የኢትዮጵያ አረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ የተመሰረተው በደን ሀብት ልማት ላይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ደን 80 በመቶ ለሚሆኑ በተለይም በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍል ለሚኖሩ ዜጎች የኃይል ምንጭ ነው፡፡ ደንን መሰረት ባደረገው ንብ ማነብ፣ የጫካ ቡና እና ከጣውላ የሚገኘው ምርት የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት 4 በመቶ ድርሻ ይዟል፡፡ በተለይም የአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ ብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ እንዲሁም ለአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሆኑትን ሙቀት አማቂ ጋዞችን በማምከን ረገድ የደን ዘርፉ የማይተካ ሚና አለው፡፡
በኢትዮጵያ የተለመደው የኢኮኖሚ ዕድገት አማራጭ ከቀጠለ እስከ 2022 ዓ.ም ባለው ጊዜ 9 ሚሊዮን ሄክታር ደን ይመነጠራል፡፡ ይህ ደግሞ የአየር ጸባይን በመቀየርና የዝናብ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ እንደ አገር የሚያደርሰው ጉዳት እጅጉን ከባድ ነው። ለአገሪቱ ጤናማ ዕድገት ከፍተኛ ሚና ያለው የደኑን ዘርፍ ጉዳት ለመቀነስ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ስልቶች ተቀይሰዋል፡፡ ዜጎች ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችን እንዲጠቀሙ ማድረግ፤ ከማገዶ ውጪ (በኤሌክትሪክ፣ ባዮጋዝና በተፈጥሮ ጋዝ) የሚሰሩ ምድጃዎች ህብረተሰቡ እንዲጠቀም በማድረግ የደን ምንጠራን ትርጉም ባለው መጠን መከላከል የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂው ሌላው ስልት ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የተጎዱ መሬቶችን በመከለል እንዲያገግሙ ማድረግና ተጨማሪ መሬትን በደን በመሸፈን የደን ልማቱ እንዲስፋፋ የሚያደርጉ ሌሎች ስልቶች ናቸው፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ያለ ታዳጊ ሀገር ኢኮኖሚው ዘላቂ እንዳይሆን ከሚያደርግ አማራጭ በመቆጠብ፤ አስቸጋሪ አማራጭ ቢሆንም የዘላቂ ኢኮኖሚ አማራጭ መጠቀም ቀጣይ ትውልድን ታሳቢ ያደረገ የአርቆ አሳቢዎች አማራጭ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ አረንጓዴ ልማትን ማፋጠን ቀዳሚና አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆኖ ይገኛል። ከእዚህ እውነታ በመነሳትም በአገራችን የነበረውን አረንጓዴነት ወደ ቀደመ ቦታው ለመመለስ እንደ አገር ታላላቅ ሥራዎችን መስራት ከተጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል።
የኢትዮጵያ ሚሊኒየም የተከበረበት የ2000 ዓ.ም በቢሊዮን ችግኞች የመትከል ዘመቻ የተደገፈበት፣ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የሙት ዓመት መታሰቢያዎች ከአረንጓዴ ልማት ጋር የተሳሰሩበትና ከታላቁ ህዳሴ ግድብ የህዝብ ማሳተፊያ መንገዶች አንዱ የአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት መሆኑ አገራችን ለዘርፉ ቀደም ሲል ጀምሮ የሰጠችውን ትኩረት አመላካች ነው። ይህ ጥረት በአዲሱ የለውጥ አመራር የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶት በተለይም ባለፈው ዓመት በክረምቱ ወራት ከአራት ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ከ84 በመቶ በላይ መጽደቃቸው መገለጹ ይታወሳል።
ይህ ስራ በአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ መመራቱ ምን ያህል ትልቅ አገራዊ ትኩረት እንዳገኘ ማረጋገጫ ነው። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመትም በችግኝ ተከላው ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆንና ወደ ቢሯቸው የመጡ ታላላቅ የውጭ አገር መሪዎችን ጭምር በዚህ ታላቅ ተልዕኮ ላይ ማሳተፋቸው ለሥራው ስኬት የበኩሉን አዎንታዊ ሚና አሳርፏል። ሥራው ተከታታይነት ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞም በዘንድሮው ዓመትም እስከ አምስት ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል ዕቅድ መኖሩም በመንግስት ተገልጿል። ለዚህም በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን በማስመልከትም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በቢሾፍቱ ችግኝ ማፍያ ተገኝቼ በመጪው ክረምት ለምናካሂደው የ5 ቢሊዮን ችግኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሚደረገውን ዝግጅት ተመልክቻለሁ፡፡ ፕሪሲሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም እስካሁን የደረስንበት የክንውን ደረጃ የሚደነቅ ሲሆን፤ ሀገራችንን አረንጓዴ ልምላሜ የማልበስ ግባችንን የሚደግፍ ነው” ሲሉ አስታውቀዋል።
በማንኛውም መመዘኛ ሲታይ አረንጓዴ ልማት ለአንድ አገር የኢኮኖሚ ዕድገትና ለህዝቦች የመኖር ህልውና ወሳኝ ነገር ነው። አገራችንም ለዚህ ታላቅ ጉዳይ ቅድሚያ ትኩረት ሰጥታ በተከታታይ እየሰራችው ያለው ሥራ ከአገር አልፎ ለአህጉርና ለዓለም የሚያበረክተው አዎንታዊ ሚና እጅጉን ትልቅ ነው። ይህ ሥራ እስካሁንም የተሳካውና ከዚህም በኋላ የሚፈለገውን ውጤት የሚያሳካው በመላ ኢትዮጵያውያን የላቀ ተሳትፎ ነውና በአንድ በኩል ኮሮናን በጥንቃቄ እየመከትን በሌላ በኩል የአረንጓዴ ልማታችንን ማፋጠን ይገባል።
አዲስ ዘመን ግንቦት 24/2012
ኮሮናን በብቃት እየተከላከልን አገራችንን አረንጓዴ እናድርግ!