የተጋቡ ሰሞን ስለፍቅራቸው ብዙ ተወራ።በመዋደዳቸው የሚያስቀኑ፣ በጥምረታቸው የሚያስደምሙ በመግባባታቸው የሚገርሙ ባልና ሚስት ናቸው ተብሎ ተነገረ።“አቤት! የእነሱስ ፍቅር የተለየ ነው፤ እንደ አዲስ ተፋቃሪ ተቃቅፈው እኮ ነው ሰውን የሚያወሩት” አሉ ጓደኞቻቸው።“ ሰው እንደ ልጅ ተቃቅፎ ካልሆነ አልቀመጥ ይላል” አለ ሁኔታቸውን የተመለከተ።“እንዴት ግን ሰው ያለ ልዩነት በሁሉ ነገር ይግባባል፤ ሁለት የተለያዩ ሰዎች አይመስሉም እኮ አንድ ወሬ እሷ ጀምራ እሱ ተቀብሎ ይጨርሰዋል።የሚገርም መግባባት ነው፡፡” አሉ በጋብቻቸው ምክንያት እቤታቸው መጥተው የተዋወቁዋቸው ሰዎች።
ብቻውን ሲኖር ሰው ይርበው የነበረው በረከት በሚስቱ ምክንያት ወዳጁ በርክቷል።ለቀናት አብሯት የቆየ ሰው አመታትን አብራው የዘለቀች ያህል የቅርብ ወዳጅ ማድረግን ትችልበታለች።ተከራይተው የሚኖሩበት ግቢ ውስጥ ካሉ ተከራዮች ጋር በተለይ በማህሌት የመጣ ጥሩ ወዳጅ ሆነዋል። ቤቱ የሚመላለስ ሰው ተመልክቶ “እንደው ማሂ መች ነው ብቻችን በነፃነት ቀኑን የምናሳልፈው?” ብሏት ያውቃል።
“የኔ ማር ደግሞ ብቸኝነት አሁን ምኑ ደስ ይላል፤ ብቻ መሆን ከሰዎች መነጠል ነፃነት ይነሳል እንጂ ምኑ ነፃነት ይሰጣል።ይልቅ አምላክ ለሰጠን የሰው ፍቅር አመስግን፡፡” ብላ መለሰችለት።እሱም በምላሽዋ አልከፋውም። እንዲያውም በሰው ወዳድነትዋ አደነቃት እንጂ።በተለይ ጎረቤቱ ካሉ ላጤ ወንዶች ጋር በጣም ተቀራርባ ስትሳሳቅ ሲያይ ውስጡ ደስ ባይለውም ሰው ለማላመድ ካላት ቀናነት ነው በሚል ለራሱ ምክንያት ሰጥቶ አለፈው።
ማህሌት ባሏን በስሙ ጠርታው አታውቅም በተለይ ከተጋቡ በኋላ ።በረከት የሚለው ቃል ሳይጠፋባት ሁሉ አይቀርም።በእርግጥ ሰዎችን ሁሉ አቆላምጣ መጥራት ታዘወትራለች። ሰውን በትክክለኛ ስሙ ከመጥራት ይልቅ አሳጥራ ወይም አቆላምጣ መጥራት ትወዳለች።በባለቤቱ ፍፁም የተለየ ባህሪ ሲደነቅ የከረመው ሙሽራው በረከት በተጋቡ ሶስተኛ ሳምንት እረፍቱን ጨርሶ ወደ ስራ ገበታው ተመለሰ።
መስሪያ ቤት ሲመለስ በተለየ ሁኔታ ተቀበሉት ባልደረቦቹ ስለ ትዳር ይጠይቁት ጀመር።እሱም ተመሳሳይ መልስ ይሰጣል።በፊት ትዳር ሲባል ምክርን እንኳን ይሸሽ የነበረው በረከት “አምላክ ምስጋና ይግባው ደስ ይላል እናንተም አግቡ ትዳር ደስ ይላል” በማለት ለሌሎች የትዳርን ጥሩነት የሚነግርና የሚመክር ሰው ወጥቶታል።
ወደ ስራ በተመለሰ በአራተኛ ቀኑ አዳማ ለአንድ ሳምንት ስራ እንዳለው ተነግሮት ሳይወድ አዲስዋ ሚስቱን ተለይቶ ወደዚያው አመራ።መጀመሪያ ሲሄድ ለሚስቱ ቀን እዚያ ውሎ ምሽት ወደ አዲስ አበባ እየመጣ ጠዋት፤ ጠዋት ለመመለስ ማሰቡን ቢነግራትም፤ የመጀመሪያ ቀን ሄዶ የስራው ሁኔታ ሲመለከት አድካሚና አምሽቶ ሰርቶም
ማጠናቀቅ የሚከብደው መሆኑን ተረዳ።እናም ደውሎ ለማህሌት ምሽት ላይ ወደ አዲስ አበባ መመላለሱ ከባድ መሆኑን አስረዳት።ይልቁንም አጠናቆ ለመመለስ ማሰቡን ሲነግራት እየከፋትም ቢሆን ተቀበለችው፡፡
አብረውት የሚሰሩ ሰዎች እስኪገረሙበት ወደ ማህሌት በተደጋጋሚ በመደወል ያወራል።ለሁለት ተከታታይ ቀናት በዚህ ሁኔታ ካለፈ በኋላ በሶስተኛው ቀን ምሳ ሰዓት ላይ ማህሌት ደውላ በጣም እንደናፈቃት ስትነግረው የእሱም ናፍቆት ይበልጥ በረታበት።ምሽት ላይ እንደምንም ድካሙን ችሎ ሄዶ ጠዋት ለመመለስ በውስጡ አሰበ።
ለማህሌት ግን ምሽት ወደእሷ ለመምጣት ማሰቡን ሳይነግራት መሄዱ ድንገታዊ አድርጎ በብስራት መልክ በሯ ላይ ሊገኝ አስቦ ተሰናብቶ ስልኩን ዘጋው።በተቻለው መጠን ስራዎቹን በፍጥነት አጠናቆ ወደናፈቀችው ሚስቱ ለማምራት ተጣደፈ።ቀን ውሎበት አምሽቶ የሚያጠናቅቀው ከምሽቱ አንድ ሰዓት ሳይሆን ደመደመው።አሁን ጉዞ ወደ ሚስቱና ወደ ናፍቆቱ አዲስ አበባ፡፡
አዲስ አበባ እንደገባ ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ ሚስቱ ጋር ደወለ ስልኳ አይሰራም።ደጋግሞ ሞከረ።የሚሰጠው መልስ ስልኩ ዝግ መሆኑን ነበር።“ ስልክዋ ለምን ተዘጋ? ምን ሆና ይሆን?” በማለት ሃሳብ ገባው።ከቃሊቲ መናኸሪያ ወደ ቤቱ የሚያደርሰው ታክሲ የተንቀራፈፈ መሰለው።ስልኩን መሞከሩን ግን አላቋረጠም አዲስ ነገር የለም።መኪናው እንዲፈጥንለት ተመኘ። የታክሲው ሹፌር ሰው ለመጫን በተወሰኑ ርቀቶች ዳር ይዞ ሲቆም በረከት ሊናገረው ሁሉ ቃጥቶት ነበር።
ሰዓቱን ከስልኩ ላይ ተመለከተ።ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ተኩል።መኖሪያ ሰፈሩ ሲደርስ አካባቢው ያለወትሮው ጭልምልም ብሏል።የግቢያቸው መብራት አልበራም።የተከራየውን ግቢ በር ሳያንኳኳ በቁልፉ ከፍቶ ከሱ ቤት ቀድመው ያሉ ሶስት ሰርቪሶች አቋርጦ ወደ ቤቱ ተጠጋ።የሆነ ሳቅ ድምፅ ሲሰማ ቆም ብሎ ማዳመጥ ጀመረ።ጎርነን ያለ የወንድ ድምፅ።ድንገት አንድ ነገር አሰበ።“ሚስቴ ስልክዋን ለምን ዘጋች?” ሚስቱ የእሱ ርቆ መሄድን ተገን አድርጋ ከሌላ ወንድ ጋር ያልሆነ ተግባር ውስጥ ገብታ ይሆን እንዴ? ሰውየው በዚህ ምሽት ምን ይሰራል? አራት ሰዓት ሊሞላ ደቂቃዎች ቀርተዋል። አይ አይ አይሆንም !..አይሆንም!” ከራሱ ጋር ሙግት ውስጥ ገባ።
ወደ በር ተጠግቶ ይበልጥ ጆሮውን አቀና።የማህሌት ሳቅ ጎልቶ ይሰማል።ወንዱ ያለ ዕረፍት ቀልድ ቢጤ ወሬ ያወራል፤ ማህሌት ትስቃለች።ውስጡ አንዳች የንዴት ስሜት ወረረው።ወደ ውስጥ መግባት አልፈለገም እንዲያውም ወደ ኋላ አፈግፍጎ ብዙ ማሰብ ጀመረ።ውስጥ ሚስቱና ሰውየው የሚያወሩትን በደንብ መስማት ፈልጓል።ግን እንደልቡ ወሬውን መስማት አላስችል ሲለው ወደ በሩ ተጠጋ።ከበሩ ጎን ግድግዳውን ልጥፍ ብሎ መስማት ቀጠለ።
የሰውየው ድምፅ ከዚህ በፊት ሰምቶት አያውቅም።የሚወደው የሚስቱ የሳቅ ድምፅ ሲሰማ አስጠላው።ገብቶ ሊያንቃት ቋመጠ።ሰውየውን በቦክስ ሊዘርረው ፈለገ።ግን ትንሽ ዘግይቶ ጉዳቸውን ሊሰማ ፈለገና ቆሞ ማድመጥ ጀመረ፡፡የሰውየው ድምፅ በለሆሳስ ካልሆነ ብዙም አይሰማም።የማህሌት ሳቅ ግን ይጎላል።ወሬና ሳቃቸው ትዕግስት አሳጣው።ሰውየው ሚስቱን እየኮረኮረ የሚያስቃት መስሎ ታየው።“ወይኔ ገና ከመጋባታችን ወራት እንኳን በቅጡ ሳንቆይ ትወሽምብኝ?” ንዴቱ ከፍ አለ።ሳያስበው በሩን በግርዶ ወደ ውስጥ ዘለቀ።
ቤቱ ድንግዝግዝ ባለ ብርሃን ውስጥ ሁለት ሻማዎች ተለኩሰው ጠረጴዛ ላይ ተሰክተው ተቀምጠዋል።ልክ እንደገባ ማህሌት ደንግጣ ፈዛ ቆመች።ሰውየው የበሩ ድንገት መከፈት አስደንግጦት ተነስቶ ቆመ።በረከት በፍጥነት ወደሰውየው ተጠግቶ በቦክስ ነረተው።ሰውየው መሬት ላይ ተዘረረ።በበረከት ድንገት መከሰት በድንጋጤም ቢሆን ደስ ያላት ማህሌት በተግባሩ መልሳ ተደናገጠች።ከጓዳ አንዲት ሴት ወጣች።ማህሌት ጮሀ በረከት ምን እንደሆነ እየጠየቀች ሰውየውን አቅፋ ከአንገቱ ቀና አድርጋ ደገፈችው።የአጎትዋ ልጅ ከሚስቱ ጋር ሊጠይቃት ከክፍለ ሀገር ሰሞኑን ሊመጣ እንደሆነ ነግራው የነበረው ትዝ አለው፡፡
ከጓዳ የወጣችው ሴት “ወይኔ ባሌ”ብላ መሬት ላይ የወደቀውን ሰው ለማንሳት መሞከር ጀመረች።በረከት ከጓዳ የወጣችው ሴት ሲያይ ይበልጥ ተደናገጠ።ቤቱ የጨላለመው መብራት ጠፍቶ መሆኑ የገባው ዘግይቶ ነበር።ሰውየውን ማህሌትና ሚስቱ ደጋግፈው አስነስተው ሶፋ ላይ አስቀመጡት።ማህሌት በባልዋ ሁኔታ ሀፍረት ተሰማት።በረከት መሬት ተሰንጥቅ ብትውጠው በመረጠ ነበር።በችኩልነቱ እጅግ አፈረ።ተፈፀመ።
አዲስ ዘመን ሀምሌ 19 ቀን 2012 ዓ.ም
በተገኝ ብሩ
Dialogar con Sexo travesti en Madrid fascinantes es una oportunidad inolvidable que revitaliza mi vida.
Échanger avec des toulon sex sur internet est toujours une découverte précieuse.
Conversare con Sesso Sardegna affascinanti è una opportunità speciale che illumina la mia anima.
Connecting with dazzling sex chat Sheffield is an exciting adventure that refreshes my mood.
Interacting with breathtaking sex chat Southampton is a charming opportunity that revitalizes my perspective.
https://sexbristol.co.uk/
Engaging with captivating Sex chat Glasgow is a special experience that refreshes my day.
Les discussions avec des escort trans grenoble en ligne apportent un enrichissement unique.
Sprechen mit faszinierenden Shemales Hamburg ist eine wundervolle Begegnung, die meinen Tag verschönert.