በዚያን ወቅት
ወቅቱ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ከፍተኛ የፖለቲካ ሽኩቻ የነበረበት ሲሆን፤ አንዱ ሥርዓት በሌላኛው ሥርዓት ሊተካ ‹‹ጎህ ሲቀድ›› የሚባል ድባብ ላይ ነው። በዚህም በዚያም ውጥንቅጡ የበዛበት ወቅት ነበር። አንዱ ከሀገር ሲሰደድ ሌላኛው አገሬን ጥዬ ወይ ፍንክች ያለበትም ጊዜ ነው። ይህ ወቅት ለኢትዮጵያ ምጥ የበዛበት ጊዜ ነበር። ወቅቱ የደርግ ሥርዓተ-መንግስት ሊወገድ፤ የኢህአዴግ ሥርዓት መሰረቱን ሊጥል ያንዣበበበት ወቅት ነው። ይህ ወቅት በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ የውስጥ እና የውጭ ተዋንያን እጃቸው የረዘመበት ነበር። እናም ይህን የፈተና ወቅት አቶ መሠረት መኮንንም በዓይን ብሌናቸው አይተውታል፤ የታሪኩ አካል ሆነው አልፈውበታል፤ አለፍ ሲልም ገፈቱንም ቀምሰውታል። በነበረው ጦርነት ጠላትን ዒላማ ያደረገ የጦር አውሮፕላን ጥቃት ሲሰነዝር እርሳቸው በብዙ ውጣ ውረድ ያፈሩት ሃብት ዶግ አመድ ሆኖባቸዋል። ዳሩ ግን ጥቂት እጃቸው ላይ ባለችው ቅሪት እና በውስጣቸው ባለው ያልተሟጠጠ ተስፋ ነገ የተሻለ ቀን ነው ከሚል እሳቤያቸው አላሰናከላቸውም፤ ሁሉን ነገር ‹‹ሀ›› ብሎ ከመጀመርም አላገዳቸውም። በውስጣቸው ያለመሸነፍ ስሜት ስለነበር ለችግር እጅ ከመስጠት ይልቅ በፅናት ታግለው ስኬትን ለመጎናጸፍ ታትረዋል።
make custom jerseys
custom baseball jerseys cheap
custom jerseys baseball
custom uniforms
custom hockey jerseys
custom volleyball jerseys
nba jersey customized
custom jerseys basketball
football jersey custom
china cheap jerseys custom
best custom jerseys
custom basketball jerseys
customize football jersey online
custom football jersey
customized baseball jerseys
custom jerseys
nba jersey customized
custom baseball jerseys
custom football
custom baseball jerseys
custom soccer jerseys
custom football jerseys
custom soccer uniforms
custom basketball uniforms
custom basketball jersey
custom football jersey
custom dodgers jersey
custom apparel
football jersey maker online
customized basketball
custom hockey jersey
custom jerseys near me
custom jerseys football
custom jerseys
custom jerseys nfl
nfl custom jersey
custom jerseys baseball
custom nfl jersey
custom design soccer jerseys online
cheap custom jerseys
customized baseball jerseys
እኚህ ሰው አቶ መሠረት መኮንን ናቸው። የተወለዱት በደቡብ ጎንደር ነው። አባታቸው ሊቀ ካህናት መኮንን ታዬ በኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የደቡብ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ገዥ ነበሩ። አያታቸው ቀኛ ዝማች ታዬ ደግሞ እጅግ በጣም ትልቅ የገበሬ ባለሃብት ነበሩ። እናታቸው እማሆይ ዘርፌ ደጉ ሽበሽ ደግሞ በወቅቱ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት አዛዥ የነበሩ ትልቅ ሰዎች የሚባሉ ከደጃዝማች ዘሮች ነው የተወለዱት። ታዲያ በእንዲህ ዓይነት ትልቅ ቤተሰብ ውስጥ የተወለዱት አቶ መሠረት- ለሀገራቸውም ትልቅ ውለታ፤ ትልቅ ሥራ ለመሥራት የታደሉ ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ‹‹ዓባይን በማንኪያ›› እንዲሉ ከብዙ በጥቂቱ የሕይወታቸውን ገፅታ እናውጋ።
ወደ ንግድ
ገና በለጋ ዕድሜያቸው ነበር ወደ ንግድ ዓለም የተቀላቀሉት። በ19 ዓመታቸው ወደ ቢዝነሱ ዓለም ሲገቡም ለመነሻ የሚሆን ገንዘብ የሚሰጣቸው ሰው አልጠፋም። ትምህርታቸውን ደቡብ ጎንደር መካነ እየሱስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ 12ኛ ክፍል ተማሩ። በ1980 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ በሀገሪቱ ጦርነት ስለነበርና ይህ ነው የሚባል አማራጭ ስላልነበራቸው ትምህርታቸውን ለጊዜው ገታ አድርገው ፊታቸውን ወደ ንግድ አዞሩ። ትምህርታቸውን እንዳቋረጡ ብዙ ነገሮችን ማሰብ ጀመሩ። ምንም እንኳ ጦርነቱ ያስከተለው ዳፋ የበዛ ቢሆንም እርሳቸው ከሁለት ያጣ ላለመሆን ወሰኑ። አንድም ከትምህርታቸው አሊያም ከንግዳቸው ለመሆንና የሕይወትን መስመር ለማሳመር መጣጣር ጀመሩ። በወቅቱ ከቅርብ ቤተሰባቸው 500 ብር ተቀብለው ወደ ሱዳን ጥራጥሬ መላክ ጀመሩ። ይህም ውጤታማ እያደረጋቸው መጣ። ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ደግሞ ጨው በማምጣት ወደ ጎንደር እና ባህርዳር አካባቢ መሸጥ ጀመሩ። በዚህ ንግድ ዓመታትን አስቆጠሩ፤ ደንበኞችንም አፈሩ፤ በርካታ ሰዎችንም ተዋወቁ።
በዓመታት ውስጥ ጥሪት አጠራቀሙ፤ ቀደም ሲል ተጋግሞ የነበረው ጦርነትም ረገበ። አገር እየተረጋጋች ስትመጣ እርሳቸውም ከጎንደር ራቅ ብለው መሄድ ጀመሩ። በወርሃ ነሐሴ 1983 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተሙ። በዚህም ብዙ የቢዝነስ አማራጮችን ማጥናት ጀመሩ፣ በአጋጣሚ ግን ወደ ቶጎ ጫሌ፣ ኬንያ፣ ሞያሌ፣ ጅቡቲ በመመላለስ ዕቃዎችን በመሸጥና በመለወጥ ቆዩ። በዚህ መንገድም ሃብት ማፍራት ጀመሩ። አቅማቸው እየደረጀ ሲሄድ በ1992 ዓ.ም የራሳቸውን ኩባንያ መሰረቱ። ህልማቸውን ሩቅ ስለነበር ሁሉንም ነገር በሂደት ማሳካት እንደሚችሉ ያምናሉ። በእርግጥ አንዳንድ ነገሮችን በድፍረት ሲወስኑ የሚሳለቅባቸውም አልጠፋም ነበር። ዳሩ ግን፤ ነገን ከአድማስ ማዶ አሻግረው ይመለከቱ ነበርና ህልማቸውን ወደ ተግባር ከመቀየር ያገዳቸው አንዳች ነገር አልነበረም።
ጥሩ አጋጣሚ
ይህ ወቅት ጉዞዋን አጠናቃ መልህቋን በሰላም ለማሳረፍ ከወጀቡ ሁሉ ተጋፍታ ከጠረፍ እንደደረሰች ከጉዞ ድካም ለማረፍ እንደቋመጠች መርከብና መርከበኛ ነበር የሆነላቸው። ስኬታማነት በራቸውን አንኳኩቶ የመጣ ያክል ተሰማቸው። አንዳንድ ጊዜ ሕይወት በራሷ ዛቢያ መልካም አጋጣሚዎችን ይዛ ከተፍ ትላለች። ከጎንደር ብዙ ራቅ ብለው ያልኖሩት አቶ መሰረት ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ ብዙ ልምድ እና ዕውቀት እየቀሰሙ መጡ። 1992 ዓ.ም ጀምረው በንግድ ላይ እየተንቀሳቀሱ እያሉ በመሃል የኢትዮጵያን ባለሃብቶች ምርታቸውንና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ በሳውዲ አረቢያ ትልቅ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን አዘጋጁ። ይህ አጋጣሚ ለአቶ መሰረት- የሃብት መሰረት በትልቁ የጣሉበት መልካም አጋጣሚ ነበር። ሜድሮክ ኢትዮጵያ፣ ኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ፣ አምቦ ውሃ፣ አያት መኖሪያ ቤቶች፣ የኢትዮጵያ ማዕድንና ኮርፖሬሽንና ሌሎችም በኤግዚብሽኑ ተሳታፊ ነበሩ። በዚህም ሥራቸውም በሳውዲ አረቢያ ልዩ ተሸላሚ ሆኑ። እነዚህ ድርጅቶችም በዚያን ጊዜ መነሻ ሆኗቸው በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸው ናቸው። ‹‹ለዚህም መሰረት የሆንኳቸው እኔ ነኝ›› ይላሉ አቶ መሰረት። በመቀጠልም ከሌሎች ባለሃብቶች ጋር በመቀናጀት ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ የሥጋ ውጤቶችና ቅመማ ቅመም ወደ ውጭ መላኩን ተያያዙት።
አሁን
በአሁኑ ወቅት በኢንዱስትሪ፣ በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ፣ በሪል ስቴት ፕሮጀክት፣ በመኪና ኪራይ፣ በህንፃ ሽያጭና ኪራይ፣ በአስመጭነትና ላኪነት የተሰማሩ አገር በቀል ድርጅት ባለቤት ሲሆኑ በልፋታቸው የሚኮሩ ሀገር ወዳድ ባለሃብት ናቸው። 15 የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች፣ በአዲስ አበባ በኩባንያው ሥም የተመዘገቡ ሦስት ግዙፍ ህንፃዎች ባለቤትም ሆነዋል። በማኑፋክቸሪንግ በአዲስ አበባ ያስገነቡትን ቤዝ ኢትዮጵያ ሆቴል አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ ፋብሪካ በ130 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያቋቋሙ ሲሆን 230 ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ሆነዋል። ቤዝ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በአሥር የቱሪስት መዳረሻዎች አካባቢ እያንዳንዳቸው ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የቱሪስት መዝናኛና የባህል ማዕከላት በመገንባት አገሪቱ ያላትን እምቅ የቱሪዝም ሃብት ለመጠቀም ወስነው ወደ ስራ ገብተዋል። የሆቴል ኢንዱስትሪውን ቤዝ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ብለው ቦሌ አዲስ አበባ የጀመሩ ሲሆን፤ ይህንንም መሰረት አስይዘው ወደ ሌሎች አካባቢዎች መንቀሳቀሱን መርጠዋል።
አቶ መሰረት የኢንቨስትመንት ዘርፋቸውን በተወሰኑ ሥራዎች ብቻ ላይ አልገደቡም። አንዱ ሥራቸው ለሌላው መጋቢ እንዲሆን በሚገባ አስበውበታል፤ ወደ ተግባርም የሚቀየር አድርገውታል። የሆቴል ኢንዱስትሪው ሲስፋፋ በዚያው ልክ ደግሞ የትራንስፖርቱንም አቅርቦት እና ምቾትን ተናቦ እንዲሰራ መላ ዘይደዋል። ለዚህም ሲባል የቤዝ ኢንተርናሽናል ቱር ኤንድ ትራቭል ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ጭምር ናቸው።
ጎንደርን፣ አርባ ምንጭንና ኮንሶን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገነቡት እነዚህ ማዕከላት ከኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በስተቀር ሙሉ በሙሉ አካባቢው ላይ ባሉ ቁሳቁስ የሚሠሩ ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው ከ50 በላይ የመኝታ ክፍሎች፣ ዘመናዊና ባህላዊ ሬስቶራንቶች፣ የየክልሉን ባህል የሚያሳዩ ሙዚቃ የሚቀርብበት፣ ጎብኚዎች ባህላዊ ምግብና መጠጦች የሚታደሙባቸው አዳራሾች፣ አነስተኛ ሙዚየሞች፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችና ሌሎችም አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው። በእነዚህ የቱሪስት የመዳረሻ ቦታዎች ደረጃውን የጠበቀ የምግብ፣ የመኝታ፣ የመዝናኛ ሥፍራ እንዲሁም ጠቅለል አድርጎ የአካባቢውን ባህልና ወግ ለማሳየት በማሰብ ጭምር የተወጠኑ ናቸው።
500 ብር የተጀመረው ንግድ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የፕሮጀክት ካፒታላቸው 10ነጥብ5 ቢሊዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን ሁሉም ፕሮጀክታቸው ወደ ተግባር ገብቷል። በዚህ መሰረት ለብዙ ዜጎቻችን ከፍተኛ የሥራ ዕድል የፈጠሩ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው። መንግሥት በሚጠይቃቸው የልማትና የድጋፍ ጥያቄዎችም ቀድመው የሚገኙ አገራቸውን እና ዜጋቸውን የሚወዱ ኢትዮጵያዊ ናቸው። በዚህም በርካታ የምስክር ወረቀቶች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና ከሌሎች በርካታ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተበርክቶላቸዋል። በቅርቡም መታሰቢያነቱ ለእናታቸው እማሆይ ዘርፌ ደጉ ሽበሽ እንዲሆን በአማራ ክልል የመካነ እየሱስ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማስገንባት ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። ሆስፒታሉ ለእናቶችና ሕፃናት ህክምናም ይውላል።
ዘመናዊ መንደር
አቶ መሠረት ለአዲስ አበባ ከተማ አቅሜ የፈቀደውን አንድ ነገር ይዤ መጥቻለሁ ይላሉ። በአሁኑ ወቅት በሰፊው የገቡበት የሪል ስቴት ልማት ከፍተኛ የሥራ ዕድል የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ ትልቅ የውጭ ምንዛሪ ገቢን የሚያስገኝ ነው። ዲያስፖራዎችንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከባንክ ጋር በማስተሳሰር የቤት ባለቤት ይሆናሉ። ለዚህም ሥራ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 8ነጥብ5 ቢሊዮን ብር ዘመናዊ መንደር ግንባታ ጀምረዋል። በግንባታው 10 ባለ 12 ወለል ህንጻዎች፣ 90 ባለ ሁለት ወለል ቪላዎችና ዘመናዊ ቤቶች፣ ሲኒማ እና ሞል ያካተተ ነው። በአጠቃላይ ይህ ግንባታም ለ2ሺ300 ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል ይላሉ።
አገር ለማሳደግ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተደጋጋሚ ስለሀገሪቱ ዕድገት፣ ቱሪዝምና ምጣኔ ሃብት ዕድገት ይመክራሉ፤ በተግባርም ያሳያሉ። ለአብነት ጎርጎራ፣ እንጦጦ ፓርክንና ሌሎች ፕሮጀክቶችን እየሰሩ ነው። ባለሃብቶች ከዚህ በበለጠ መሥራት አለብን። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ ቴክኖሎጂና ሌሎች መስኮች እያደረጉት ያለው ጥረት በጣም የሚደነቅ ነው። የእርሳቸውን ራዕይና ተልዕኮ ከጎናቸው ሆነን ብናግዛቸው ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ማማ መውሰድ በጣም ቀላል ይሆናል። እኛ እንደ አንድ ድርጅት የኢትዮጵያን ቱሪዝም ለማሳደግ በስፋት እየሰራን ነው ይላሉ አቶ መሰረት። አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ሳውድ አረቢያ፣ አውስትራሊያ፣ ዱባይ እና ሌሎች ሀገራትም የቢዝነስ አጋር እየፈጠርን ነው።
በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በክልል ከተሞችም ከፍተኛ የቤት እጥረት በመኖሩ ወደ ክልልም ለመግባት ወስነን ከሥራና ከተማ ልማት ሚኒስትርና ከክልሎች ጋር ተነጋግረናል። በዚህም በቀጣይ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ደቡብ፣ ድሬዳዋ ተጋጣጣሚ ቤቶችን ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፤ ለሥራቸው መቀናትም ከቱርክ ካምፓኒዎች ጋር መነጋጋራቸውን ይገልፃሉ። በመሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻቸውን ከሚለፉ ቢያንስ ትንሽ ማገዝ ይጠበቅብናል የሚል መልዕክትም አላቸው።
ሰብዓዊነት
አቶ መሰረት በበርካታ ሰብዓዊ ድጋፎች ላይም እየተሳተፉ መሆኑን ይናገራሉ። ካለው ሃብት በላይ ትልቅ ተስፋ እና ደስታ መስጠት ነው የሚል እምነት አላቸው። ለአቅመ ደካሞች መስጠት ያስደስታል። ምንም የማይሰሩት እናቶችና አባቶች ተስፋቸው እኛ ነን። ይህችን ሀገር ያቆዩ ሰዎች ሲጎሳቆሉ ማየት ያማል›› ይላሉ። ‹‹እኔ አንድ የሚሰማኝ ነገር ሃብት የሚፈጠረው ለዜጋና ለሀገር ለግል አይደለም የሚሉት አቶ መሠረት፤ በሀገሪቱ ብዙ ዜጎች ሥራ አልባ ናቸው። በዚህ ወቅት ደግሞ እንደ ባለሃብት የሥራ ዕድል መፍጠር አለብኝ። እኔ ያለኝን ሃብት ተጠቅሜ የሥራ ዕድል መፍጠር ግዴታዬ ነው። ሥራ የፈጠርኩለት ዜጋ ልጆቹን፣ እናቱን፣ አባቱን ወገኑን ሲረዳ ማየት ከምበላውና ከምጠጣው በላይ ያስደስተኛል›› ይላሉ።
‹‹እኔ በቅርቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባቀረብልኝ ጥሪ መሰረት፤ የድሃ ድሃ ቤቶችን ሰርቻለሁ። በአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ባለሃብቶች ኮሚቴ ሆነን 180 ቤቶች ገንብተናል። ለድሃ ድሃ አራት የዳቦ ፋብሪካዎች በ87 ሚሊዮን ብር አቋቁመናል። በአጠቃላይ 210 ሚሊዮን ብር አሰባስበን ወጪ አድርገናል። ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ጋር በመዋዋል በቀን 30ሺ ዜጎች ዳቦ ያገኛሉ። የሸገር ዳቦ ሱቆችን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኙ 13ቱም ወረዳዎች ገንብተናል። በ90 ቀን ሰው ተኮር ፕሮጀክት ባለሃብቶችን በማስተባበር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየሠራን ነው›› ይላሉ።
ድርጅታቸውን ደግሞ በ10 ሚሊዮን ብር የቱሉ ዲምቱ አደባባይን እጅግ ዘመናዊ በሆነ ዲዛይን ገንብቶ ምረቃ ተከናውኗል። እኔ አሁን ያለሁበትን ደረጃ እግዚአብሔር ስለሰጠኝ እና ቤተሰቤ ሲደሰት ሌላው መብራት ላይ ቆሞ ሲለምን ውስጤን ይነካኛል። ሰው ለምን ይለምናል? ሥራ ቢኖረው፤ አቅመ ደካማ ባይሆን ወይንም ወላጅ አልባ ባይሆን አይለምንም። እነዚህን መርዳት ከደስታ በላይ ነው። እኔ ለአንድ ድሃ ስሰጥ መጀመሪያ ጥሪውን የሚያቀርበው፣ የሚያመሰግነውና ደውል የሚደውለው ለፈጣሪው ነው። ይህ ደግሞ በዕምነት ዓይን ትልቅ መልዕክት አለው። መስጠት በረከት ነው፣ በራሱ ዕድል ነው፤ ፀጋ ነው። ሃብት ሰብስበን መጨረሻ ጥለው ነው እንሄዳለን። ግን ለሀገር፣ ለወገን፣ ለዜጋ ሰጥቶ መሄድ መልካም ነው።
ፈተናዎች
እኚህ ግለሰብ እነዚህን ስኬቶች ለመጎናጸፍ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፈዋል። በተለያየ ወቅቶች በንግድ ሥራቸው ላይ ያልጠበቁት እክል አጋጥሟቸው ወደ ተስፋ መቁረጥ ተቃርበዋል። ስደትን ተመኝተው ያውቃሉ። ወዲህ ደግሞ በአገሬ ሰርቼ ችግሮችን በሙሉ አሸንፋለሁ ብለው በልበ ምሉዕነት ተነስተው ችግርን በሥራ ድል ነስተዋል። በአሁኑ ወቅት በክልሎች ተንቀሳቅሰው ለመስራት በሰፊ ውጥን ቢኖራቸው አልፎ አልፎ የሚስተዋለው የፀጥታ ችግር ያሳስባቸዋል። የውጭ ምንዛሪ እጥረትም ሌላኛው ፈተና ነው።
በአንዳንድ የሙያ ዘርፎች ደግሞ ብቁ ባለሙያ አለመገኘቱ ያሳስባቸዋል። በተለይም 10 ቢሊዮን ብር በሚጠጋ ካፒታል የሚገነባውን ሪል እስቴት ለመገንባት ከአቶ መሰረት ድርጅት ጋር ውል የገባው የቻይና ኩባንያ ሲሆን፤ ይህን ሊገነባ የሚችል ሀገር በቀል ኩባንያ አለመፈጠሩ ምቾት አልሰጣቸውም። በፍጥነት ሥራዎችን አጠናቀው የሚያስረክቡ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ አለመበራከታቸው ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ባለሃብቶችም ጭምር ፈተና ነው ይላሉ። በሀገር ውስጥ መቅረት የሚገባው ሃብትም ሌሎች እንዲጠቀሙበት በር እየከፈትን ነው የሚል እምነት አላቸው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉ ነገር የተመቻቸ ነው፤ ግን መሥራት አልቻልንም የሚሉት አቶ መሰረት፤ አገሪቱ ተስማሚ የአየር ንብረት፣ ማዕድን፣ ተፈጥሮ ሃብት፣ እንስሳት ሃብት፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪ፣ ኮንስትራክሽን፣ ሪል እስቴትና ሌላውም ዘርፍ ለመስራት በጣም ብዙ ዕድል አለ። ሆኖም የፖለቲካው ውጥንቅጥና የነገሮች አለመረጋጋት ፈተና ነው። ጠንካራ የሥራ ባህል አለመፈጠሩም አንድ አገር ጉዳት ነው። ከምንም በላይ ደግሞ በርካታ ባለሃብቶችና አልሚዎች የሚያቀርቡት ጥያቄ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሲሆን፤ ይህን ፈተና ለዘመናት መሻገር አለመቻል የባለሃብቶችን እንቅስቃሴ የሚገዳደር ነው ባይ ናቸው። እንደ አገር የተረጋጋ ገበያ ሥርዓት መፍጠር አለመቻልም ሌላኛው ፈተና ነው። በአጠቃላይ እነዚህ ነገሮች ተደማምረው ብዙ መሥራት እየቻልን፤ ብዙ ርቀት መጓዝ ሲገባን እያገደን ነው ይላሉ። ሆኖም ችግር አለ ብሎ ከማውራት መፍትሄ ለማምጣት መትጋት የችግሮቹ ሁሉ መቋጫ ነው።
እቅዶች
አቶ መሠረት አሁንም ቢሆን ሥራ ገና ምን ተሰርቶ የሚል ነው ሐሳባቸው። ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ ያልተነካ ሃብት አላት። ከዘመናዊ አፓርታማዎች በተጨማሪ ከ5 እስከ 10 ዓመታት ውስጥ ከመንግስት ጋር በመሆን አንድ ሚሊዮን አነስተኛ እና ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው። ለዚህም ሁሉንም ግብዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ማምረት እንደሚቻልና ለዚህም ይረዳ ዘንድ ቴክኖሎጂ የማስገባት ሥራ መጀመራቸውን ይገልጻሉ።
በአገልግሎት ዘርፍ ብዙ ሥራዎችን ያሰቡ ቢሆንም፤ በአሥር የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ መዝናኛና የባህል ማዕከል መገንባት ቀዳሚው ሥራቸው ነው። ቤዝ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በአሥር የቱሪስት መዳረሻዎች አካባቢ እያንዳንዳቸው ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የቱሪስት መዝናኛና የባህል ማዕከላት የመገንባት ውጥን አለው። በተለይም ኤርታሌ፣ ሶፉመር፣ ጢስ ዓባይ፣ አክሱም፣ ላሊበላ፣ ዳሎል አፋር፣ አርባ ምንጭ፣ ኮንሶ፣ የቱሪስት መዳረሻዎች በዚህ ፕሮጀክት ታቅፈዋል።
በቱሪዝም ዘርፍ ከኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ በብዙ እጥፍ የሚበልጥ አቅም ያላት ኢትዮጵያ የምታገኘው ገቢ ግን የእነዚህ ሀገራት አምስት በመቶ አይሞላም የሚሉት አቶ መሠረት፤ በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎች ሰላማቸው የተጠበቀ ባለመሆኑና ባለሃብቱም በዚህ ላይ ባለመስራቱም ሀገራችን አልተጠቀመችም የሚል ቁጭት አላቸው። ታዲያ በቀጣይ እነዚህ የመዳረሻ ቦታዎች የሚገነቡት የመዝናኛና የባህል ማዕከል ይህን ታሳቢ በማድረግ ነው።
በተለያዩ አካባቢዎች የሚገነቡት እነዚህ ማዕከላት ከጥቂት ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በስተቀር ሙሉ በሙሉ አካባቢው ላይ ባሉ ባህላዊ ቁሳቁስ የሚሠሩ ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው ከ50 በላይ የመኝታ ክፍሎች፣ ዘመናዊና ባህላዊ ሬስቶራንቶች፣ የየክልሉን ባህል የሚያሳዩ ሙዚቃ የሚቀርብበት፣ ጎብኚዎች ባህላዊ ምግብና መጠጦች የሚታደሙባቸው አዳራሾች፣ አነስተኛ ሙዚየሞች፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችና ሌሎችም ዘመናዊ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው። የገንዘብ አቅርቦት ከባንክ የተገኘ ሲሆን፣ አሁን ያለው የፀጥታ ችግር ከተስተካከለ ግንባታውን በቀጥታ እንደሚጀምሩም ነው አቶ መሠረት የሚናገሩት።
ሰዎች ምን ይላሉ?
ሰዎች ስለ አቶ መሰረት እንዲህ ይላሉ። ብዙ ነገሮችን ቀለል አድርገው የሚመለከቱ እና ስሜታቸው በቁጥብ አኳኋን የሚገልጹ ናቸው። ብዙ መናገር ልምድ የሌላቸው፤ ከተናገሩም ፊት ለፊት እውነታውን ፍርጥ አድርገው የሚናገሩ ናቸው። ሲበዛ ብዙ ነገሮችንም የሚደፍሩ ስለመሆናቸው ይመሰክሩላቸዋል። በተለይም አዳዲስ የቢዝነስ ሥራዎችን ለመጀመር የማያቅማሙ ግን በዚያ ላይ የባለሙያ ምክርን የሚያስቀድሙ ስለመሆናቸውም የግል አማካሪያቸው ይመሰክርላቸዋል። ከዚያ በተረፈ ለሚያወጧት ወጪ በሙሉ በስሌት የሚንቀሳቀሱ ሰው ናቸው። ሌላው ቀርቶ ከግል ሆቴላቸው ለራሳቸው ሲጠቀሙም ሆነ ድንገት ሰው ቢጋብዙ እንኳን እንደማንኛውም ተጠቃሚ ሂሳብ ከፍለው የሚጠቀሙ ሲሆን፤ ይህም አንድ ድርጅት ጤናማ አካሄድ እንዲኖረው እና ሕግና ሥርዓት እንዲገዛው ያደረጋል የሚል እምነት አላቸው። ከልጆቻቸውና ከመላ ቤተሰቦቻቸው ጋርም ያላቸው ግንኙነት ለሌሎች አርዓያ ስለመሆኑም ይመሰክሩላቸዋል። ስለድርጅታቸው ቀጣይ ዕጣ ፋንታ ላይም በጋራ ይመክራሉ፤ ሀሳብም ያዋጣሉ።
መልዕክት
ባለሃብት ነኝ የሚል ሰው፤ ሀገሩን፣ መንግስትን፣ ሕዝብን፣ ሃይማኖቱን የሚያከብርና ከሀገሩ የማይሰርቅ መሆን አለበት። ታሪክን ለማሸጋገር መጀመሪያ ለራስ ንጹህ መሆን ያስፈልጋል። ጥሩ ዜጋ ለመፍጠር መጀመሪያ ንጹህ መሆን ይገባል። ራዕያቻን ሰፊ መሆን አለበት፤ ሀገራችን ለሁላችንም ሁሉንም መሆን ትችላለች። ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነትና ለውጥ ያስፈልጋል። ሀገራችን የተፈጠርንባት፣ ያደግንባትና የምንኖርባት ስለሆነ ልንጠብቃት ይገባል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በፓርላማ ስለሙስና የተናገሩት በጣም ትክክል ነው። እኔ የሚታየኝ ይህችን ሀገር አምስት ቡድኖች እያጠቋት ነው። ማፊያ ባለስልጣናት፣ ማፊያ አክቲቪስቶች፣ ማፊያ ባለሃብቶች፣ ማፊያ ፖለቲከኞች እና በሃይማኖት ካባ ተደብቀው የሚንቀሳቀሱ ማፊያ ሃይማኖተኞች ሀገሪቱን በከፍተኛ ደረጃ እያጠቁ እና ሕዝብን ለችግር እየዳረጉ ነው።
ሁልጊዜም የምናገረው ኢትዮጵያ ትልቅና ሃብታም ሀገር ናት። በሁሉም ዘርፍ ተዝቆ የማያለቅ ሃብት አላት፤ ግን አልተጠቀመችበትም። እንድትጠቀም የምናደርገው ደግሞ በዚህች ምድር የተፈጠረ ዜጋ ጥላቻን በማስወገድ፣ በመተባበር፣ በቅንነትና በመተሳሰብ እና በመተባበር ነው። ፍቅር፣ አንድነትና ሰላም ካለን ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር ናት፤ ከሌሎች ዓለማት ሁሉ በበለጠ ትልቅና የተለየች ናት። ችግሩ የእኛ የዜጎቿ እንጂ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እንከን የለባትም። በአጭር ጊዜ ትልቅ ለውጥ የምታመጣ ሀገር ናት። ማንም ባለሃብት፣ ዜጋ ሆነ ባለስልጣን ሀገሩን መስረቅ የለበትም። ይህን የሚያደርግ ከራሱ እንደሰረቀ ማሰብ አለበት።
ክፍለዮሐንስ አንበርብር
አዲስ ዘመን ሰኔ 25/2015