ታህሳስ 7 ቀን 1965 ዓ.ም የታተመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ አንድ ሰው ገድላችኋል ተብለው 500 ሰዎች መከሰሳቸውን በተከ ታዩ ዘገባ አስነብቦ ነበር፡፡
በአንድ ሰው ሞት 500 ሰዎች ተከሰሱ
እስካሁን ድረስ በሕግ ታሪክ ውስጥ ተመሳሳይ የሌለው ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ 500 ሰዎች አንድ ሰው ገድላችኋል ተብለው ተከሰዋል፡፡ የተገደለውም የደቡብ አፍሪካ ተወላጅ ነው። ስሙ ንዶምቤ ንካምቢያንዲ ይባላል። ሥራው ገንዘብ አበዳሪ ነው። ንዶምቤ የየመንደሩን ህዝብ ንብረት መያዣ እያደረገ ገንዘብ ማበደር ይወድ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ተበዳሪዎች ከፍ ያለውን የአበዳሪውን ወለድ (አራጣ) ለመክፍል ሲሉ መሬታቸውንና ከብታቸውን ያጡ መሆናቸውን ተገነዘቡ፡፡
ከሁሉ ይበልጥ ጉዳት ላይ የወደቀው የኢቱካሚ መንደር ሕዝብ ነው ፣ ይህ መንደር ከባድ የሰብል ብልሽት ስላጋጠመው ከገንዘብ አበዳሪው ዘንድ ለዘር የሚሆን እህል ተበደሩ። በሚቀጥለውም ጊዜ የሰብል ብልሽት ስላጋጠማቸው መክፈል ቸገራቸው፡፡ ብድሩ ስለበዛ መላው መንደር የአበዳሪው ንብረት ለመሆን ስለተቃረበ የሰፈሩ ሴቶች ተማክረው ሰውዬው ሲመጣ ደብድበው ገደሉት፡፡
ዳኛው ማን እንደገደለው ቢጠይቅ ሁላችንም ነን ብለው ስላደሙ ምናልባት በግድያው ተካፋዮች ያልሆኑ እንዳሉ ተብሎ ሲመረመር 42 ሴቶች በግድያው ተካፋዮች የመሆናቸው ሁኔታ ዝቅ ያለ ነው ተብሎ በነጻ ተለቀቁ፡፡ የተረፉት 458 ሰዎች ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር እንዲታሰሩ ተፈርዶባቸዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ሬዲዮ
አዲስ ዘመን ግንቦት 26/2012
የትናየት ፈሩ
አዲስ ዘመንድሮ