አዲስ ዘመን ጋዜጣ 79ኛ ዓመት የልደት በዓሉን እያከበረ ነው።ኢትዮጵያ በእነዚህ ስምንት አስርት አመታት የነበራትን መልክ ለመመልከት አዲስ ዘመንን የሚመጥን መስታወት የላትም።አዲስ ዘመን የታሪክ ሰነድ ነው።ግንቦት 30 ቀን 1933 ዓ.ም የታተመው የመጀመሪያ እትም በፊት ገጹ የጋዜጣውን ዓላማ የሚገልፅ ጽሑፍ ይዞ ወጥቶ ነበር። እንዲህ ይነበባል ፡-
“ይህ አዲስ ዘመን ተብሎ የተሰየመው ጋዜጣ ከዛሬ ጀምሮ ወደፊት ለመላው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የረዳትነቱን ስራ ይሰራ ዘንድ ተመሰረተ። ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ለኢትዮጵያ አዲስ በሆነው ዘመን ለአገርና ለሕዝብ ጥቅም የሚያስፈልገውን ስራ ሁሉ እያመለከተ ፤ ይልቁንም ሕዝብ ለአገሩ ፤ ለመሪውና ለንጉሰ ነገሥቱና ለንጉሰ ነገሥቱም መንግሥት ማድረግ የሚገባውን እየገለፀ የበጎን ስራ መንገድ የሚመራ እንዲሆን ይህ ጋዜጣ በግርማዊ ንጉሰ ነገሥት ተመሰረተ።”
አዲስ ዘመን ከተመሰረተበት ዕለት አንስቶ የተጣለበትን ኃላፊነት እየተወጣ ለ79 ዓመታት ዘልቋል።ይህ አንጋፋ ጋዜጣ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የይዘትና የቅርጽ ለውጥ በማድረግ በተሻለ ጥራት ወደ እንባቢዎቹ እየደረሰ ይገኛል።አዲስ ዘመን አሁንም ድረስ ከወንድሙ “ዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ” በቀር አቻ የሌለው ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ዕለታዊ ጋዜጣ ነው።ለመቁጠር ከሚታክቱት ከአዲስ ዘመን ትውስታዎች ጥቂቶቹን እነሆ !
አዲስ ዘመን ግንቦት 30/2012
የትናየት ፈሩ