የበርካታ ቱሪስቶችን ቀልብ የሚስበውና መዳረሻቸውም እንዲሆን ከሚመኟቸው አካባቢዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አንዱ የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ነው። ይህ በአስደናቂነቱ፣ በታሪካዊነቱና በኪነ ሕንፃ ጥበቡ የሚያስደምም የታሪክ ቅርስና የዘመን አሻራ፤ በ1979 ዓ.ም በዓለም ቅርስነት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተመዝግቧል። በአፄ ፋሲለደስ ግንብ ውስጥ ያሉት ቤተ መንግሥቶች ከ100 በላይ ክፍሎች አሏቸው። ባለ ሦስትና ባለ አራት ፎቅም እንደሆኑ ይነገራል።
ለግንባታውም በዋናነት ድንጋይ፣ ኖራና እንጨት ጥቅም ላይ መዋላቸው ይጠቀሳል። በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች መሠራቱም ይነገርለታል። በአፄ ፋሲለደስ ግንብ ውስጥ ያሉት ቤተ መንግሥቶችን ልዩ የሚያደርጋቸው ነገሥታት የየራሳቸውን አሻራና ታሪክ ለትውልድ ትተው ያለፉባቸው መሆናቸው ነው።
ከቤተ መንግሥቶቹም መካከል የአፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት አንዱና ቀደምቱ ሲሆን፣ ንጉሡ ቤተ መንግሥቱን ለማሳነፅ 10 ዓመታት እንደፈጀባቸው ይነገራል። ሌሎቹ የአፄ ዮሐንስ ቤተ መንግሥት፣ የታላቁ አዲያም ሰገድ እያሱ ቤተመንግሥት፣ የአፄ ዳዊት ቤተመንግሥት፣ የንጉሥ መሲሰገድ በካፋ ቤተ መንግሥት እንዲሁም የእቴጌ ምንትዋብ ቤተ መንግሥት ናቸው።
በአፄ ፋሲል ግቢ ከሚገኙ ሕንፃዎች ትልቁ የአፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት ሲሆን፣ 32 ሜትር ርዝመት እና 3 ፎቆች እንዲሁም የምድር ውስጥ ክፍሎች እንዳሉት ይነገራል። ከመጨረሻ ፎቅ በስተደቡብ ምዕራብ ላይ በከበሮ ቅርፅ የተሠራ ክፍልም አለ። የሕንፃው አራት መዓዘን አናቶች የግማሽ እንቁላል ቅርፅ አላቸው።
ይህ በጎንደር ከተማ የሚገኘው የአፄ ፋሲል ቤተመንግሥት ወይንም የነገሥታት ግቢ ምሽጎችና የቤተመንግሥታት ድንቅ የኪነ ሕንፃ ግንብ ስብስብ ነው። ግቢው የተመሰረተው በ1628 ዓ.ም በዓፄ ፋሲለ ደስ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ይገልጻሉ። ማቀባበያ የሚሰኘው የግቢው አጥር 900 ሜትር ርዝመት ሲኖረው በውስጡ 70 ሺህ ስኩዌር ሜትር የመሬት ይዞታ ያካልላል።
ፋሲል ግቢ፣ የውሃ እጥረት እንዳይገጥመው በማሰብ የተመሰረተው በአንገርብና ቃሃ በተሰኙ ሁለት ምንጮች መካከል ነበር። ከግቢው በስተደቡብ የጎንደር አደባባይ ሲገኝ፣ ቦታው ለገበያነት፣ ለአዋጅ መንገሪያነትና ለወንጀለኛ መቅጫነት ያገለግል ነበር። በአሁኑ ወቅት የጎንደር ከተማ መናፈሻ በመሆን ያገለግላል። ማቀባበያ የሚሰኘው የግቢው አጥር ግንብ በዙሪያው 12 በሮች ሲኖሩት፤ እነዚህ በሮች ግልጋሎታቸውን የሚወክሉ ስያሜ ነበሯቸው። አንዳንዶቹ በሮች ከውጪኛው ዓለም ጋር ይገናኙ የነበሩት በትላልቅ ድልድዮች ነበር። ምንም እንኳ አብዛኞቹ የግቢው ቤቶች በጦርነትና እሳት ቢወድሙም ዋና ዋናዎቹ ሕንፃዎች ግን እስከ አሁኑ ዘመን ዘልቀው ይታያሉ። ከእነዚህ ጉልህ ሕንፃዎች መካከል የፋሲለደስ ግንብ፣ ትንሹ የፋሲል ግንብ፣ የታላቁ እያሱ ግንብ፣ የዳዊት 3ኛ ዙፋን ቤት፣ ምንትዋብ ግንብ፣ የምንትዋብ ቱርክ መዋኛ፣ የፈረሶች ቤት፣ የፈረሰኞች አለቃ ቤት፣ አንበሶች ቤት፣ የበካፋ ግንብ፣ የበካፋ ሰገነት፣ የቀዳማዊ ዮሐንስ ጽሕፈት ቤት፣ ዮሐንስ ቤተ መጻሕፍት፣ አዋጅ መንገሪያን፣ ክረምት ቤት፣ ቋል ቤት (የሠርግ ቤት) እና ግምጃ ቤት ማርያም እንዲሁም አጣጣሚ ሚካኤል የሚሰኙ አብያተ ክርስቲያናት ይግኙበታል።
አዲስ ዘመን ግንቦት 25/2012
አስቴር ኤልያስ
ባለታሪካዊ አሻራው የአፄ ፋሲል ቤተመንግሥት