አገራችን ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ላለው ተፅዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ናት:: ኢኮኖሚያችን በሚፈለገው ደረጃ ያላደገ በመሆኑም ጊዜ እየቆጠረ የሚከሰተው ድርቅ የሚያሳድረውን ጫናም ሆነ የአየር ንብረት ለውጡን የሚቋቋም አቅምም የለንም::አረንጓዴ አሻራን በማሳረፍ የደን ሽፋንን ማሳደግ የአየር ንብረት ለውጥ እያሳደረ ያለውን ተፅዕኖ ለመቋቋም ዓይነተኛ መፍትሔ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግም ሆነ አመቺ የአየር ንብረትን ጠብቆ ለማቆየት የጎላ ሚና ያለው የኢትዮጵያ የደን ሀብት፣ ለበርካታ ዓመታት ሲመናመን ቆይቷል፡፡
በኢትዮጵያ 80 በመቶ ያህሉ ሕዝቦች በተለይም በገጠር የሚኖሩ ቤተሰቦች ለኃይል አቅርቦት የሚጠቀሙት የማገዶ እንጨትን ነው::ከአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት አራት በመቶ ያህሉን የሚይዙት ማር፣ የጫካ ቡናና የጣውላ እንጨትም የደን ትሩፋቶች ናቸው:: ለአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ የካርበን ልቀትን ለመምጠጥ፣ ለብዝኃ ሕይወት፣ ለመሬት ምርታማነትና ለሰው ልጅ ጤንነት፣ ለማኅበራዊ ኢኮኖሚው ከፍተኛ አበርክቶ ያላቸው የኢትዮጵያ ደኖች ለበርካታ ዓመታት በመኖርና ባለመኖር ሂደት ውስጥ ሲመላለሱ ኖረዋል:: የሕዝቡ የቀደመ ዛፍ የመትከል ባህል ላይ መንግሥታት በየዘመናቸው ደኖች እንዳይመናመኑ ጥረት ሲያደርጉ ቢቆዩም፣ የኢትዮጵያ ደኖች ከመራቆት ግን አልዳኑም፡፡
እያደገ የመጣው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ተጨማሪ ማገዶና የእርሻ ቦታ የሚፈልግ ነው:: የደን ጭፍጨፋንና መመናመንን አባብሷል:: በመሆኑም የኢትዮጵያ ደኖች መልሰው እንዲያገግሙ ብሎም እንዲጨምሩ ማድረግና ባህላዊውን የደን ልማት አሠራር መቀየር ካልተቻለ፣ ኢትዮጵያ እስከ 2030 ድረስ ዘጠኝ ሚሊዮን ሔክታር መሬቷ ይመነጠራል፣ ዓመታዊ የማገዶ ፍጆታዋም በ65 በመቶ ይጨምራል፡፡
ይህንን እውነታ መሰረት በማድረግ ቀደም ሲልም ጀምሮ በየዓመቱ የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ሥራዎችን በመስራትና ደንን በመትከል የኢትዮጵያን አረንጓዴነት ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። ከዚህም ጋር ተያይዞ መልካም የሚባሉ ውጤቶችም ተመዝግበዋል። ይሁንና የተሰራው ሥራ ከችግሩ ጋር ሲነጻጸር ፈጽሞ የሚመጣጠን አልነበረም። ስለሆነም አሁን አገሪቱን በመምራት ላይ የሚገኘው የለውጥ አመራር ቅድሚያ ትኩረት ከሰጣቸው ዓበይት አገራዊ ጉዳዮች አንዱ ኢትዮጵያን አረንጓዴ
ማድረግ የሚል ሆኗል።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ዓብይ አህመድ በአንድ ወቅት የሚከተለውን ብለው ነበር። “እውነት ነው ሀገራችን ለምለም ነበረች ዛሬ ግን አይደለችም፤ ምክንያቱም አባቶቻችን ያቆዩልንን እኛም በተራችን ለልጆቻችን አላቆየንምና። እናም ልምላሜዋን እና አረንጓዴ ውበቷን ከትዝታ ብቻ አወዳጅተን አደራችንን በልተናል::ዜማዎቻችን ብቻ ሳይሆኑ ተረቶቻችንም ሀገራችን በደን የተሞላች እንደነበረች ይነግሩናል::በተረቶቻችን ውስጥ የምናገኛቸውን ብዙዎቹን እንስሳት ዛሬ በአካባቢያችን አናገኛቸውም::በየቋንቋችን ስማቸው ብቻ የቀረው የዛፍ ዓይነቶች ሀገራችን ዓይነተ ብዙ ደን እንደነበራት ቋሚ ምስክሮች ናቸው::የዛፎች ጉዳይ ለእኛ የውበት ጉዳይ ብቻ አይደለም::የህልውና ጉዳይ ነው፤ የእምነት ጉዳይ ነው፤ የባህል ጉዳይ ነው፤ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው! እኛ ማለት ያለ ዛፍ ምንም ነን፡፡”
ከዚህ መሰረታዊ እውነታ በመነሳትና ለመጪው ትውልድ አረንጓዴዋን ኢትዮጵያ ለማውረስ ታላቅ አገራዊ ፋይዳ ያላቸው ሥራዎች በተለይም ካለፈው ዓመት ጀምሮ በመሰራት ላይ ናቸው። በአገራችን ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት 4 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ወደ ትግበራ ተገብቶ ነበር። በዚህ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አንድ ሰው 40 ችግኞችን እንዲተክል በማድረግ አፈጻጸሙ ከዕቅድ በላይ እንዲሆን ተደርጓል። የዚሁ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካል በሆነ ‹‹አረንጓዴ አሻራ›› በሚል መርህ በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮን ችግኞች የሚተከሉበት መርሐ ግብር ሀምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በመላ አገሪቱ ተካሂዶ በአንድ ጀምበር ከ300 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ደማቅ ታሪክ ለመጻፍ ተችሏል። ባለፈው ዓመት ከተተከሉ ችግኞች ከ84 በመቶ በላይ መጽደቃቸውም በቅርቡ መገለጹ በዘርፉ ምን ያህል ስኬታማ ሥራ እንደተሰራ አመላካች ነው።
ዘንድሮም ከአምስት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ለመትከልና በመጪዎቹ ዓመታትም 20 ቢሊዮን ችግኝ በመትከል ኢትዮጵያን አረንጓዴ ለማድረግ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። ከባለፈው ዓመት ልምድ በመነሳትም ይህ ሥራ በስኬት እንደሚፈጸም ምንም የሚያጠራጥር ነገር አይኖርም። ይልቁኑ ከሁላችን የሚጠበቀው ራስን፣ ቤተሰብንና ወገንን ከኮሮና በመጠበቅ ለምንናፍቃት አረንጓዴ ኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራችንን ማሳረፍ ይሆናል!
አዲስ ዘመን ግንቦት 19/2012
አረንጓዴዋን ኢትዮጵያ ለመመለስ!