ኢትዮጵያ የህዝቦቿን ጥቅም አስቀድማና የመልማት ዕቅድን ሰንቃ በሙሉ ድጋፍ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ለመገንባት የተነሳችበት ሥራ ታላቅ ታሪክ ነው። ይህ ተግባር ህዝቡ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ሲባል በነቂስ ወጥቶ የአገሩን ድንበር ለማስከበር በቆራጥነት እንደሚሰለፈው አገር ወዳድ ዜጋ ለልማቱም በቆራጥነት መሰለፉን ያሳያል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ የሃገርን ክብር እና ሉዓላዊነት ወደላቀ ደረጃ ክፍ ለማድረግ ከሚደረግ ጦርነት ያልተናነሰ በግምባር ምሽግ ቆፍረን ከምናደርገው ጦርነት የባሰ ከባድ እና የተወሳሰበ የልማት የጦርነት አውድማ ነው ማለት ያስደፍራል። ለዚህም ነው መላው ኢትዮጵያዊ ይህን ተገንዝበው ያለ የሌለ ሃብታቸውንና ጉልበታቸውን ያለስስት እየለገሱ የሚገኙት።
ይህ አገራዊ ፕሮጀክት ሰፊ ህዝባዊ አቅም ማሰባሰብ የቻለ፣ የብዙዎቹን ልብ በተስፋ የሞላ፣ የአዳጊዋን ኢትዮጵያ የህዳሴ ችቦ የለኮሰ ፣ የይቻላል መንፈስን የተከለና ከተባበርን የማንችለው ነገር እንደሌለም ያሳየ ነው።
ይኸው ግድብ የግንባታው መሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ወቅት አንስቶ በአገር ውስጥ ሥራውን የሚያጣጥሉና የሚያደናቅፉ ፤ በውጭ ደግሞ ያላሰለሰ የዲፕሎማሲ ሥራ የሚፈልጉ ተጽዕኖዎች ሲጋረጡበት በብልሀት እየታለፈ ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ በቅቷል።
ከግድቡ ሥራ ጋር ተያይዞ በ በተለይም በአገር በቀሉ ሜቴክ የተፈጸሙ ስህተቶችን ማረምና የግድቡን ግንባታ ማፋጠን በለውጡ አመ ራር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል። በተለይም በያዝነው በጀት ዓመት መንግሥት በያዘው ቁርጠኛ አቋምና የህብረተሰቡ ግድቡ ተጠናቅቆ የማየት ጉጉት ተደማምረው የወቅቱ የሥራው አፈጻጸም እንደሚያመለክተው የሲቪል ኢንጅነሪንግ ስራው 87 በመቶ ፣የብረታብረት ስራዎቹ ደግሞ ከ 31 በመቶ በላይ ፤ የኤሌክትሮ ሜካኒካል፣ የተርባይንና የጀነሬተር ተከላ ስራዎች አፈጻጸምም 45 በመቶ ፤ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም ደግሞ 74 በመቶ መድረስ መቻሉ የግድቡን መጠናቀቅ ለሚናፍቁ ተስፋን ሲመግብ፤ የግድቡ ሥራ ሳይደናቀፍ ወደ ፍጻሜ መንደርደሩ ያሳሰባቸውን ደግሞ እንቅልፍ ነስቷቸዋል።
በሥፍራው ተገኝተው የግንባታውን ሥራ የሚመሩት የሥራ ሃላፊዎች እንደሚናገሩት በተያዘለት ዕቅድና ሥራው በሚፈቅደው አግባብ በዚህ ዓመት የውሃ ሙሌቱ ይጀመራል። ይህ የሚሆነውም አሁን ላይ ያለው የግድቡ ስራ አፈጻጸም በራሱ የውሀ ሙሌት እንዲጀመር አስገዳጅ በመሆኑ ነው ።
አዎ! የአባይ ውሃ በበራቸው እያለፈ መብራት የማያገኙ ኢትዮጵያውያን የትዬለሌ ናቸው፤ እናቶች የኃይል አቅርቦት አጥተው የማገዶ እንጨት ለቅመው ምግብ ለማብሰል በጭስ ሲቸገሩ ማየት ምንኛ ያሳዝናል። ከተሞች የኃይል አቅርቦት አጥተው ኢንዱስትሪ ሳይስፋፋ መቆየቱ ፣የስራ አጥ ቁጥር ማሻቀቡ ፣የኑሮ ደረጃ ያለመሻሻሉ ሁሉ መንስዔው እስከዛሬ ድረስ ባለን ወንዝ ተጠቅመን የኤሌክትሪክ ኃይል ያለማግኘታችን ጉዳይ ነው።
እነሆ ዛሬ የሥራ ጽናታችን ፣ በህብረት የመነሳታችን ውጤት፣ ታላቅ ራዕይ የመሰነቃችን መዳረሻ ደስታን ሊያጎናጽፈን በተቃረብንበት ወቅት ጥቂትም ቢሆን የሚያሳስበን ጉዳይ ከተፋሰሱ አገራት ዋነኛዋ ተጠቃሚ የሆነችው ግብጽ ከፍተኛው የውሃ መጠን ይገባኛል፣ የውሃ ሙሌቱም ከሰባት እስከ አሥር አመት መሆን አለበት በሚል ግትር አቋም የዲፕሎማሲውን ሥራ ለማደናቀፍ ያላሰለሰ ጥረት ማድረጓ ነው። ይሁንና ይህ የሚጠበቅ ሆኖ በመንግሥትና በተደራዳሪዎች ብቃትና ብልህነት፣ አገራችን ከያዘችው የፍትሃዊ ተጠቃሚነት መርህና በመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ስኬታማነትን በመጎናጸፍ ግድቡ ተጠናቆ ለህዝባችንም ሆነ ለተፋሰሱና ለጎረቤት አገራት እራትም መብራትም የሚሆንበት ጊዜ ተቃርቧል!
አዲስ ዘመን ሰኔ 10/2012
ታላቁ የህዳሴ ግድባችን እራትም መብራትም ሊሆን ተቃርቧል!