በህንፃ ዲዛይን ዘርፍ የቴክኖሎጂ ለውጦች እየታዩ ናቸው፤ ይህም በአንድ ጊዜ የመጣ ለውጥ አይደለም።በዘርፉ ለውጥ ለማምጣት የፕሮጀክት ምርምሮች፣ የሙከራና የተለያዩ የህንፃ ጥበብ የሚያስተምሩ ዩኒቨርሲቲዎች በመክፈት ረገድ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዲጅታል ምርቶች ወደ ግንባታው ዘርፍ ከገቡ በኋላ የህንፃ ዲዛይኖች በከፍተኛ ሁኔታ ተለውጠዋል።ቴክኖሎጂ በሥነ-ህንፃ ልምድ ውስጥ እስካሁን ያመጣውን ውጤት ለመረዳት በዘርፉ ያለውን እንቅስቃሴ መዳሰስ ይገባል። በግንባታ ውስጥ የሚስተዋሉ የተለያዩ ሂደቶችን፣ ዓይነቶችን እና በእነሱ ላይ የሚሠሩ ፕሮጀክቶችን ዲጂታል የማምረት አቅም የመገንባት ሁኔታን እስቲ እንመልከት።
የዲጅታል ምርቶች አይነት
ዲጅታል ምርቶች በተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ለውጥ ውስጥ የሚያልፉና በኮምፒውተር ቁጥጥር የሚደረግባቸው ናቸው።በአሁኑ ወቅት የቴክኖሎጂ ምርቶች እየተስፋፉ መጥተዋል።የቴክኖሎጂው መስፋፋት ሦስት አይነት መንገዶች አሉት።እነሱም ተጨማሪ የማኑፋክቸሪንግ፣ ተቀናሽ የማኑፋክቸሪንግ እና ማናቸውንም ዓይነት የሮቦት ሥራ በመባል ይጠቀሳሉ።
ተጨማሪ ማኑፋክቸሪንግ
በተለምዶ 3D ማተሚያ ተብሎ የሚጠራው ተጨማሪ ማምረቻ የንብርብር ምርቶችን ያካትታል።3ዲ ቴክኖሎጂ በእ.ኤ.አ. 1983 በአልትራቫዮሌት ጨረርን ወደ ፎቶፖሊመር በማሸጋገር ወደ ጠንካራ ፕላስቲክ የሚቀየር ስቴሪዮ ሊብራግራምን በመጠቀም ጥቅም ላይ ዋለ።አሁንም ብዙ ሌሎች ሂደቶች እየመጡ ይገኛሉ።በዚህም ቴክኖሎጂዎች በከፍተኛ ፍጥነት ይለዋወጣሉ። ብረቶችን፣ ብርጭቆዎችን፣ ሸክላዎችን፣ የናኖ ውህዶችን አልፎ ተርፎም የሰውን ሕብረ ሕዋሳት ለመተካት ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ። አስተማማኝ ባለ ብዙ ቁጥር 3 ዲ ማተሚያዎችን ለማዘጋጀትም ምርምር እየተካሄደ ነው።
ተቀናሽ ማኑፋክቸሪንግ
በተቀናሽ ማኑፋክቸሪንግ ቁሳቁስ ከጠጣር ግድግዳ መሰል ነገር ይቀረፃሉ።የሲ ኤን ሲ ወፍጮ በጣም የተለመደ ሂደት ነው።የሲ ኤን ሲ ወፍጮዎች የመጡበት አጋጣሚ የሮቦቲክ ክንዶች የመጡበት ወቅት እንደሆነ ይገለፃል፤ በዚህ ምክንያትም ተፈላጊነታቸው ከፍ እያለ መጥቷል።በዚህም በግንባታው ዘርፍ ላይ የቴክኖሎጂው ችሎታ ይበልጥ እየጨመረ ይሄዳል። ሌሰር መቁረጫ እና ሙቅ ሽቦ፣ መደበኛ የሞዴል መሥሪያ ቴክኒኮች እንዲሁ በዚህ ንዑስ ማምረቻ ምድብ ውስጥ ይካተታሉ።
ማንኛውም ዓይነት የሮቦት ሥራ
ሦስተኛው ምድብ ማንኛውም ዓይነት የሮቦቲክ ሥራ ነው።ይህም እንደ ማጠፍና ማሸት ያሉትን ማንኛቸውንም የዲጂታል ማምረቻ አይነቶችን ይካትታል።ከትክክለኛ መሣሪያዎች ጋር የታገዙ ሮቦቶች በቀጣይነት ለተለያዩ ሥራዎች ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉባቸው ዕድሎች እየሰፉ መጥተዋል።ኤም አይ ቲ የፋይበር ሮቦቶች ፕሮጀክት፣ የጥቃቅን ሮቦት ማምረቻ ፋብሪካዎች እና መዋቅራዊ ንጥረ ነገሮች በዲጂታል ዲዛይንነት ይጠቀሳሉ።ምርምሩ ጥቅም የማይሰጡ የዲጅታል ምርቶችን በማስወገድ በጥናት ላይ የተመሠረተ ምርት ላይ ያተኮራል።
የሥነ ሕንፃ ግንባታ መተግበሪያዎች
ቤት ወይም ድልድይ ሊሠሩ የሚችሉ እንደ 3ዲ ማተሚያዎች ያሉ አንዳንድ አስፈላጊ ቴክኖሎጂዎች ከመጡ በኋላ የቴክኖሎጂው ሥነ-ጥበባዊ ትግበራዎች ከሚጠበቀው በላይ እየጨመሩ መጥተዋል። በዚህም ምክንያት የዲጂታል ምርቶች ቀስ በቀስ እያደጉ መጥተዋል። የዲጅታል ምርቶች በግንባታው ዘርፍ እያመጡ ካለው ለውጥ የተወሰኑትን እንመልከት።
የግንባታ ሂደቶች የሚከናውኑበት ራስ ሰር ሮቦት በማምረት
በኢንዱስትሪ ማምረቻ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ቀድሞውኑ ተቀባይነት ያገኘው ዲጂታል ምርት ከሰው ፍጥነት በሦስት እጥፍ ሊሠራ የሚችል ሮቦት ማለትም ከፊል ራስ-ሰር ማሽን እንዲመረት ማድረጉ ነው።ራስ ሰር ቴክኖሎጂዎች ለግንባታ ሂደቶችና ለአውቶማቲክ ግንባታ ትልቅ አቅም አላቸው።ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ካደረጉት መካከል ኢት ዙሪክ ራስ ሰር ኮንስትራክሽን የእንጨት ፍሬሞችን መቁረጥ፣ ቀዳዳዎችን መብሳት እና ሌሎች ሥራዎች በሮቦት እንዲሠሩ ማደረጉ ነው።
አዳዲስ ቁሳቁስን በማዘጋጀት
በግንባታ ቁሳቁስ የፈጠራ ሥራ ውስጥ ሌላ አስደሳች መሻሻል መደረግ እንዳለበት ይታመናል።የኤም አይ ቲ የድርድር ቡድን ያንን ለማሳካት እየጣረ ይገኛል።እንደ ኮንክሪት ያሉ አንዳንድ የተለመዱ የግንባታ ቁሳቁስ በጣም ከፍተኛ የካርቦን ልቀት ስላላቸው እነሱን የመቀየር ምርምር በእጅጉ ያስፈልጋል።ሰፋ ያለ የቁስ ልማት እድገት ለምሳሌ የኔሊ ኦስማን እና የኤም አይ ቲ የምርምር ፕሮጀክት ለውጥ ለማምጣት እየሠሩ ነው። የዲዛይኑ ባለሙያዎች ሴሉሴ፣ ቺቶሳን፣ ቴስቲን እና ውሃን እንዲሁም በተፈጥሮ ውስጥ የሚገኙትን ሁሉንም ንጥረ ነገሮች እና ከባዮአካላዊ እና አካባቢያዊ ተስማሚ የሆኑ ቁሳቁስን በመጠቀም የተወሰኑ ሜካኒካል እና ኦፕቲካል ዕቃዎች እንዲመረቱ ጥናት እያደረጉ ናቸው።
የዕቃዎችን አጠቃቀም ምቹ በማድረግ
ዲጂታል ምርቶች ለተለያዩ መዋቅሮች እና የዲዛይኖች ቁሳቁስ የበለጠ ቀልጣፋ አጠቃቀም ይሰጣሉ።በኢት ዙሪክ የተገነባው ስማርት ስላቭ በከፍተኛ ደረጃ የተሻሻለ እና ትክክለኛ የዲዛይን ምርት ሂደትን ያሳያል። የኮንክሪት ሰሌዳው የተሠራው በ3ዲ የታተመ መዋቅሮችን በመጠቀም ነው።ይህ መዋቅር እንዲሠራ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁስ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል።ፕሮጀክቱ ለተለያዩ የሕንፃ አካላት የሚተገበሩ አምስት የምርት ዘዴዎችን የያዘ ሲሆን፣ በዲጂታል ምርት ሥነ-ሕንፃን እንዴት ሊለውጥ እንደሚችል ያሳየ ሰፊ የምርምር ጥረት ውጤት ነው።
ለአዳዲስ ምርቶች በር መክፈት
እንደማንኛውም የግንባታ ሂደት ዲጂታል ምርት ለአዳዲስ ሀሳቦች ዕድል ይሰጣል።የአንድ አካል ውስብስብ ጂኦሜትሪክ ሥራ ለዲጂታል ማምረቻ አያስፈልግም።ስለሆነም የተወሳሰቡ ቅርፆችን በማጣመር ዲዛይኖች እንዲፈጠሩ እየተደረገ ይገኛል። ለህንፃ የመጨረሻውን ውበት ለማምጣትና የቅርፃ ቅርፅ ሥራውን ለመፍጠር የሚያግዝ መሣሪያ የፈጠረው ግሬግ ሊንን በህንፃ ውስጥ የዲጂታል ፕላስቲክ ማምረት ተመራማሪ ፕሮፌሰር ነው።ሌላው የዲጂታል አፈጣጠር ሁለገብነት እና ውበት የመፍጠር ችሎታ ሲሆን፣ ለምሳሌ የኮንክሪት የኮሪዮግራፊ ፕሮጀክት አንዱ ነው።ለእዚህም በኢት ዙሪክ የተገነቡት የኮንክሪት ቋሚዎች እንዲሁም የመሬት ንጣፎች አንድ ማሳያዎች ናቸው።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 28/2012
መርድ ክፍሉ