የመኪና የፊቱ መስታወት ሰፊ ሆኖ ሳለ ከኋላ ያለውን እንቅስቃሴ የምንቆጣጠርበት መስታወት ደግሞ ጠባብ እና አናሳ መሆኑ ከዚህ መቅሰም የምንችለው ትምህርት ምን ሊሆን ይችላል? መጪው ጊዜ ካለፈው በተለየ መልኩ አስፈላጊና አሳሳቢ መሆኑን ያሳያል። ትኩረትህን ከሞላ ጎደል ወደፊት አድርግ። ያለፈውን ግዜ መማሪያ እንጂ በትርጉም አልባ ፀፀት መጠበሻ ምዕራፍ እንዲሆን መፍቀድ የለብህም። ካለፈው ሙሉ በሙሉ ተፀፅተህ የነገን ብሩህ ተስፋ መመልከት የሚያስችል አቅም መላበስ ሲገባህ መጪውን እንዳታይ አይንህን በፀፀት መጋረጃ አትሸፍነው። ምንም ወንጀል ብትፈፅም ከመሃሪዎች ሁሉ ምህረተ-ሰፊ የሆነው ፈጣሪ በሩን ላይዘጋ ቃል ከገባ፣ አንተ በራስህ ሰዓት ለምን ትዘጋዋለህ? ከኋላ የነበረውን በመመልከት የምትወጠር ከሆነ ወደፊት ያለውን አጓጊ ነገር ማግኘት አትችልም። መልካም ነገሮችን ማጣት ብቻም ሳይሆን መልካም ነገሮችን ለመፈለግ አንተ በምታሽከረክርበት የህይወት ጎዳና በተቃራኒው አቅጣጫ የሚመጡ አካላት ጋር ትላተማለህ። እነርሱ መጪው ናፍቋቸው ከአደጋው ለመሸሽ ጥረት ሲያደርጉ አንተ ግን ከእነርሱ ጋር ትጋጫለህ። አይንህ የሚመለከተው ከፊት ቢሆንም ትኩረትህ ግን ጠባቧ መስታወት ላይ ስለሆነ ከትርፍህ ይልቅ ኪሳራህን ታበዛለህ።
እንግዲህ ህጋዊ የሆነ የህይወት መንጃ ፈቃድ ይኖርህ ዘንድ በቂ ስልጠና መውሰድ ይጠበቅብሃል። ያለፈው ላይ የሙጥኝ እያልክ የፊቱን መመልከት እንዳትችል እንቅፋት የሆነብህን ጉዳይ መቀነስ የሚያስችል ተግባር ተኮር ስልጠና መውሰድህ የግድ ነው። ከስኬት – አልባነት ዑደት በስተጀርባ ካሉ ቁልፍ ምክንያቶች መካከል ዋነኛው ባለፈ ጉዳይ ላይ አለቅጥ ተመስጦ መጪውን ጊዜ መስጋት ነው። ፈሶ የተነነን ውሃ ለማፈስ የሚደረግ ትንቅንቅ ትርፉ ድካም ነው። ከራስ ጋር ከመላተም ውጭ ምንም አይነት ፋይዳ አያስገኝም። በእጅህ ያለው ቀሪ ውሃ ዳግም እንዳይፈስ ከባለፈው መማር እንጂ የፈሰሰውን ማፈስ አይቻልም። ከፊትህ ያለውን ሰፊ ዓለም በሰፊው መስታወት መመልከት ሲገባህ ተሻግረህ የመጣኸውን ዓለም በጠባቧ መስታወት በልዩ ሁኔታ መቃኘትህ አይመከርም – አንተ ወደፊት ተጓዥ እንጂ ተመላሽ አይደለህምና።
ላትመለስ ከሄድክ የመጣህበት አባጣ ጎርባጣ መንገድ በተመሳሳይ መልኩ ከፊት ስለሚጠብቅህ ያለፈው ውድቀትህን በመጪው ጎዳናህ ላይ መማሪያ ይሆን ዘንድ በጨረፍታ አስታውሰው። እንዲህ ስልህ፣ ከፊት ላለው መጪ ዘመን የተለየ ትኩረት ስጥ ማለቴ እንጂ ጭራሽ የኋላውን አትመልከት የሚል እንድምታ ያለው ሃሳብ እንዳትይዝ። አልፎ አልፎ ከኋላ ያለውን ያለፈ ህይወት ለመመልከት አይንህን ጣል አድርገው። ለመጪው ስኬትህ የኋላው ተሞኩሮህ ግብዓት ነውና። መጨውን ጊዜ ናፍቀህ ያለፈው ድክመትህ እንዳይደገም ስትጥር የናፈቅከውን ወቅት በጊዜ ታገኘዋለህ። መጪው ዘመን ያንተ የወጣቱ ነው። ሙሉ እይታህን ሰፊው መስታወት ላይ በማድረግ አልፎ አልፎ ጠባቧን መስታወትም እየሰለልክ ጊዜህን ተጠቀምበት። ይህ ወጣትነት በሁለት ድክመቶች መካከል ያለ ጥንካሬ ነው – በልጅነት እና በእርጅና። ዛሬ ላይ ልጅነትህ ታሪክ ብቻ ነው። ወጣትነትህም እንደ ልጅነትህ ታሪክ ብቻ ለመሆን የቀረው ጊዜ ደግሞ ኢምንት ነው ።
የተሰጠነው የተስፋ ጉልበት ይበልጥ ሃይል ያገኝ ዘንድ አንድ ቅመም ያስፈልገዋል። በመልካም ስራ መጠመድ። ይህን ለማረጋገጥ አዛውንቶችን ጠይቃቸው። ሰማኒያ ዓመት ኖረው ስምንት ሰከንድ የቆዩ እንዳልመሰላቸው ይነግሩሃል። ወደ ሞት ጥርስ በተጠጉ ቁጥር ባሳለፉት የእድሜ ሀዲድ ላይ በመመለስ የሰሩትን የመልካምና ክፉ ተግባር መዝገብ በመፈተሽ ይጠመዳሉ። የህሊና ማህደር ደግሞ መዝግቦ ያስቀመጠውን የታሪክ እውነታ ቅልብጭ አድርጎ ከማሳየት ስለማይታቀብ ክፉና በጎ ተግባራቸውን በረድፍ ያሳያቸዋል።
ወጣት ሆነህ “ወይኔ የልጅነት ጊዜ እንዴት ይሮጣል” ብትልም ሌላ የመኖር ተስፋ ከፊትህ እንዳለ ታምናለህ። ምርኩዝ የመያዝ ፀጋውን ስትሰጥ ግን የምታልመው ተስፋ ይበናል። አካልህን ወደዚህች ምድር ላመጣህ አካል ለመመለስ ሞት ጋር ውይይት ትጀምራለህ እንጂ ሌላ የእድሜ እርካብ እረግጣለሁ ብለህ አታስብም። ምናልባት አንድ እንደ ጉም የማይጨበጥ ተስፋ ትሰንቅ ይሆናል። “ምነው ዛሬ ወጣትነት ተመልሶ ቢመጣ ኖሮ!” እያልክ በሃሳብ ትባዝናለህ። በተሳፈርክበት የእድሜ መኪና ህግ ደግሞ ወደፊት መጓዝ እንጂ ወደኋላ መመለስ አይፈቀድም። እርጅና ላይ ሆነህ ደግሞ ልጅነትን እንደማትመኝ ልብ ትላለህ። እርጅና እና ልጅነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸውና። እኩል ናቸው። ሁለቱም ድክመቶች ናቸው። የሰው እገዛ የሚሹ የዕድሜ እርከኖች። ለዚያም ነው በቅርብ ርቀት ላይ ያሳለፍከውን ጣፋጭ የ”ወጣትነት” ጊዜ ቢመለስልህ የምትመኘው። ያጠፋኸውን ለማልማት፣ አልምቻለሁ ብለህ ያሰብከውን የበለጠ ለማጎልበት። አሁንም ግን ጊዜው አልረፈደም። ፈጣሪ በሩን ሁሌም ክፍት አድርጓል። በጎ ለመሆን እና በጎ ስራ ለመስራትም እዛው እርጅና ላይ ሆነህ መፈፀም ትችላለህ። ነገር ግን የትጋትህ ምንጭ የሆኑትን መንፈስና አካላዊ ጥንካሬህን እያጣህ ስለመጣህ በወጣነት ጊዜህ ከምትከውነው ተግባር አንፃር ይህኛው ውስን ነው። ምርኩዝ ጋር ነህ። ወጣትነትን “ቻው” ካልከው በኋላ የመጣህበት ጎዳና በጣም ረጅም ነው። አድካሚ የህይወት ጎዳና። አካላዊና መንፈሳዊ ጥንካሬህን ሁሉ እንደ ሸንኮራ አገዳ ልጣጭ መጦ የጣለ መንገድ። መሆን የሚጠበቅብህን ሳትሆን የመጣህበት ጎዳና።
ሰው በምድራዊ ውሎው ከፍተኛ የህይወት ሃላፊነት የሚሸከመው በወጣትነት እድሜው ነው። በሁለት ድክመቶች መካከል ያለ ጥንካሬ ነውና። ይህ ለሰው ልጅ ከአምላኩ የተቸረው ከባድ ፀጋ ነው። ከዕድሜ እርከኖች መካከል አንዱ ቢሆንም ከሁሉም የተለየ ነው። እነዚህን ጥያቄዎች መጠየቅ ግድ ነው። ከጥያቄዎቹ መካከል ከተነሳሁበት ዓላማ አንፃር ሁለቱ በተለየ መልኩ ይዛመዳሉ፡- አድሜህን በምን እንዳሳለፍክ እና የወጣትነት ጊዜህን በምን መልኩ እንደተጠቀምክበት፡፡
እነዚህ ላንተ የሚቀርቡልህ ጥያቄዎች ናቸው። ጥያቄዎቹ ትኩረትን ይስባሉ። ወጣትነት <እድሜ> በሚለው ማዕቀፍ ውስጥ የሚካተት ሆኖ ሳለ እንዴት ለብቻው ተነጥሎ በጥያቄ መልክ ሊቀርብ ቻለ የሚል ጥያቄ ያጭራል። አዎ! ወጣትነት ከዕድሜዎች ሁሉ በተለየ መልኩ ትልቅ ሃላፊነት የምንሸከምበት ወቅት ስለሆነ ነው። በሁለት ድክመቶች መካከል ያለ የህይወት ጥንካሬ ነው። ወጣትነት ቤቱን ደግፎ እንደሚሸከም ምሰሶ ነው።
የእድሜያችን አብይ ንዑስ ክፍል ነው። የህይወት ወሳኝ ምዕራፍ ነው። ብዙ ነገሮች ይገለጡበታል። እሳት ነው – ይለበልባል። እውር ነው – መጪውን አሻግሮ ላለማየት የስሜት ግንብ ይዘረጋል። ዛሬ በስሜት ስትነድ ነገ በፀፀት መንደድህን አሻግረህ እንዳትመለከት የሚያስችል የሽንገላ መነፅር የሚከመርበት የህይወት ክፍል ነው። ይህን እሳት ማለዘብ ችለው ወቅቱን በመጠቀም በሚጓዙበት የህይወት ጎዳና ላይ መልካም ዘር የሚጥሉ ወጣቶች፣ ነገ እርጅና ሲጫጫናቸው የዘሩት ዘር ፍሬ አፍርቶ ስንቅ ይሆናቸዋል።
አዲስ ዘመን ግንቦት 14/2012
ግርማ መንግሥቴ
ክብር አየልኝ
(ሳይክ-ኢን-አክሽን ክበብ፤ ሳይኮሎጂ ት/ቤት አ.አ.ዩ)
ወደፊት አሻግረህ ተመልከት