ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የላቀ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና የጋራ ብልጽግና የሚያገኙበትን ዕድል ይዞ የመጣ ነው። ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው ጀምሮ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ያላት አቋምም ምክንያታዊ ፣ህጋዊ፣ ማንንም አለመጉዳት እና እኩል ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ነው። በዚህ አቋሟ ዛሬም እንደትናንቱ ማንንም የመጉዳት ዓላማ ሳይኖራት የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ቆማ የግድቡን ግንባታ በማካሄድና ወደ ፍጻሜ በማቃረብ ላይ ትገኛለች ። በያዘችው ፕሮግራም መሰረት በቀሪዎቹ ሁለት ሳምንታት የህዳሴ ግድቡን ቀሪ ስራዎች በማጠናቀቅ የውሀ ሙሌት ስራዋን ታካሂዳለች። ይሄ የኢትዮጵያ የማይለወጥ እና የማያወላዳ አቋም በመሆኑ ለሁሉም ግልጽ ሊሆን ይገባል።
ይሁን እንጂ ግብጽ ይሄንን የኢትዮጵያን ጠንካራ አቋም ለማስለወጥ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና እንዲያደርግ ለማድረግ የተለያዩ ጊዜ ያለፈባቸውን ሀሰተኛ እና የቅኝ ግዛት ስምምነት ሰነዶችን ይዛ ታች ላይ ማለቱን አሁንም ቀጥላለች።
አንዴ አሜሪካና የአለም ባንክ ያደራድሩን ስትል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ የመንግስታቱ ድርጅት ያሸማግለኝ ስትል ቆይታለች። የአረብ ሊግ አገራትም ድጋፍ እንዲሰጧት የሙጥኝ ስትል ከርማለች። በዚህ ሁሉ ሙከራዋ ያሰበችው መሰሪነት አልሳካ ብሏት ድርድሩ ወደ ሶስቱ ሀገራት ተመልሶ እየተካሄደ በአቋራጭ ደግሞ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይዛ የሮጠችው አቤቱታ ዳግም እንዳሰበችው ውጤት አላመጣላትም።
ኢትዮጵያ በአለምአቀፍ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ህግ በመመራት ሁሉንም የተፋሰሱን ሀገራት
እኩል ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ጉዳዩ እንዲደመደመም ጥረት አድርጋለች። ይሄ ጥረቷ አሁንም ቀጥሏል። ጉዳዩም አፍሪካዊ በመሆኑን አፍሪካዊ ጉዳይ በአፍሪካውያን እንዲታይና መፍትሄም እንዲያገኝ ስትወተውት ቆይታለች። ይሄ ጥረቷ አሁን ውጤት አምጥቷል።በነገው ዕለትም በአፍሪካ ጉዳይ ያለማንም ጣልቃ ገብነት አፍሪካውያን ታዛቢዎች በሚገኙበት የሚካሄደው ድርድር አፍሪካዊ ፍትህና መፍትሄ እንደሚያመጣ ታምናለች።
ዓባይ ለኢትዮጵያ ተፈጥሮ የለገሰቻት ከድህነት መውጫ መሰላሏ ነው። በዚህ መሰላል ተንጠላጥለን ፣ በራሳችን ጥረት ልናሳካውና ልንጠቀምበት የምንገነባውን የህዳሴ ግድብ ለማጨናገፍ ግብጽ የማትምሰው መሬት የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም። ግብጽ የዓለም ሀገራትን በማሳሳት የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን መነሻ በማድረግ ለማሳመን የምዕራቡን አለም እና የመካከለኛው ምስራቅ ሁሉንም አይነት መገናኛ ብዙሀን በክፍያ ጭምር በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ ሰፊ አለም አቀፍ ዘመቻ ስታካሂድ ቆይታለች። አሁንም ይሄንኑ ዘመቻ እና አለ ም አቀፉ ማህ በረሰብ ለማሳሳት የምታደርገውን ሩጫ ቀጥላለ ች።
ግብጽ የምታራምዳቸው አብዛኞቹ አቋሞች በሃሰተኛ ማስረጃ እና ጥናት ላይ የተመሰረተ ነው። በዚህም የተሳሳቱ መልዕክቶችን በመቅረጽ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ እይታ በመቀየር በኢትዮጵያ ላይ ሁሉንም አይነት ጫና ለመፍጠር የተለያየ ጥረት ማድረጓን እንደምትቀጥል ይጠበቃል። ግብጽ ምንም ትበል ምን ኢትዮጵያ ግን ከአቋሟ ዝንፍ አትልም። ይሄ ሁሉ ሩጫ እና ላይ ታች ማለት የመጣው ኢትዮጵያ በራሷ አቅም አታሳካውም ብላ ያሰበችው ተሳክቶ እውን ሲሆን ማየቷ ስላስደነገጣት መሆኑ ግልጽ ነው። አሁንም ቢሆን የጀመርነውን ከመጨረስ የሚያቆመን ምንም ሀይል አይኖርም።
አልተሳካላትም እንጂ ግብጽ ከመነሻውም ግድብ የመገንባት አቅም እንዳይኖረን ብዙ ጥራለች፤ ለጋሽ ሀገራት ድጋፍ እንዳያደርጉልን ሰርታለች።በራሳችን አቅምም እንዳንጀምር፣ የጀመርነውን እንዳንቀጥል ለማድረግም ስትወጣ፤ ስትወርድ መቆየቷ የማይታበል ሀቅ ነው።
ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ የተፈጥሮ ሀብቷ ተጠቅማ ሀገሯን እንዳታለማ ፣ ህዝቧን ከድህነት እንዳትወጣ እና ግብጽ ልማቷን እንቁልልጭ እያለች እንድትቀጥል አሁንም ትመኛለች።ይሄ ግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያከትሟል። ኢትዮጵያ ህዝቧን ከድህነት ለማውጣት የጀመረችውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች። ግድቡን ውሃ የመሙላት ሂደትም ያለምንም ማንገራገር ይከናወናል። ታላቁ የህዳሴ ግድብን በማጠናቀቅም ግብጽን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ይቋደሳሉ!
አዲስ ዘመን ሰኔ 21/2012
ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድቡ ዙሪያ ያላት አቋም ዛሬም ነገም አንድ ነው!