በመሪነት ብቃታቸው ከተመሰከረላቸው ኢትዮጵ ያውያን ሴቶች አንዷ የሆኑት የአጼ በካፋ ባለቤት ፣ የአጼ ኢያሱ ዳግማዊ (የቋረኛ ኢያሱ) እናትና የአጼ ኢዮአስ አያት እቴጌ ምንትዋብ ብርሃን ሞገሳ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ከ247 ዓመታት በፊት በዚህ ሳምንት ግንቦት 26 ቀን 1765 ዓ.ም ነበር። እቴጌ ምንትዋብ 1700 ዓ.ም አካባቢ ቋራ ውስጥ ከአባታቸው ከደጃዝማች መንበሩና ከእናታቸው ከወይዘሮ እንኮዬ ተወለዱ። በዘመናቸው በዓጼ ልብነ ድንግል ጊዜ እንደ ነበሩት እንደ አጼ በዕደ ማሪያም ባለቤት እቴጌ እሌኒ እና እንደ ዳግማዊ ምኒልክ ባለቤት እቴጌ ጣይቱ በቤተ መንግስቱም በህዝቡም ዘንድ የተከበሩና የተፈሩ ነበሩ። ከባለቤታቸው ከአጼ በካፋ ጀምሮ በልጃቸው በቋረኛ እያሱና በልጅ ልጃቸው በኢዮአስ ዘመን ለ40 ዓመታት በሙሉ ስልጣን ያዙ ነበር።
ተክለጻዲቅ መኩሪያ “የኢትዮጵያ ታሪክ ከአጼ ልብነ ድንግል እስከ አጼ ቴዎድሮስ” በተሰኘ መጽሐፋቸው በምዕራፍ 72 አጼ በካፋና እቴጌ ምንትዋብ እንዴት እንደተገናኙ ሲተርኩ “አጼ በካፋ ለአደን ወደ ስናር ድንበር ሄደው ሳለ በወባ በሽታ ስለታመሙ ቋራ በባላባቱ ቤት ገብተው ተኙ። ባላባቱም ንጉሥ መሆናቸውን ሳያውቅ ተቀብሎ በቤቱ አስተኛቸው። የቤቱ ውብ ልጅም ስታስታምማቸው ሰነበተች። ታመው አልጋ ላይ እንዳሉ ድኜ ጎንድር ስገባ ይህችን ልጅ አገባለሁ ብለው አሰቡ። እንዳሰቡትም ከህመማቸው ድነው ጎንደር ሲገቡ መኳንንቶቻቸውን ልከው ወጣቲቱን ሴት አምጥተው በጎንደር ታላቅ ድግስ ተደግሶ በሠርግ አገቡ። እኚህም ሴት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የታወቁት ስመ ጥሩዪቱ እቴጌ ምንትዋብ ናቸው። የክርስትና ስማቸው ወለተጊዮርጊስ ተጨማሪ ስማቸው ደግሞ ብርሃን ሞገሳ ይባላል። እቴጌዪቱ በኋላ ብርሃን ሰገድ ተብለው የነገሡትን ኢያሱን ለበካፋ ወለዱላቸውና ታላቅ ደስታ ተደረገ።” ይላሉ።
ሁለቱ ጥንዶች ስምንት ዓመታት ከኖሩ በኋላ አጼ በካፋ አረፉ። የአባቱን ሞት ተከትሎ ልጅየው ኢያሱ ስመ መንግስቱ “ብርሃን ሰገድ” ተብሎ ነገሰ። በእናቱም የቋራ ተወላጅ ስለሆነ “ቋረኛ ኢያሱ” እየተባሉ ይጠራሉ። ለአዲያም ሰገድ ኢያሱም ሁለተኛ በመሆኑ “ዳግማዊ ኢያሱ” ይባላል። በነገሰ ጊዜ ዕድሜው ያልበሰለ ስለሆነ በነገሠበት ቀን እናቱ እቴጌ ምንትዋብ እንደ ንግስት ዘውድ ጭነው በሞግዚትነት ነገሱ። እቴጌይቱም ኃይለኛና ብልህ ስለነበሩ ከልጃቸው ከንጉሡ ይልቅ የርሳቸው ኃይልና ሥልጣን የገነነ ነበር። እቴጌ ጣይቱ በአጼ ምኒልክ ዘመን ያደርጉት እንደነበረው፣ እቴጌ ምንትዋብም ከቋራ ወንድሞቻቸውንና የወንድሞቻቸውን ልጆች አስቀምጠው ሥልጣኑን ሁሉ አሲዘዋቸው ስለ ነበረ በጊዜያቸው ሊደፈሩ አልቻሉም። የቀድሞዎቹ ባለስልጣኖች አዲስ እየመጡ በሥልጣን የተቀመጡትን ቋረኞች በመጥላታቸው የወገን ልዩነት ሆኖ ይናናቁ ነበር ፤ ህዝቡ ግን ደስ ተሰኝቶ ነበር። ንግሥት በተባሉበት ቀን የወርቅ አክሊል ደፍተውና የወርቅ ጫማ ተጫምተው «ጐማ» በሚል መጠሪያ በሚታወቀው በቅሏቸው ላይ ተቀምጠው ወደ አደባባይ በወጡ ጊዜ ህዝቡ የሚከተለውን ዘፈን በመዝፈን የደስታቸው ተካፋይ ሆነላቸው።
አሁን ወጣች ጀምበር ፣ ወጣች ጀምበር፣
ተሸሽጋ ነበር።
አሁን ወጣች ጨረቃ፣ ወጣች ጨረቃ፣
የምትለን ፍርድ ይብቃ።
ደስ ይበልህ ዘመድ፣ ይበልህ ዘመድ፣
ከነገሠች በዘውድ።
ደስ ይበልህ ባለጌ፣ ይበልህ ባለጌ፣
ከነገሠች እቴጌ።
ደስ ይበልህ ጐንደር፣ ይበልህ ጐንደር፣
ቀድሞ ከፍቶህ ነበር።
ባለጌ የወቅቱ የእደጥበብ ባለሙያዎች መጠሪያ ነው። እቴጌ ምንትዋብ አጼ በካፋን ሲያገቡ ገና ልጅ ነበሩ። ባለቤታቸው በሞት ሲለዩዋቸው ወጣት ነበሩና ከምልምል ኢያሱ ጋር ይፋ ያልሆነ ግንኙነት መሰረቱ። ምልምል ኢያሱ የተባለውም የሚስጥር ግንኙነቱን ህዝብ አውቆ አምቶ ስለነበር ለቤተ መንግስት የታጨ ለማለት ነው። እቴጌም ተቆጥተው “ምልምል አትበሉ ደጃዝማች ኢያሱ በሉ” ብለው አዋጅ አስነግረው ነበር። በኋላ ለደጃዝማች ኢያሱ አስቴርን ፣ አልጣሽንና ወለተ እስራኤልን ወለዱ።
ፋንታውን እንግዳ “ታሪካዊ መዝገበ ሰብ” በሚል ርእስ ባሳተሙት መጽሐፍ በሰፈረው የእቴጌ ምንትዋብ ታሪክ እንደተገለጸውበእቴጌ ምንትዋብ ልጅ (በቋረኛ ኢያሱ)ዘመን ራስ ሥሁል ሚካኤል የተባሉ በፖለቲካና በውትድርና ሙያ ዝነኛ የሆኑ ሰው በትግራይ ተነስተው ነበር። ራስ ሥሁል ሚካኤል ለመጀመሪያ ጊዜ በእምቢተኝነት ተከሰው ነበር። በዚህ ጊዜ አፄ ኢያሱ ዘምተውባቸው ሰማያት በተባለው ትልቁ አምባ ላይ ተከበው እጃቸውን ሰጡ። በመጨረሻም የነበራቸውን ሀብት ሁሉ ለንጉሡ አስረከቡ። አንዳንድ ፀሐፊዎች ሲፅፉ ደግሞ ከነበራቸው ሀብት ግማሹን ብቻ እንዳስረከቡ ገልፀዋል። ውሎ አድሮ ችግር እንደሚፈጠር የተረዱት እቴጌ ምንትዋብ ግን ልጃቸውን አስቴርን ለራስ ሥሁል ሚካኤል በመዳር ከልጃቸው ከአፄ ኢያሱ ጋር የነበረውን ቅራኔ እንዲሽር በማድረግ ከአልጋው ጋር ቁርኝት እንዲኖራቸው አደረጉ።
እቴጌ ምንትዋብ ከሰሜናዊ ኢትዮጵያ በኩል የአስተዳደሩን ሰላም በዚህ መልኩ ሲያስጠብቁት ከደቡባዊ ምሥራቅ በኩል ደግሞ ልጃቸው አፄ ኢያሱን ከነገደ ኤጃው ከተወለደችው ውቢት ከተባለች ወጣት ልጃገረድ ጋር አጋቧቸው። የወጣቷን የክርስትና ስምም ቤርሳቤሕ ተባለ። ሆኖም ግን ንጉሱ ክርስቲያን ያልሆነች የየጁ ሴት አገባ ተብሎ ይታማ ስለነበር ጋብቻው በከተማው እርሱን ያስጠላና ድብቅ እንጂ በግልጽ የሚካሄድ አልነበረም። ቤርሳቤሕ ቀስ በቀስ የየጁ ዘመዶቿን እንደ እቴጌ ምንትዋብ በቤተመንግስት መሰግስግ ጀመረች። በዚህ ሁኔታ በየጁዎችና በቋራዎች የለሆሳስ ፉክክር ተጀመረ።
ሥርገው ሐብለሥላሴ በፃፉት “የአማርኛ የቤተ-ክርስቲያን መዝገበ ቃላት” መፅሃፍ እቴጌ ምንትዋብ ብዙ አብያተ-ክርስቲያናትን ማሰራታቸው ተጠቅሷል። ካሠሯቸው አብያተ-ክርስቲያን መካከል የጐንደር ቁስቋም ፣ በጣና ሃይቅ በደቅ ደሴት ላይ የሚገኘውን ናግራ ሥላሴ እና በጐንደር ከተማ ያለው መጥምቁ ዮሐንስ ይጠቀሳሉ። ጣና ሃይቅ የሚገኘውን የደጋ እጢፋኖስ ቤተ-ክርስቲያንንም አሳድሰዋል።
ተክለጻዲቅ መኩሪያም እቴጌ ምንትዋብ በጎንደር እስከ ዛሬ ከድርቡሽ ቃጠሎ ተርፎ ፍራሹ የሚያስደንቀውን የቅድስት ቁስቋምን ቤተ ክርስቲያን በዘመናቸው ማሰራታቸውን ጽፈዋል። ለዚህም ስራ ሺህ ወቄት ወርቅ ከራሳቸው እንዳወጡ ይኸም የማይበቃ ቢሆን የጣታቸውን ቀለበት አውልቀው እንደጨመሩ ይገልጻሉ።
እቴጌ ምንትዋብ በዘመናቸው በሹም ሽርም ሆነ በዘመቻ ከፍ ያለ ቦታ የነበራቸው ንግስት ነበሩ። የታሪክ ተመራማሪው አቶ አበባው አያሌው በሸገር ኤፍ ኤም 102 ነጥብ አንድ በሚተላለፈው ስንክሳር የተሰኘ የሬዲዮ ዝግጅት የእቴጌዪቱን ጀግንነት ሲተርኩ “ምንትዋብ ደፋርነቷ ደጃዝማች ወሬኛ በጣም ኃይለኛ ሰው ነበር። በአጼ በካፋ ዘመን ዳሞትን ይዞ የጃዊን ጦር ይመራ ስለነበር ይፈራ ነበር። ሌሎችም ደግሞ ክደዋት ነበር። እንዲያውም ቤተ መንግስት ድረስ ደርሰው ጎንደር ግማሿ ተቃጥሎ ነበር። በዚህ ጊዜ ጠላት ተነስቷልና እንዝመት ሲባል ግማሹ የኃይል ሚዛኑን በመገመት ደጃዝማች ወሬኛ ቢያሸንፈንስ ፤ የተቀረው ደግሞ ለዚህ ህጻን ልጅና ለዚህች ሴት ነው ወይ ምንታዘዘው በሚል ሲያቅማሙ እቴጌ ምንትዋብ በግዕዘ ሴት ብፈጠር እንዲያው የሴት አምሳል ያዝኩ እንጂ የወንዶች ወንድ ነኝ። የማልክ በኩላተርሱ ማልና ተከተለኝ ፤ የማትከተለኝ ተወው’ ብላ ተነሳች ፤ ሄደውም የደጃዝማች ወሬኛን ጦር አሸዋ መድኃኒአለም ላይ አሸነፉ። እዚያ ድረስ ትልቅ የሆነች ሴት ናት” ብለዋል።
እቴጌ ምንትዋብ ከእርሳቸው ዘመን በፊትም ሆነ በኋላ ከነበሩ እቴጌዎች በተለየ መልኩ በጎንደር አብያተ መንግስታት በሚገኙበት ጊቢ ከልጃቸው ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ጋር በመሆን እጅግ የተዋበ ዘመናዊ ቤተ መንግስት አሳንጸዋል። ቁስቋምን ከተከሉ በኋላም በቅርብ ርቀት የእንግዳ ማረፊያ ቤተ መንግስት አሰርተዋል። ለስነ ጥበብ ልዩ ፍቅር ስለነበራቸው በተለይም ደግሞ ሰዓሊዎችን ያቀርቧቸውና ያበረታቷቸው ስለነበር የኢትዮጵያ ስነ ስእል በእርሳቸው ዘመን በከፍተኛ ደረጃ አድጓል። ሰዓሊዎች በጥሩ እንክብካቤ እንዲያዙ አድርገው የዮሐንስ ራዕይ እጅግ ባማረ ሁኔታ እንዲሳል አድርገዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለማዊ ስዕል የሰዎች ምስል የተሳለው በእቴጌ ምንትዋብ ዘመን ነው። የተሳሉትም እቴጌ ምንትዋብ ራሳቸውና ልጃቸው ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ነበሩ። ሰዓሊው “ንግስት ይህን ሁሉ ነገር አድርገው ምንድን ነው ዋጋቸው? ሳልስላቸው አልቀርም” ብሎ እንጂ እቴጌ ፈልገው አልተሳሉም። የታሪክ ተመራማሪው አቶ አበባው እቴጌ ምንትዋብ አገር በማቅናት ረገድ እንደነበራቸው ሚና ስማቸው አይነሳም፤ ተዘንግተዋል ይላሉ።
እቴጌ ምንትዋብ ለሙያዎች ከፍተኛ ዋጋ ይሰጡ ስለነበር ሴቶችን አሰባስበው ሙያ ያስተምሩ ነበር። አሁንም ድረስ የእቴጌ ምንትዋብ ሙያ ልኬት ሆኖ ያገለግላል። የወጥ ቤቱን ፣ የቅመማ ቅመም ዝግጅቱን፣ የጠጅና ጠላ ዝግጅቱና አቀራረቡ ጭምር በየዘርፉ ሥርዓቱ እንዲተዋወቅ ጥረዋል። ራሳቸው ጭምር በቀጥታ እየተሳተፉ የተለያዩ የወጥ አይነቶችን በማስተማር ሙያው እንዲያድግ ታትረዋል። የዶሮ ብልት አስራ ሁለት እንዲሆን ልኬቱን የሰሩት እቴጌ ምንትዋብ እንደሆኑ ይነገራል። በቤተ መንግስታቸው አጠገብ ግንብ አስገንብተው ሴቶች በተለያዩ ሙያዎች እንዲሰለጥኑ ይረዷቸው ነበር። ቀጭን ፈትል እንዲፈትሉ፤ ጥልፍ እንዲጠልፉና የአንገትና የጥርስ ንቅሳት ሙያን እንዲማሩ ያተጓቸው ነበር። ባህላዊ የመዋቢያ ጌጣ ጌጦች እንዲዳብሩም አድርገዋል።
“ታሪክ ወንግስት ብርሃን ሞገሳ” የሚል አርስት በተሰጠው የእቴጌ ምንትዋብ ዜና መዋዕል እንደሰፈረው ራሳቸው ባሰሯት ቁስቋም ማሪያም ተጠግተው ለሚማሩ ተማሪዎች ትምህርቱን ለማበረታታት እንደ የደረጃቸው ለፊደል ቆጣሪ እንጀራ በወጥ ፣ ለዜማ ተማሪ እንጀራ በወጥ ከአንድ ብርሌ ጠላ ጋር ፣ ለቅኔ ተማሪ እንጀራ በወጥ ከአንድ አንድ ብርሌ ጠጅና ጠላ ጋር እንዲሁም ለትርጓሜ መጽሐፍት ተማሪ እንጀራ በወጥ ከሁለት ብርሌ ጠጅና ጠላ ጋር ከቤተ መንግስት እየላኩ ፤ ልብሳቸውን ከጠገዴ በሚመጣ እንዶድ እያሳጠቡ በማስመረቅ ከከፍተኛ ሽልማት ጋር በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እንዲያገለግሉ ያደርጉ ነበር። በዚህ ተግባራቸው ዘመናዊ የትምህርት ተቋማት ባልነበሩበት በዚያ ዘመን እቴጌ የቤተ ክህነት ትምህርት በሊቃውንት እንዲመራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።
የናይል ወንዝን ምንጭ ለመፈለግ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ስኮትላንዳዊው ጀምስ ብሩስ “Travels to Discover the Source of the Nile” የሚል ርዕስ በሰጠው መጽሐፉ በጎንደር በነበረው ቆይታ የተመለከተውን የቤተመንግስቱን ሁኔታ ባሰፈረበት ማስታሻው እቴጌ ምንትዋብ ምን ያህል በወቅቱ የሚፈሩ የሚከበሩና በጥበብ ወዳድነታቸው የሚደነቁ መሆናቸውን አስፍሯል።
እቴጌ ምንትዋብ መንግስታዊ አስተዳደሩን ከልጃቸው ኢያሱ ብርሃን ሰገድ ጋር ለ25 ዓመታት ሲመሩ ከቆዩ በኋላ ኢያሱ አረፉ። ከወለተ ቤርሳቤሕ የተወለደው ልጃቸው ኢዮአስም መንግስታቸውን ወረሰ። በዚህ ጊዜ የኢዮአስ እናት ወለተ ቤርሳቤሕ ልክ እንደ ምንትዋብ የንግስትነት ማዕረግ ተሰጥቶኝ ከልጄ ጋር ልግዛ በማለቷ በአማትና ምራት መካከል ታላቅ ክርክርና አለመግባባት ተፈጠረ። በሁለቱ ውዝግብ የአገሪቱ ማዕከላዊ መንግስት ተናጋ። የወለተ ቤርሳቤሕ ደጋፊዎች የነበሩት የየጁ ባለሟሎች ከቋረኞቹ ጋር ትንቅንቅ በመያዛቸው የሁለቱ ወገን ግጭት እየባሰ ሄደ። አጼ እዮአስ አያቱን ምንትዋብን ከመደገፍ ይልቅ የቤርሳቤህና የየጁዎች ወገን ሆኖ ቆመ።
በሂደት የሁለቱ ወጎኖች ግጭት መካረሩን በማየት አጼ ኢዮአስ ራስ ሚካኤልን ከትግሬ አስመጥተው በእንደራሴነት ሾመው በእርሳቸው በኩል ቋረኞችን ለማጥቃት አሰቡ። አስመጥተዋቸውም በመጀመሪያ እጅና ጓንት ሆነው በቋረኞቹ ላይ ተነስተው ነበር። እቴጌ ምንትዋብ በበኩላቸው በሁለቱ መካከል ግጭት እንዲፈጠር በስውርና በብልሃት ይሰሩ ነበር። በኋላም በእቴጌዪቱ የዲፕሎማሲ ስራ ራስ ሚካኤል ከአጼ ኢዮአስ ተጣልተው የእቴጌ ምንትዋብ ወዳጅ ሆኑ። ቆይቶም ሥዑል ሚካኤል ፣ አጼ ኢዮአስ የጁዎችን በጦርነት ደግፏል በሚል ክስ እንዲገደል አደረገ። የእቴጌ ምንትዋብ ጥረት ቋረኞችን ከየጁዎች ጥቃት መከላከል እንጂ ልጃቸውን ለማስገደል ያለመ አልነበረምና የልጃቸው ህይወት በራስ ስዑል ሚካኤል እንደጠፋ ሲያውቁ እጅግ አዘኑ። ቀሪ ህይወታቸውንም ራሳቸው በቆረቆሯት ቁስቋም ቤተክርስቲያን በጾም በጸሎት ተወስነው አሳለፉ። ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩም በዚያው በቁስቋም ማርያም በታላቅ ድምቀት ቀብራቸው ተፈጽሟል::
አዲስ ዘመን ግንቦት 26/2012
የትናየት ፈሩ
እቴጌ ምንትዋብ – ብርሃን ሞገሳ ስትወሳ