረከት ያመሰገነው። ለዚህም ማሳያው የእንግዳችን ስም ሲሆን፤ በቀለች ያሏቸው ምንም ሳይታመሙና ችግር ሳይገጥማቸው በማደጋቸው እንዲሁም ቤተሰቡ እየተበራከተ በመሄዱ የተነሳ እንደሆነ ይናገራሉ።
እንግዳችን ትውልዳቸው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ በጣሶና ጉልት አገር ሬት አፋፍ በምትባል ልዩ ስፍራ ሲሆን፤ በ1948 ዓ.ም ነው የተወለዱት። እንደማንኛውም የገጠር ልጅ ከብት አግደውም ነው ያደጉት። በእርግጥ የባላባት ልጅ በመሆናቸው አገልጋዮች ቤቱን ስለሞሉት ሥራ መስራት አይፈቀድላቸውም።
ነገር ግን ወይዘሮ በቀለችና ወንድሞቻቸው መስራትንና ከሰው ጋር መዋልን ስለሚወዱ ከብት ለመጠበቅ ከእነዚህ አገልጋዮች ጋር ተደብቀውም ቢሆን ይሄዳሉ። አብረው ቆይተው የሚመለሱት ማታ ላይ ነው። ከፊታቸው የሚያዩት ደስታ ስለሚገርማቸውም እያደር መቆጣጠሩን እንዳቆሙም አጫውተውናል።
ባለታሪካችን ፈቃድ ካገኙበት ጊዜ ጀምሮ ከአገልጋዮቹ ጋር የማይሰሩትና የማይሞክሩት ሥራ አልነበረም። በተለይ የእርሻ ሥራ ላይ ልዩ ችሎታቸውን እንዲያሳዩ ሆነዋል። አረም በማረም የሚቀድማቸው የለም። ከዚያ ሻገር ሲል ደግሞ በቤት ውስጥ ስራ ‹‹ወጧ ጣት ያስቆረጥማል›› የሚባልለት ሙያ ያላቸው አድርጓቸዋል።
ስፌት መስፋት፣ ጥጥ መፍተልና ጥልፍ ነገሮችን መስራትም በእረፍት ጊዜያቸው የሚያከናውኑት ስራ ነው።ይህንን ሁሉ ሲከውኑ ደግሞ ጊዜው ይነጉድና ከአገልጋዮቹ እኩል የሚተኙበት ሰዓት እንደነበር ያስታውሳሉ።
በዚህ ጊዜ ግን በተለይ አያታቸው በጣም ይቆጣሉ። በቤት ውስጥ ሁሉም ልጅ የፈለገውን አግኝቶ ተቀማጥሎ እንዲያድግ ፤ የአያት ልጅ ቅምጥል የሚባለውን ተግባራዊ እንዲደረግ ፤ በባላባት የልጅ ልጅ ባህል እንዲያድጉ እንጂ እንዲለፉ አይፈልጉም።
ስለዚህም ዘወትር አገልጋዮቹን ‹‹ ይህ እንዳይደገም›› እያሉ ይቆጧቸዋል። እነ ወይዘሮ በቀለች ግን ቁጣውን ወደጎን በመተውና ምንም እንደማይሏቸው በማሳመን መስራትን ልምዳቸው አድርገው ለዛሬ ሕይወታቸው ስንቅ ሰንቀዋል።
እንግዳችን በባህሪያቸው ምስጉን፣ ታዛዥና ያላቸውን ማካፈል የሚወዱ ናቸው። በዚህም ከቤት ሳይቀር በርበሬና ሽሮ እየሰረቁ ለተቸገሩ ይሰጡ እንደነበር አይረሱትም። ተጨዋችና ፍልቅልቅም ናቸው።
ከሰው ጋር አብሎ መብላት የሚያስደስታቸው፤ ብቻዬን የሚሉት ነገር የሌላቸውና እችላለሁ እንጂ አልችልምን የማይወዱም ልጅ ነበሩ። ያዩትን በአንድ ጊዜ የሚቀዱና የሚሰሩ በመሆናቸው የቆዩ ነገሮች ሳይቀሩ እርሳቸውን በመጠየቅ ነው የአካባቢው ልጆች የሚያስታውሱት። ታሪክ መስማትን በጣም የሚወዱና ማንበብ የሚያዘወትሩ ልጅ እንደነበሩ ያስታውሳሉ።
በውጤት የታጀበው ትምህርት
ወይዘሮ በቀለች ፊደል የቆጠሩት ከአያታቸው ጋር እያሉ ሲሆን፤ አያታቸው በኋላ ስደክም ታግዘኛለች በሚል የጸሎት መጽሐፍት እንዲያነቡ ፊደል አስቆጥረዋቸዋል። ከዚያም የመሰረተ ትምህርትን ተቀላቀሉ ። ብዙም ሳይቆዩ የተሻሉ ተማሪ በመሆናቸው አንደኛ ክፍል ገቡ ።
ስለዚህም በእነዋሪ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ስምንተኛ ክፍል ትምህርታቸውን በአንድ ዓመት ሁለት ጊዜ(ደብል) እንዲያልፉ እየተደረጉ ጭምር በማለፍ መከታተል ችለዋል። በትምህርታቸው በጣም ጎበዝ ተማሪ በመሆናቸው በፈተና ጊዜ መቶ ከመቶ ነበር የሚያገኙት። በተለይ እንግሊዝኛና የሒሳብ ትምህርት አንድም ክፍል ላይ ከመቶ ውጪ አምጥተው እንደማያቁ የትምህርት ውጤት ማሳወቂያ ካርዳቸው ይመሰክራል።
የስምንተኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተናም ቢሆን ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት መካከል ናቸው። በዚህም የዘጠነኛ ክፍል ትምህርታቸውን ለመከታተል በእነዋሪ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት ገቡ። ሆኖም ባለቤታቸው በማረፉና የልጆች ኃላፊነት በእርሳቸው ጫንቃ ላይ በመውደቁ ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ ተሳናቸው ።
ትምህርቱ ከእንግዲህ ለልጆቼ ብለው የተጋፈጡትን ኑሮ ለማሸነፍ ደፋ ቀና ወደማለት ገቡ። በእርግጥ ዛሬ ድረስ በሁለቱ ትምህርት ያላቸው እውቀት ስንመለከት ተምረናል ከሚሉ ሰዎች የተሻለ መሆኑን በደንብ እንገነዘባለን። በዚያ ላይ የትምህርት ጥማታቸውን በልጆቻቸው አርክተዋል።
ጎሽ ለልጇ ስትል
እናትነት ተፈጥሮ ለሴቶች የሰጠቻቸው ልዩ ገጸ በረከት እንደሆነ ማንም የሚክደውና የሚጋፋው አይደለም። በዚህም እንደ እናቶች የአመራር ብቃትና ነባራዊ ሁኔታ ልጆች ተቃኝተው ያድጋሉ። አገር የመሆንንም ኃላፊነት ይረከባሉ። ዳግም እናት የሚሆኑ ሰዎችንም ይፈጥራሉ። ስለዚህም እናትነት ሰው የመስራት ኃይል ነው፤ እናትነት ከሆድ መሙላት በላይ በመንፈስና በአዕምሮ ልጅን መኮትኮት ነው።
እናትነት የማንነት ጤናን መፍጠሪያ ፣ መንከባከቢያ ትምህርት ቤት ነው። ከራስ በላይ ለልጅ ማሰብና መሞትም ጭምር ነው። ለዚህም ማሳያው በአባባል ሳይቀር ‹‹ ጎሽ ለልጇ ስትል ተወጋች›› ይባላል። ስለዚህም እናት ለልጅ የምትከፍለው መስዋዕትነት ማሳያ ነው። ይህ ሁሉ ባህሪ ስላለውም ብዙዎች ስለእናት ሲነሳ እንባ ይቀናቸዋል።
የወይዘሮ በቀለች ልጆችም ይኸው ስሜት ነው ያላቸው። ምክንያቱም እናታቸው ይህን እውነታ ቁልጭ አድርገው አሳይተዋቸዋል። እርሳቸው ለልጆቻቸው ሲሉ ወጣትነታቸውን ሰጥተዋል፤ ትምህርታቸውን ትተዋል፤ ሀብትና ንብረት ለምኔ ብለዋል። ከተደላደለ ኑሮ ወርደው አረቄ፣ ጠላና ከሰል እየሸጡ ልጆቻቸውን አሳድገዋል።
በሕይወት አጋጣሚና ጉዞ ውስጥ ብዙ መልካም አጋጣሚዎች በተለያየ መንገድ ያመልጡና ምርጫችን ያልሆነ ነገርን እንድመርጥ እንገደዳለን። ወይዘሮ በቀለችም ያልመረጡትን ምርጫ እንዲኖሩት የሆኑት ለዚህ ነው። ግን አንድ ነገር ያምናሉ። ክፉ የሚባል ነገር በሥራ እንደሚቀየርና መልካም ምርጫ እንደሚሆን። በዚህም አጋጣሚው ከባድ ቢሆንም ያንን እናት ስለሆኑ አልፈውታል።
ምቾታቸው ሲጠፋ አሁን ያለው ፈተናቸው የደስታ ምንጫቸው የሚያደርጉበትን አጋጣሚም ፈጥረዋል። ነገሩ ከሀዘን ውጪ ምንም መልክ የለውም። መቆዘም ግን መፍትሄ አይሆንም ብለው ስላሰቡም ያለፈውን ለጊዜው ትተው የወደፊቱን በማለም ነው በትጋት ቀጣይ ጉዟቸውን የቀጠሉት።
በእርሳቸው አይን ልጅ ማለት ሁሉ ነገር ነው። እናትነትም ለልጅ መኖር ነው። ስለዚህ የራሳቸውን ሕይወት፣ ወጣትነት ለልጆቻቸው ገብረው የልጆቻቸው ልጅነት፣ ወጣትነትና ስኬት እንዳይቀጭጭ አድርገዋል። በዚህ ሕይወት ውስጥ ያልታየ ፈተና የለም። ልጆቻቸውን እያሉ በሀብት ሲንደላቀቁ በነበረበት ቤት ውስጥ ሆነው ሻይ፣ ዳቦ ፤ ከሰል ሸጠዋል።
አረቄ ማውጣት ባይችሉም ከሰራተኛቸው በመማር አረቄ እያወጡ በመሸጥ ክፉውን ጊዜያቸውን አሳልፈዋል። በተለይም እርሳቸው እየራባቸውና ጦማቸውን እያደሩ የልጆቻቸውን ፈገግታ ማየት መቻላቸው እውነተኛ እናትነት መገለጫ ያደርጋቸዋል።
ወይዘሮ በቀለች ለልጆቻቸው የከፈሉት መስዋዕትነት የሚጀምረው ባለቤታቸውን በሕይወት ሲለዩት ጀምሮ ነው። ምክንያቱም ባለቤታቸው በሕይወት ሳሉ እንኳን ልጆቻቸው ጎረቤቶቻቸው ችግር ሲጠብሳቸው አይተው አያውቁም። በዓል በመጣ ቁጥር በሬ ታርዶ በነጻ ተካፍለው ነው በደስታ ጊዜውን የሚያሳልፉት። አሮጌ ልብስ የሚለብስ አይኖርም።
ጣቃውም ሰፊውም ከቤት ስለሆነ አዲስ ልብስ ተሰፍቶ ይሰጣቸዋል። ስለዚህም ሁሉም ጎረቤት እየመረቀ ኑሮውን አጣፍጦ ይኖራል ። ልጆች ሲሆኑ ደግሞ ምን ምን እንደሚደረግላቸው መገመት አያዳግትም። ይሁንና ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለጎረቤቱ የሚኖሩት የባለታሪካችን ባለቤት ባልጠበቁት መንገድ በወዳጃቸው ተከዱ። ሕይወታቸውንም ተነጠቁ። ልጆቻቸውንም ትተው ላይመለሱ ነጎዱ።
ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ
ነገሩ እንዲህ ነው። ከአንድ ወዳጃቸው ጋር በሽርክና የሕዝብና የጭነት መኪና ይገዛሉ። ሚስት ደግሞ ገንዘብ የሰውን ነብስ እንደሚነጥቅ ታምናለችና ‹‹ንብረትህን ወደራስህ ሰብስብ›› ስትል ትመክራለች። ምክሯን የሰማው ባልም ቤት ውስጥ ያሉ ውድ የሚባሉ ንብረቶቹን ሸጦ እቁብም በግዢ ወስዶ ወዳጄ ለሚለው ሸሪኩ ይሰጠዋል። ስሙን ነገ ለማዘዋወርም እየተሰናዳ ሳለ ሀብትና ንብረቱ ያሳሳው ሸሪኩ ሊያስገድለው ፈለገ።
ሁኔታው እንዳይታወቅበትም ዘረፋ ለማስመሰል ነው የሞከረው። ወንበዴዎችን ቀጥሮ እንግዳችን የሚሸጡበት ሱቅና እርሱም የሚነግድበት ቦታ ላይ ጸብ እንዲፈጠር አደረገ። የዋሁ ሰው የተደገሰለትን ሳያውቅ ሊገላገል ከተመቻቸ ወንበሩ ላይ ተነስቶ መሀል ገባ።
በገላጋይ ስምም ተገደለ። ያ ሳያበቃም ሀብት ንብረቱ ተዘረፈ። ባለታሪካችንም እንዲሁ ሊሆኑ ነበር። ነገር ግን አምላክ ቀናቸውና ባልሽ አረፈ ሲባሉ ራሳቸውን ስተው ነበርና ሀብት ንብረቱ ቢዘረፍም እርሳቸው ከሞት ተረፉ። ይህ ከሆነ በኋላ ነው በባዶ እንዲነሱና ልጆቻቸውን በችግር ውስጥ እንዲያሳድጉ የተገደዱት።
ወይዘሮ በቀለች ሁለት አይነት ሞት በወዳጃቸው ሞተዋል። የመጀመሪያው ባላቸው መገደሉ ሲሆን፤ ሁለተኛው ሀብት ንብረታቸው መዘረፉና በጋራ የተገዛው መኪናን መካዳቸው ነው። በእርግጥ በሕግ መጠየቅ ይችሉ ነበር። ሆኖም ሕግም ቢሆን በገንዘብ የተያዘበት ጊዜ ነው። በዚያ ላይ ልጆቻቸውን ሳያሳድጉ
ጽጌረዳ ጫንያለው
ጸባየ ሸጋ እና ጠንካራ ሰራተኛ ከሚባሉ ሴቶች መካከል ይመደባሉ። በተለይ አራት ለምግብ እንጂ ለስራ ያልደረሱ ልጆቻቸውን ጥለውባቸው ባለቤታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩዋቸው ብዙዎች «ሰማይ ተደፋባቸው » አይነት አዘኔታ አዝነውላቸው ነበር ። እሳቸው ግን ለችግር አልተንበረከኩም።
ያለምንም የገቢ ምንጭ ልጆችን ይዘው ኑሮን መግፋት ተራራን እንደመግፋት ቢሆንባቸውም ሁሉንም ተቋቁመው ለውጤት በቅተዋል። በሥራም ቢሆን የወንድ የሴት ብለው ሳይመርጡ የሚሰሩ፤ እናትነትን ከአባትነት አስተሳስረው የተወጡ ብርቱ ሴት ፣ መንፈሰ ጠንካራ በመሆናቸው ብዙዎች ይቀኑባቸዋል። እኚህ በአድናቆት ያሞካሸናቸው እንስት ወይዘሮ በቀለች ከበደ ይባላሉ።
በአካባቢው ባህል አንዲት ባሏ የሞተባት ሴት ልጆቿን እናትም አባትም ሆና ታሳድጋለች ተብሎ አይታመንም። በዚህም ልጆቿን በዘልማድ እንደሚባለው ‹‹የሴት ልጅ›› ላለማስባል ሲባል ሌላ ባል ለማግባት ይገደዳሉ። እንግዳችን ግን ይህንን አላደረጉም። ልጆቼን በእንጀራ አባት አላሳድግም ፤ ከዚህ በኋላ ወንድ ለምኔ በማለት ዛሬን ደርሰዋል።
በዚህ ደግሞ የቀደመ ሕይወታቸውን ዞር ብለው ሲያዩ ቁልቁለት የሆነው የትላንቱ የፈተና ተራራ በአካባቢያቸው ተምሳሌትነት አንቱ የተባሉ ስላደረጋቸው ደስተኛ ሆነውበታል። «እንደ በቀለች መሆን ይቻል የለ እንዴ? » እንዲባልላቸውም መንገድ ጠርገዋል።
ወይዘሮ በቀለች ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለአካባ ቢው ልጆችም የሥነምግባር መምህር ናቸው። ከእናት በላይ የሰፈሩን ልጅ ቆንጥጠው አሳድገዋል። ዛሬ ድረስ «ለዚህ ያበቃሽኝ አንቺ ነሽ» የሚሏቸውም ብዙ ናቸው። እናቶችም ቢሆኑ ለልጆቻቸው እናት ስለሆኑላቸው ያመሰግኗቸዋል። ምክንያቱም እዚያ ሰፈር ውስጥ አድጎ በእርሳቸው ተቆንጥጦ ዋልጌ የሆነ ልጅ የለም። ለቁምነገር ያልበቃም እንዲሁ። ስለዚህ እናቴ የሚሏቸው ብዙዎች ናቸው።
ባለታሪካችን ከዚህ አለፍ ሲልም ድህነትን በሀብት መኖርን በሚገባ ያዩ፤ ከትልልቅ ሱቅ እስከ ሻይና ቡና እንዲሁም ከሰልና አረቄ ሸጠው ያደሩ በመሆናቸው ምሳሌነታቸው የጎላ ነው። እናም ብዙ ሊዘከሩና አርአያነታቸው ሊቀሰም የሚገባቸው፣ ታዋቂ ሳይሆኑ አዋቂ የሆኑ እናት በመሆናቸው፤ ባላደራነት የሆነላቸው የተፈጠሩለትን አላማ በአግባቡ የከወኑ ናቸውና ለዛሬ ‹‹ የሕይወት ገጽታ›› አምድ እንግዳችን አድርገናቸዋል።
ስምን መላክ ያወጣዋል
የወይዘሮ በቀለች እናት ሰማችኝ ማርያም ጠገናው የሚባሉ ሲሆን፤ የስለትና ብቸኛ ልጅ ናቸው። በዚህም ነው ሰማችኝ የተባሉት። ይህ ደግሞ ቤተሰቡ የልጅ ጠኔ እንዲይዘው አድርጎታል። ሆኖም ከሰማችኝ ማርያም በኋላ አምላክ ቤታቸውን በልጅ በረከት ሞላውና ስምንት ልጆች ተወለዱ። ቤቱም በልጅ አሸበረቀ።
ይህ የሆነለት ቤተሰብም ለእያንዳንዱ ልጅ የተለየ ስም እየሰጠ ነበር የአምላኩን በረከት ያመሰገነው። ለዚህም ማሳያው የእንግዳችን ስም ሲሆን፤ በቀለች ያሏቸው ምንም ሳይታመሙና ችግር ሳይገጥማቸው በማደጋቸው እንዲሁም ቤተሰቡ እየተበራከተ በመሄዱ የተነሳ እንደሆነ ይናገራሉ።
እንግዳችን ትውልዳቸው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ በጣሶና ጉልት አገር ሬት አፋፍ በምትባል ልዩ ስፍራ ሲሆን፤ በ1948 ዓ.ም ነው የተወለዱት። እንደማንኛውም የገጠር ልጅ ከብት አግደውም ነው ያደጉት። በእርግጥ የባላባት ልጅ በመሆናቸው አገልጋዮች ቤቱን ስለሞሉት ሥራ መስራት አይፈቀድላቸውም።
ነገር ግን ወይዘሮ በቀለችና ወንድሞቻቸው መስራትንና ከሰው ጋር መዋልን ስለሚወዱ ከብት ለመጠበቅ ከእነዚህ አገልጋዮች ጋር ተደብቀውም ቢሆን ይሄዳሉ። አብረው ቆይተው የሚመለሱት ማታ ላይ ነው። ከፊታቸው የሚያዩት ደስታ ስለሚገርማቸውም እያደር መቆጣጠሩን እንዳቆሙም አጫውተውናል።
ባለታሪካችን ፈቃድ ካገኙበት ጊዜ ጀምሮ ከአገልጋዮቹ ጋር የማይሰሩትና የማይሞክሩት ሥራ አልነበረም። በተለይ የእርሻ ሥራ ላይ ልዩ ችሎታቸውን እንዲያሳዩ ሆነዋል። አረም በማረም የሚቀድማቸው የለም። ከዚያ ሻገር ሲል ደግሞ በቤት ውስጥ ስራ ‹‹ወጧ ጣት ያስቆረጥማል›› የሚባልለት ሙያ ያላቸው አድርጓቸዋል።
ስፌት መስፋት፣ ጥጥ መፍተልና ጥልፍ ነገሮችን መስራትም በእረፍት ጊዜያቸው የሚያከናውኑት ስራ ነው።ይህንን ሁሉ ሲከውኑ ደግሞ ጊዜው ይነጉድና ከአገልጋዮቹ እኩል የሚተኙበት ሰዓት እንደነበር ያስታውሳሉ። በዚህ ጊዜ ግን በተለይ አያታቸው በጣም ይቆጣሉ።
በቤት ውስጥ ሁሉም ልጅ የፈለገውን አግኝቶ ተቀማጥሎ እንዲያድግ ፤ የአያት ልጅ ቅምጥል የሚባለውን ተግባራዊ እንዲደረግ ፤ በባላባት የልጅ ልጅ ባህል እንዲያድጉ እንጂ እንዲለፉ አይፈልጉም። ስለዚህም ዘወትር አገልጋዮቹን ‹‹ ይህ እንዳይደገም›› እያሉ ይቆጧቸዋል። እነ ወይዘሮ በቀለች ግን ቁጣውን ወደጎን በመተውና ምንም እንደማይሏቸው በማሳመን መስራትን ልምዳቸው አድርገው ለዛሬ ሕይወታቸው ስንቅ ሰንቀዋል።
እንግዳችን በባህሪያቸው ምስጉን፣ ታዛዥና ያላቸውን ማካፈል የሚወዱ ናቸው። በዚህም ከቤት ሳይቀር በርበሬና ሽሮ እየሰረቁ ለተቸገሩ ይሰጡ እንደነበር አይረሱትም። ተጨዋችና ፍልቅልቅም ናቸው። ከሰው ጋር አብሎ መብላት የሚያስደስታቸው፤ ብቻዬን የሚሉት ነገር የሌላቸውና እችላለሁ እንጂ አልችልምን የማይወዱም ልጅ ነበሩ።
ያዩትን በአንድ ጊዜ የሚቀዱና የሚሰሩ በመሆናቸው የቆዩ ነገሮች ሳይቀሩ እርሳቸውን በመጠየቅ ነው የአካባቢው ልጆች የሚያስታውሱት። ታሪክ መስማትን በጣም የሚወዱና ማንበብ የሚያዘወትሩ ልጅ እንደነበሩ ያስታውሳሉ።
በውጤት የታጀበው ትምህርት
ወይዘሮ በቀለች ፊደል የቆጠሩት ከአያታቸው ጋር እያሉ ሲሆን፤ አያታቸው በኋላ ስደክም ታግዘኛለች በሚል የጸሎት መጽሐፍት እንዲያነቡ ፊደል አስቆጥረዋቸዋል። ከዚያም የመሰረተ ትምህርትን ተቀላቀሉ ። ብዙም ሳይቆዩ የተሻሉ ተማሪ በመሆናቸው አንደኛ ክፍል ገቡ ።
ስለዚህም በእነዋሪ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ስምንተኛ ክፍል ትምህርታቸውን በአንድ ዓመት ሁለት ጊዜ(ደብል) እንዲያልፉ እየተደረጉ ጭምር በማለፍ መከታተል ችለዋል። በትምህርታቸው በጣም ጎበዝ ተማሪ በመሆናቸው በፈተና ጊዜ መቶ ከመቶ ነበር የሚያገኙት። በተለይ እንግሊዝኛና የሒሳብ ትምህርት አንድም ክፍል ላይ ከመቶ ውጪ አምጥተው እንደማያቁ የትምህርት ውጤት ማሳወቂያ ካርዳቸው ይመሰክራል።
የስምንተኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተናም ቢሆን ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት መካከል ናቸው። በዚህም የዘጠነኛ ክፍል ትምህርታቸውን ለመከታተል በእነዋሪ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት ገቡ። ሆኖም ባለቤታቸው በማረፉና የልጆች ኃላፊነት በእርሳቸው ጫንቃ ላይ በመውደቁ ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ ተሳናቸው ።
ትምህርቱ ከእንግዲህ ለልጆቼ ብለው የተጋፈጡትን ኑሮ ለማሸነፍ ደፋ ቀና ወደማለት ገቡ። በእርግጥ ዛሬ ድረስ በሁለቱ ትምህርት ያላቸው እውቀት ስንመለከት ተምረናል ከሚሉ ሰዎች የተሻለ መሆኑን በደንብ እንገነዘባለን። በዚያ ላይ የትምህርት ጥማታቸውን በልጆቻቸው አርክተዋል።
ጎሽ ለልጇ ስትል
እናትነት ተፈጥሮ ለሴቶች የሰጠቻቸው ልዩ ገጸ በረከት እንደሆነ ማንም የሚክደውና የሚጋፋው አይደለም። በዚህም እንደ እናቶች የአመራር ብቃትና ነባራዊ ሁኔታ ልጆች ተቃኝተው ያድጋሉ። አገር የመሆንንም ኃላፊነት ይረከባሉ። ዳግም እናት የሚሆኑ ሰዎችንም ይፈጥራሉ። ስለዚህም እናትነት ሰው የመስራት ኃይል ነው፤ እናትነት ከሆድ መሙላት በላይ በመንፈስና በአዕምሮ ልጅን መኮትኮት ነው።
እናትነት የማንነት ጤናን መፍጠሪያ ፣ መንከባከቢያ ትምህርት ቤት ነው። ከራስ በላይ ለልጅ ማሰብና መሞትም ጭምር ነው። ለዚህም ማሳያው በአባባል ሳይቀር ‹‹ ጎሽ ለልጇ ስትል ተወጋች›› ይባላል። ስለዚህም እናት ለልጅ የምትከፍለው መስዋዕትነት ማሳያ ነው። ይህ ሁሉ ባህሪ ስላለውም ብዙዎች ስለእናት ሲነሳ እንባ ይቀናቸዋል።
የወይዘሮ በቀለች ልጆችም ይኸው ስሜት ነው ያላቸው። ምክንያቱም እናታቸው ይህን እውነታ ቁልጭ አድርገው አሳይተዋቸዋል። እርሳቸው ለልጆቻቸው ሲሉ ወጣትነታቸውን ሰጥተዋል፤ ትምህርታቸውን ትተዋል፤ ሀብትና ንብረት ለምኔ ብለዋል። ከተደላደለ ኑሮ ወርደው አረቄ፣ ጠላና ከሰል እየሸጡ ልጆቻቸውን አሳድገዋል።
በሕይወት አጋጣሚና ጉዞ ውስጥ ብዙ መልካም አጋጣሚዎች በተለያየ መንገድ ያመልጡና ምርጫችን ያልሆነ ነገርን እንድመርጥ እንገደዳለን። ወይዘሮ በቀለችም ያልመረጡትን ምርጫ እንዲኖሩት የሆኑት ለዚህ ነው። ግን አንድ ነገር ያምናሉ። ክፉ የሚባል ነገር በሥራ እንደሚቀየርና መልካም ምርጫ እንደሚሆን። በዚህም አጋጣሚው ከባድ ቢሆንም ያንን እናት ስለሆኑ አልፈውታል።
ምቾታቸው ሲጠፋ አሁን ያለው ፈተናቸው የደስታ ምንጫቸው የሚያደርጉበትን አጋጣሚም ፈጥረዋል። ነገሩ ከሀዘን ውጪ ምንም መልክ የለውም። መቆዘም ግን መፍትሄ አይሆንም ብለው ስላሰቡም ያለፈውን ለጊዜው ትተው የወደፊቱን በማለም ነው በትጋት ቀጣይ ጉዟቸውን የቀጠሉት።
በእርሳቸው አይን ልጅ ማለት ሁሉ ነገር ነው። እናትነትም ለልጅ መኖር ነው። ስለዚህ የራሳቸውን ሕይወት፣ ወጣትነት ለልጆቻቸው ገብረው የልጆቻቸው ልጅነት፣ ወጣትነትና ስኬት እንዳይቀጭጭ አድርገዋል። በዚህ ሕይወት ውስጥ ያልታየ ፈተና የለም። ልጆቻቸውን እያሉ በሀብት ሲንደላቀቁ በነበረበት ቤት ውስጥ ሆነው ሻይ፣ ዳቦ ፤ ከሰል ሸጠዋል።
አረቄ ማውጣት ባይችሉም ከሰራተኛቸው በመማር አረቄ እያወጡ በመሸጥ ክፉውን ጊዜያቸውን አሳልፈዋል። በተለይም እርሳቸው እየራባቸውና ጦማቸውን እያደሩ የልጆቻቸውን ፈገግታ ማየት መቻላቸው እውነተኛ እናትነት መገለጫ ያደርጋቸዋል።
ወይዘሮ በቀለች ለልጆቻቸው የከፈሉት መስዋዕትነት የሚጀምረው ባለቤታቸውን በሕይወት ሲለዩት ጀምሮ ነው። ምክንያቱም ባለቤታቸው በሕይወት ሳሉ እንኳን ልጆቻቸው ጎረቤቶቻቸው ችግር ሲጠብሳቸው አይተው አያውቁም። በዓል በመጣ ቁጥር በሬ ታርዶ በነጻ ተካፍለው ነው በደስታ ጊዜውን የሚያሳልፉት።
አሮጌ ልብስ የሚለብስ አይኖርም። ጣቃውም ሰፊውም ከቤት ስለሆነ አዲስ ልብስ ተሰፍቶ ይሰጣቸዋል። ስለዚህም ሁሉም ጎረቤት እየመረቀ ኑሮውን አጣፍጦ ይኖራል ። ልጆች ሲሆኑ ደግሞ ምን ምን እንደሚደረግላቸው መገመት አያዳግትም። ይሁንና ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለጎረቤቱ የሚኖሩት የባለታሪካችን ባለቤት ባልጠበቁት መንገድ በወዳጃቸው ተከዱ። ሕይወታቸውንም ተነጠቁ። ልጆቻቸውንም ትተው ላይመለሱ ነጎዱ።
ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ
ነገሩ እንዲህ ነው። ከአንድ ወዳጃቸው ጋር በሽርክና የሕዝብና የጭነት መኪና ይገዛሉ። ሚስት ደግሞ ገንዘብ የሰውን ነብስ እንደሚነጥቅ ታምናለችና ‹‹ንብረትህን ወደራስህ ሰብስብ›› ስትል ትመክራለች። ምክሯን የሰማው ባልም ቤት ውስጥ ያሉ ውድ የሚባሉ ንብረቶቹን ሸጦ እቁብም በግዢ ወስዶ ወዳጄ ለሚለው ሸሪኩ ይሰጠዋል።
ስሙን ነገ ለማዘዋወርም እየተሰናዳ ሳለ ሀብትና ንብረቱ ያሳሳው ሸሪኩ ሊያስገድለው ፈለገ። ሁኔታው እንዳይታወቅበትም ዘረፋ ለማስመሰል ነው የሞከረው። ወንበዴዎችን ቀጥሮ እንግዳችን የሚሸጡበት ሱቅና እርሱም የሚነግድበት ቦታ ላይ ጸብ እንዲፈጠር አደረገ። የዋሁ ሰው የተደገሰለትን ሳያውቅ ሊገላገል ከተመቻቸ ወንበሩ ላይ ተነስቶ መሀል ገባ።
በገላጋይ ስምም ተገደለ። ያ ሳያበቃም ሀብት ንብረቱ ተዘረፈ። ባለታሪካችንም እንዲሁ ሊሆኑ ነበር። ነገር ግን አምላክ ቀናቸውና ባልሽ አረፈ ሲባሉ ራሳቸውን ስተው ነበርና ሀብት ንብረቱ ቢዘረፍም እርሳቸው ከሞት ተረፉ። ይህ ከሆነ በኋላ ነው በባዶ እንዲነሱና ልጆቻቸውን በችግር ውስጥ እንዲያሳድጉ የተገደዱት።
ወይዘሮ በቀለች ሁለት አይነት ሞት በወዳጃቸው ሞተዋል። የመጀመሪያው ባላቸው መገደሉ ሲሆን፤ ሁለተኛው ሀብት ንብረታቸው መዘረፉና በጋራ የተገዛው መኪናን መካዳቸው ነው። በእርግጥ በሕግ መጠየቅ ይችሉ ነበር። ሆኖም ሕግም ቢሆን በገንዘብ የተያዘበት ጊዜ ነው። በዚያ ላይ ልጆቻቸውን ሳያሳድጉ ሊገደሉ ይችላሉ።
ስለዚህም እውነቱን ለአምላክ ፍርድ ትተው በሞት ውስጥ ሕይወት እንዳለ አምነው ‹‹የእናት ሻማነት ሲወድቁ በእጅ ሲያረጁ በልጅ›› የሚለውን አባባል በተግባር ለማሳየት ጉዟቸውን ወደ ፊት አደረጉ። ከሚጋግሩት የአረቄ እንጀራ ላይ አንዱን ለአራት ልጆቻቸው እያካፈሉም ሕይወት እንዲህ ናት እያሉ ኑሯቸውን መግፋት ጀመሩ።
ልጆቻቸውን አንዱን ከ12ኛ ክፍል በኋላ ውጤት ስላልመጣለት ዲፕሎማ እንዲማር በክፍያ ነበር ያስተማሩት። ሁለቱን ሴት ልጆቻቸውንም ቢሆን እንዲሁ በአካባቢው የ11 እና 12ኛ ክፍል ትምህርት ስለማይሰጥ ወደ ደብረብረሃን በመላክ ቤት ተከራይተው ቀለብ እየላኩ ነው ያስተማሯቸው።
ይህም ፈታኝ ጊዜያቸው እንደነበር አይረሱትም። ምክንያቱም ለምግብ የሚሆናቸውን እህል መግዢያ ገንዘብ አገኘሁ ብለው እፎይ ሲሉ የቤት ኪራዩ ይደርሳል። ያንን ለመሙላት ደግሞ እጅጉን ይሰቃያሉ። ምክንያቱም ከዚህ ቀደም በነበረ አኗኗራቸው ቤት ያፈራውን ሰጥተው ያኖራሉ። ተጨማሪ ለቤት ብለው የሚያወጡት ነገር አልነበረም።
ልጆቹ ምንም የሚናገሩት ነገር ባይኖርም እርሳቸው ግን ከሌሎች ለምን ያንሳሉ በሚል ነበር ከሚችሉት በላይ የሚለፉት። እንደውም አንድ የራሳቸውን ሥራም ፈጥረው ነበር። ይህም አረቄ እያወጡ ጎን ለጎን የሰዎችን ጋቢ ይቋጩ እንደነበር አይረሱትም። የሚቋጭ ጋቢ ከለሌለ ደግሞ ለሰርግ የሚሆኑ መሰበወርቆችን በመስፋት ይሸጣሉ። በቃ ለእርሳቸው እረፍት አይታሰብም። ለልጆቻቸው እንቅልፋቸው ነጥፏል።
ለልጆቻቸው እጃቸው ነቅቷል። ለልጆቻቸው እግራቸው ነቃቃት አውጥቷል። ውርጭና ብርዱ ፊታቸውን ሳይቀር ሰነታትሮታል። ግን ይህም ቢሆን አንድም ቀን ከፍቷቸው እንደማያውቅ ይናገራሉ። ምክንያቱም ልጆቻቸው በዚያ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ሆነው ይረዷቸዋል።
አንድም ልጅ ዋልጌ ሆኖ ከተባለው ውጪ አያደርግም። በዚህም የሰፈሩ ሰው ሳይቀር በልጆቻቸው ያመሰግናቸዋል። ይህ ደግሞ የሁልጊዜ የደስታና የመልካም ተስፋ ስንቃቸው እንደነበር ይናገራሉ።
በተለይም በትምህርታቸው አስመስጋኝና የተሻሉ ሆነው ለቁምነገር መብቃታቸው እንኳን ለፋሁ ያስብላቸዋል። እናትነቴን በሚገባ እንደተወጣሁ የማየውም በመጣው ውጤት ነው ይላሉ።
ልጆቻቸውን በሥነምግባር በማሳደጋቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን በልጆቻቸውም ጭምር ሲመሰገኑ ሲያዩም ከዚህ በላይ ክፍያ ምን አለ ይላሉ። በእርግጥ እርሳቸው በልጆቻቸው ብቻ ሳይሆን ባልወለዷቸው ሰዎች ሳይቀር የሚመሰገኑ ናቸው። ምክንያቱም የእርሳቸው ልጆች ከሰላምታቸው በተረፈ ሰዎችን በመርዳት የሚያምኑና የሚያደርጉ በመሆናቸው ሰፈርተኛው ሁሉ ይመርቋቸዋል። ልጅማ የእርሳቸው ልጆች ይባልላቸዋልም።
እናትነት ለራስ ልጅ ብቻ መኖር አይደለም። ልጅ ለሚባለው ሁሉ መጨነቅና ከአለ ላይ ማድረግ እንደሆነ የሚያምኑት ወይዘሮ በቀለች፤ የሰፈር ልጆችን ሳይቀር እየተቆጡና እየረዱ አስተምረዋል። ብዙ ልጆችም እማዬ ይሏቸዋል። በቁጣቸው ብቻ አድገውና ቁምነገር ላይ ደርሰው ሲያገኟቸው ‹‹አንቺ ነሽ እኮ ለዚህ ያበቃሽኝ›› ይሏቸዋል።
ሰፈር ውስጥ አሁንም ቢሆን ገና የሶስትና የአራት ዓመት ልጅ ምንም እንኳን አዛውንት ቢሆኑም በአንቺታ መንፈስ ‹‹በቄ›› ነው እያለ የሚጠራቸው። ይህ ደግሞ ምን ያህል ቅርበትና ወዳጅነት እንዳላቸው በደንብ ያሳያል። አሁንም ቢሆን ለሌሎች ልጆች እንደመኖር የሚያስደስታቸው ነገር የለም።
‹‹ለራሷ የምትኖር እናት እናት ነች አልላትም። ልጇ እየተራበ እርሷ ልብሷን የምታሳምርም እንዲሁ። በአሁኑ ወቅት ብዙዎቹን ሳያቸው ይህንን አይነት ባህሪ አይባቸዋለሁ። ግን እናትነት ይህ አይደለም። እናትነት ጦም እያደሩ ልጆችን መመገብ ነው። የራስን ምቾት ለልጅ ነው። ሌሎች ምንም የማያውቁ ልጆችን ማገዝና ከሚያልሙት ላይ ለማድረስ መጣጣር ነው። ስለዚህ እናቶች ከእኔ ቢወስዱ የምለው ይህንን ባህሪዬን ነው›› ይላሉ።
ልጆች ከእናት ቅርበትን ይፈልጋሉ። ይህንን ከተሰጣቸው ደግሞ ከሚባሉት አይወጡም። ለዚህም ማሳያው የእኔ ልጆች ናቸው። አንድ እንጀራ ለአራት ከፍዬ ሰጥቻቸው አንድም ቀን ፊታቸውን አጥቁረውብኝ አያውቁም። ርቦኛልም አይሉም። ውጪ ወጥተው አሳፍረዋቸውና የተለየ ስሜት አሳይተውም አያውቁም።
ከዚያ ይልቅ ችግሬን አይተው እኔ እንዳይከፋኝ ነው የሚያጽናኑኝ። እናም እናቶች ልጆቻቸውን ሲደግፏቸው ልጆችም ያንኑ ምላሽ ይሰጣሉ። ስለዚህ ይህንን ቢያደርጉም ባይ ናቸው።
እንደውም ዘወትር አንድ ነገር ደጋግመው እንደሚናገሩ አጫውተውናል። ይህም ‹‹ በነበረብኝ ፈተና ላይ የልጆቼ ባህሪ የተበላሸ ቢሆን ኖሮ እሞት ነበር። ነገር ግን የተባረኩና በምፈልገው መልኩ የማዛቸው ልጆችን አምላክ ስለሰጠኝ አመሰግነዋለሁ። ሴት ሆኜ ብቻዬን እንዳሳድጋቸው መርቆልኛል። ›› የሚል ነው።
የትዳር ህይወት
ወይዘሮ በቀለች እድሜያቸው ገና ለአቅመ ሄዋን ሳይደርስ ነው በአካባቢው ባህል ልጅሽን ለልጄ በሚል ወደ ትዳር የገቡት። በተለይም የባላባት ልጅ በመሆናቸው ይሄ ባህል ነገራቸው ጠንክሮባቸዋል። ከአደገች በኋላ የማይመጥናትንና ዘሩ ያልታወቀ ሰው ታገባብናለች በሚል ፍራቻ ዘር ተቆጥሮ በ12 ዓመታቸው እንዲያገቡ ሆኑ። በእርግጥ ይህም ቢሆን ለእርሳቸው ከባድ ስለነበር በየጊዜው እየተጣሉ አባትና አያታቸው ጋር ይሄዱ ነበር።
ግን ያገባች ሴት አንድም ቀን በቤተሰቧ ቤት ማደር የለባትምና መላልሰው በሽማግሌ ጭምር እያስታረቁ ያስገቧቸዋል። ይህ የመረራቸው ወይዘሮ በቀለችም አባታቸው ጋር ሄደው ‹‹ ከአሁን በኋላ ከመለስከኝ ራሴን አጠፋለሁ›› አሉ። አባትም ፈርተው እነዋሪ የምትባል ከተማ ወሰዱዋቸውና ከዘመድ ዘንድ ሸሸጓቸው።
ከሁለት ዓመት ቆይታ በኋላ አሁንም ቢሆን ከትዳር የሚያስቀራቸው ነገር አልነበራቸውና በአባታቸው ግፊት ለሁለተኛው ለልጆቻቸው አባት ተዳሩ። መማር እፈልጋለሁ ቢሉም ቦታ የሰጣቸው አልነበረም።
ይልቁንም ‹‹ቆሞ ቀር ልትሆኚ ነው›› በማለት ልብስ በመስፋት የሚተዳደርና በቂ ሀብት ላላፈራ በባህሪው ግን ምስጉን ለሆነው የልጆቻቸው አባት የተዳሩት። ይህ ሲሆን ግን የአባት እንጂ የሌሎቹ ቤተሰቦች ፈቃድ አልነበረበትም። እንደውም ‹‹እንዴት ድሃ ታገባለች ፤ ዘሩ የማይታወቅ›› እያሉ ለዓመታት አኩርፈዋቸው እንደነበር ያስታውሳሉ።
ሰርቶ የማያልፍለት ማንም ሰው የለምና ጠንካራ ሰራተኞች በመሆናቸው ስማቸውን ዓመት በሞላው ጊዜ ውስጥ ቀየሩ። በከተማዋም አሉ ከሚባሉ ሀብታሞች ተርታ ተሰለፉ። ሁለት የልብስ ሱቆች፣ ቤትና ሦስት መኪኖች ኖራቸውም። በዚህ ጊዜ የሚያውቃቸውም የሚወዳቸውም በዛ። ቤተሰብ ሳይቀር መከታዬ ይላቸው ጀመር።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን መጥፎ አጋጣሚ ምቾትና ደስታቸውን ነጠቃቸው። በላብና በወዛቸው ያፈሩት ንብረት በአንድ ቀን ሌሊት ወደመ ። ዳግም ልፋት ውስጥ ገቡ። በመስራት ይህንንም ታሪክ መቀየር እንደሚቻል ያውቃሉና ታሪካቸውን ዳግም ለማደስ በባዶ ተነሱ። ብቻቸውን ጥረው ግረውም ልጆቻቸውን አስተማሩ። በተለይ በሁለቱም መንግስታት ሴት በመሆናቸው የገጠማቸው ፈተና መራር ጽዋ እንዲጎነጩ ያደረጋቸው እንደነበር ያስታውሳሉ።
የደርግ ስርዓት ማብቂያ አካባቢ የሆነው ሲያስታውሱ፤ አንዳንድ ወታደሮች ከሕግ ውጭ እየሆኑ ሕዝብን የሚያንገላቱበት በተለይም ወጣት ሴቶች ሰርቶ ለመብላት እንዳይችሉ የሚያደርጉበት ስለነበር እኔንም የገፈቱ ቀማሽ አድርገውኝ ነበር።
ገበያ ላይ የምሰፋውን ልብስ እንኳን ለመሸጥ ሁለት የገበያ ቀናትን በመጠቀም የቤተሰብ ሰዎችን በማቆም ነበር። አለበለዚያ ግን በጥፊ መላጋትና ሀብት ንብረትን መቀማት ይኖርበታል። ቤት ከተመለሱ በኋላም ቢሆን በር ክፈች በየጊዜው የሚደረግ ተግባር ነበር። እናም በፍራቻ ውስጥ ሆኖ የተኖረበት እንደነበር ይናገራሉ።
‹‹ባል የሌላት ሴት በዚያን ጊዜ የነበረባት ፈተና ከአላገባች ሴት አይለይም። እኩል ፈተናዎችን ትጋፈጣለች። በዚያ ላይ የልጆችን ጉሮሮ መድፈኑም ሌላው ከባድ ችግር ነበር። በቃ በዚህ ጊዜ የነበረውን ነገር ማውራት በራሱ የቃላት ብዛት እንኳን አይበቃውም።›› ይላሉ ጊዜውን ሲያስቡት።
የኢህአዴግን ጊዜ ሲያስታውሱትም የተለየ እንዳልነበረ ያስረዳሉ። ይህ ጊዜ ደግሞ በመመታትና በመነጠቅ ሳይሆን ሲፈሩና ሲፈተኑ የቆዩበት የልጆቼን ጉሮሮ ምን ሰርቼ ልሙላው የሚለው ነጻነት አለመስጠቱ ነው። ሴት በመሆናቸው ጾታዊ ትንኮሳው ይጠነክርባቸው ነበር። በተለይ ከሚሰሩት ሥራ ጋር ተያይዞ። አረቄና ጠላ ሻጭ ግድ መሳቅና መጫወት አለባት። ይህ ሲሆን ደግሞ ምሽቱ ለእርሳቸው ፈተና ይሆናል። ስለዚህም ነጻ ሆነው ለመስራት በጣም ተቸግረው እንደነበር አይረሱትም።
ምስጋና
‹‹መጀመሪያ አምላኬን እኔንም ልጆችንም ለዚህ ላበቃን አመሰግነዋለሁ። ከዚያም ልጆቼን አመሰግናቸዋለሁ። ከማንም አላሳነሱኝም። አክብረውኝ የፈለኩት ላይ ደርሰውልኛል። በመቀጠል ፊታቸውን ሳያጠቁሩብኝ የፈለገኝን እህል እየወሰድሁ ሸጬ እንድመልስላቸው ላገዙኝ የእነዋሪ ከተማ የእህል ነጋዴዎች ምስጋና ይድረስልኝ።
በተለይ ለቀለም አጉኔ አምላክ ውለታዋን ይክፈላት። ልጆቼ እንዳይከፋቸው በቻለው ሁሉ የደገፋቸው በቀለ ተስፋይም እንዲሁ። በቃ አመስግኜ የማልጨርሳቸው ብዙ ሰዎች ስላሉ ሁሉም ምስጋናና ከበሬታ ይግባቸው›› ብለዋል።
መልዕክት
የብዙ ትልልቅ ህልሞች መሳካት ጀርባ እናቶች ዋና ባለድርሻዎች ናቸው። አሁንም ቢሆን እንደ እኔ በትግል ውስጥ ሆነው ልጆችን የሚያሳድጉ ድሃ እናቶች በልጆቻቸው ውስጥ በሚያዩት ተስፋ ብርሃን ታግዘው እራሳቸውን በማበርታት ለቀጣዩ ትውልድ የወደፊት ተስፋ ጠንከረው መስራትና በልጆቸቸው እድል መሳካት ከፈጣሪ ጋር መታገል አለባቸው የመጀመሪያው መልዕክታቸው ነው።
ሌላው ያነሱት ነገር የእናቶች ጥንካሬ ለልጆች የልጆች ጥንካሬ ለእናቶች መሆናቸው በተግባር ከታየ የከበደ ችግር እንኳን ቢሆን በቀላሉ ለማለፍ አይከብድም። ሆኖም ከድሃ መወለድንና ከሃብታም መወለድን ተገን አድርጎ እያመካኙ በችግር ውስጥ የሚቆይ ከሆነ መቼም ቢሆን ፈተናዎች ማለፍ አይችሉም። ለዚህም እኔ ጥሩ ማሳያ ነኝ።
ስወለድ ከባላባት ልጅ። ስኖር ደግሞ ድሃ ከነበረው ባለቤቴ ጋር ሀብት ንብረቱ ተትረፍርፎ ነበር። ሆኖም ብር ነውና ብር ብሎ ሲጠፋም አልወደኩም። እናም ሰዎች ስላላቸው ብቻ መሞላቀቅ የለባቸውም። ሳይኖራቸውም ደስታቸውን ወደነእርሱ ለማምጣት መጣር አለባቸው። ለዚህ ደግሞ መሰረቱ ሥራ ነው።
አባቶቻችን እንደሚሉት እራስን በስራ መውለድ መቻል ነው ለቁም ነገር የሚያበቃውና ተስፋ መቁረጥ አይገባም። በችግር ውስጥ ያለ ነገ ብሩህ እንደሚሆን በማለም ከችግሩ ለመላቀቅ መሞከር ያስፈልጋል።
ሰዎች በሀብት ላይ ጥገኛ መሆን የለባቸው። ይልቁንም ሀብት ቢጠፋ ሀብት ይተካል ብለው ማመን አለባቸው። የማይተካው ነገር የውስጥ ሰላም እንደሆነ ሊያስቡ ይገባል። ምን ይሉኛልን ከውስጣቸው ሊያስወግዱት ያስፈልጋል።
በተለይም ሀብታም እንደሆኑ የሚያስቡ ሰዎች። ዝቅ ብሎ መስራት የበለጠውን እንደሚሰጥ ማሰብ ይገባል። ያ ካልሆነ ግን መቼም መቆዘም እንጂ ማደግ አይታሰብም። ውጤታማ መሆንም አይቻልም የመጨረሻ መልዕክታቸው ነው።
አዲስ ዘመን ጥር 30/2013