ዓለምን ባስጨነቀው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት የዓለም ታላላቅ አየር መንገዶች ሠራተኞችና ደመወዝ ቀንሰዋል፤ ኪሳራ እንደደረሰባቸው አሳውቀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእነርሱ እጣ ፋንታ ይደርስበታል ተብሎ ሲታሰብ በወረርሽኙ መዛመት ሠራተኞቹ እንዳይጎዱ ጠብቆ፣ የኤክስፖርት ምርትን እያጓጓዘ፣ ለቫይረሱ ስርጭት መከላከል ለአፍሪካ የተለገሱ ቁሳቁሶችን እንዲያከፋፍል አደራ ተጥሎበት በስኬት ዛሬ የደረሰበት የስኬታማነት ደረጃ ላይ ሲደርስ ፤ለአገሪቱ የውጭ ምንዛሪን አስገኝቶ፣ ምርታቸውን እንዲያጓጉዙለት የጠየቁትንም አስደስቶ ገናናነቱን አስመስክሮ ታይቷል። የባህር በር በሌላት ኢትዮጵያም የአፍሪካ በር ሆኗል!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ ከትናንት በስቲያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች መልስ በሰጡበት ወቅት ‹‹ የአየር መንገዱ ማኔጅመንትና ሠራተኞቹ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል፤ እንደ ኩባንያ ትልቅ መሆኑንና ትልቅ ነን ብለው ከሚሉት የሚሻል መሆኑን በተግባር አስመስክረዋል ›› ሲሉ ተቋሙ ያከናወነውን ሥራ ጠቅሰው አወድሰዋል።
እውነት ነው በአገሪቱ ባለፉት 10 ወራት በሁሉም ዘርፍ አበረታች እድገት ሲመዘገብ ቢቆይም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት ባለፉት ሶስት ወራት የታየው እድገት መቀዛቀዝ ቢያሳይም በዚህ ሂደት የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ አልተጎዳም ።
መንግሥት ከግል ባንኮች ቦንድን ማስቀረቱ፣ ብሄራዊ ባንክ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት በኋላ ለባንኮች 48 ቢሊየን ብር ፈሰስ ማድረጉ፣ አነስኛና ጥቃቅን ኢንዱስትሪዎች እንዳይጎዱና ብድር እንዳይስተጓጎል መደረጉ፣ ከፍተኛ ዕዳ ለነበረባቸው ግብር ከፋዮች ከ78 ቢሊየን ብር ያላነሰ እዳ መሰረዙ የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት ታድጓል።
ባለፉት 10 ወራት ወደ ውጭ የሚላክ ምርት በ13 በመቶ ማደጉ ፤ የ27 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው 800 ኪሎ ግራም ወርቅ ብሄራዊ ባንክ ገቢ መደረጉ፣ ቡና 667 ሚሊየን ዶላር፣ አበባ 440 ሚሊየን ዶላር እንዲሁም ስጋ 45 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማስገኘታቸው በችግር ውስጥ ጠንክሮ በመሥራት የተገኘ ውጤትና ብቃት ያለው አመራር የመኖሩ ውጤቶች ናቸው ።
ይሁን እንጂ በኮቪድ-19 ምክንያት የቱሪዝም ዘርፉ በተለይም የአገልግሎት ዘርፉ የተጎዳ ቢሆንም በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ የቱሪስት መስህብ ሥፍራዎችና በኪነ ጥበብ የተዋቡ የከተማ ፓርኮች የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ሲገታና ሁሉም ሰው በነጻነት የመንቀሳቀስ መብቱን ሲጠቀም የቱሪስቶች መስህብ ሆነው ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እንደሚሆኑ ከወዲሁ መናገር ይቻላል። የሸገር ፕሮጀክት፣ የእንጦጦና አንድነት ፓርክ ደረጃቸውን ጠብቀውና አምረው በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ድህረ ኮቪድ የኢትዮጵያ የቱሪዝምና ሆቴሎች ትንሳኤ እውን መሆኑን አመላካች ናቸው። ከግብርናና ከኢንዱስትሪው በተጨማሪ አገራችን ከቱሪዝሙ ዘርፍ ጠቀም ያለ ገቢ እንድታገኝ ጥሩ መደላደል እንደሆነም ግልጽ ነው።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ 11 በመቶ በአማካይ ሲያድግ መቆየቱ ቢታወቅም፣ በአሁኑ ወቅት ያጋጠሙ የኢኮኖሚ ቀውሶች መነሻ ዋና ዋና ነጥቦች ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፣ የብድር ዕዳ ጫና፣ ከፍተኛ የሥራ አጥነት፣ የገንዘብ አቅርቦት ችግርና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሚዛን ይደፋሉ።
ቀጣይነት ያለው ዕድገት ማምጣትና ፍላጎትን በአገር ውስጥ ምርቶች መሸፈን ወይም ከውጭ ሊገቡ የሚችሉ ምርቶችን በዘላቂነት መተካት መቻል፣ የውጭ ምንዛሪ የሚያመነጭ ኢኮኖሚ መፍጠር መቻሉ መሠረታዊ ከሚባሉ የመፍትሔ መንገዶች ዋናዎቹ ስለመሆናቸው ይጠቀሳል።
የአገሪቱን ኢኮኖሚ በዘላቂ የዕድገት መርህ ማስኬድ እንዲቻል ፈርጀ ብዙ ተግባራት መከናወን ይኖርባቸዋል። የመንግሥት የማስፈጸም ብቃትን በማሳደግ በኢኮኖሚው ውስጥ የተቆጣጣሪነት ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ የሚያስችሉትመዋቅራዊ ማሻሻያዎች ተግባራዊ ማድረግም ያስፈልጋል።
የአገሪቱን የውስጥ ሰላም በማጠናከር፣ ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ በመሆን፣ ከፍተኛ የሥራ ዕድል በመፍጠርና ሥራ አጥነትን በመቀነስ እንዲሁም የቱሪስት መስህብ በመሆን ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር መሆን፤ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ መሰለፍም የምትችል ትሆናለች።
በተለይም ባለፉት ሦስት ወራቶች በአገሪቱ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ያጋጠመው የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ይህ ነው የሚባል ጉዳት እንዳያደርስ በመንግስት በኩል ዘዴ የተመላበት አመራር እንደተሰጠው ሁሉ በኢኮኖሚው መጻኢና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ላይ ትኩረት ከተደረገ ይበልጥ አገሪቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ የሚያሸጋግር ውጤታማ እድገት ማየት የሚቻልበትና የኢትዮጵያ ብልጽግና የሚረጋገጥበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም!
አዲስ ዘመን ሰኔ 3/2012
በፈተና ውስጥ ውጤታማ ኢኮኖሚ!