በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ዙሪያ የሚነሱ የፍትሀዊ ተጠቃሚነት ጉዳዮች አዲስ አይደሉም። በዓለማችን በቁጥር ትንሽ የማይባሉ ወንዞች ሰው ሰራሽ የሆነውን የሀገራት ድንበር እየተሻገሩ ወደ ባህር ሲፈሱ ኖረዋል ፤ አሁንም ይፈሳሉ ፤ ወደፊትም የተለየ ነገር ይፈጠራል ተብሎ አይገመትም ። በተለያዩ ወቅቶች በነዚህ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ሀገራት ተወዛግበዋል ። ይህንን ተከትሎም ችግሩን ለዘለቄታው ለመፍታት የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች የውሃ አጠቃቀም ዓለም አቀፍ ህጎች ተዘጋጅተው ተግባራዊ ሆነዋል ።
ህጎቹ በዋነኛነት መሰረት ያደረጉት የውሃውን አጠቃቀም ፍትሀዊነት ማረጋገጥ፣ የተፈጥሮ ሀብት የግጭት ሳይሆን የጋራ ተጠቃሚነት ማእከል እንዲሆን ማስቻል ነው ። ከዚህ አንጻር ዓለም አቀፍ ህጉን መሰረት ባደረገ መልኩ ብዙ አለመግባባቶች ተፈትተዋል ።ቀደም ሲል ያለመግባባት ምንጭ የነበሩ ወንዞችም የጋራ ልማትና የትብብር መሰረት ሆነዋል ።
ይህ ተጨባጭ ዓለም አቀፍ እውነታ በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ውሃ አጠቃቀም ዙሪያ የተቀመጡ ዓለም አቀፍ ህጎች በውሃ አጠቃቀም ዙሪያ የሚፈጠሩ ውዝግቦችን የመፍታት አቅም እንዳላቸው ብቻ ሳይሆን አቅማቸው ተፈትኖ ውጤታማ መሆናቸውን ጭምር አመላካች ነው።
በአባይ ውሃ አጠቃቀም ዙሪያ በተፋሰሱ ሀገራት መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችም ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኙ የሚችሉት እነዚህኑ ዓለም አቀፍ ህጎች መሰረት በማድረግ እንደሚሆን ለመገመት የሚከብድ ጉዳይ አይደለም ።የህጎቹ ዝርዝር ትርጓሜ ውስጥ ሳንገባ እንኳን ህጎቹ በመርህ ከተገዙለት ፍትሀዊ ተጠቃሚነት አንጻር ስናየው በተፋሰሱ ሀገራት መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን ለዘለቄታው ለመፍታት ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ትልቁ የመደራደሪያ አጀንዳ ሊሆን ይገባል ።
ከዚህ ውጭ የሕግን /የፍትሀዊነትን / ጥያቄ ወደ ጥግ አስቀምጦ በተፋሰሱ ሀገራት መካከል ለሚነሱ ጥያቄዎች ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ የሚደረጉ ጥረቶች በየትኛውም መስፈርት ዘላቂ መፍትሄ ሆነው ሊቀጥሉ አይችልም ።የመፍትሄ ሀሳብም ሆነው የድርድር መድረኮችን ማጣበብ አይጠበቅባቸውም ። ጊዜ ለማባከንና ዓለም አቀፉን ህብረተሰብ ለማዛናጋት ካልሆነ በስተቀርም በሀገራቱና በህዝቦቻቸው መካከል መተማመንን በመፍጠር የወንዙን ውሃ ለጋራ ተጠቃሚነት ማልማትን አያስችልም ።
ይህንን እውነታ የግብጽ መንግሥት ሆነ የግብጽን መንግሥት የተሳሳተ የችግር አፈታት መንገድ በመደገፍ ላይ ያሉ ሀገራትና መንግሥታት በአግባቡ ሊያስተውሉት የሚገባው ነው ። በአባይ ወንዝ የውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ያሉ አለመግባባቶች ለዘለቄታው ሊፈቱ የሚችሉት በተቀመጡ ዓለም አቀፍ ህጎች መሰረት ብቻ እና ብቻ ነው ።
ዓለም አቀፍ ህጎች የተዘጋጁበት አንዱና ዋንኛው ምክንያት ህዝቦች ወደ አልተገባ ግጭቶች በመሄድ በዓለም ሰላም ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ከማሳደር ባለፈ የህዝቦችን በሰላም የመኖር ፍጥረታዊ መብት ለማስከበር ጭምር ነው ። በግጭቶች የሚገኝ ተጠቃሚነት ውሎ ሲያድር ተጠቃሚ ነኝ ብሎ ለሚያምነውም አካል/ቡድን/ ይዞት የሚመጣው የከፋ ኪሳራ ከግምት የሚያልፍ አይደለም ። የቅርቡን የዓለም ታሪክ ማየት ብቻ በቂ ነው ። ለጊዜው ያተረፉ የመሰላቸው በመጨረሻ ምን እንዳጋጠማቸው ዓለም ዋጋ ከፍሎ መታዘብ ችሏል።
ዓለምን ከግጭትና ከሁከት ፤ ካለመረጋጋትና ከስጋት ለማውጣት ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ እራሱ ላወጣቸው ህጎች ተገዥ መሆን ይጠበቅበታል።እነዚህ ህጎች ብቸኛ የችግርና ያለመግባባቶች መፍቻ አቅሞቻችን ናቸው ። በህጉ ፊት ደግሞ ሁልም እኩል ነው ።
አለመግባባቶችን ለዘለቄታው መፍታት የሚስችል የተፈተኑና ውጤታማ የሆኑ ዓለም አቀፍ ህጎች ባሉበት በዚህ ዘመን ፣ እነዚህን ህጎች ቦታ በማሳጣት ከህጎቹ የተሻሉ አማራጮች ያሉ እስኪመስሉ ድረስ ዓለም አቀፍ መድረኮች ማጣበብ ከማስተዛዘቡ ባለፈ በየትኛውም መመዘኛ መፍትሄ አማጭ ሊሆን አይችልም ።
የአባይ ውሀ አጠቃቀም ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች ማንም ያንሳቸው ማን ጥያቄዎች የሚፈቱት ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ተስማምቶ ባስቀመጣቸው የህግ አግባቦች ብቻ ነው ።ከዚህ ውጪ በአንድ በኩል ጥያቄዎችን በማግዘፍ፣ በሌላ በኩል ለግዝፈት ያልተገቡ ጥያቄዎች ያልተገቡ የመፍትሄ አማራጮችን በማቅረብ፣ ለጥቄዎች መልስ ለመስጠት መሞከር ሊያስከትል የሚችለው አደጋ የከፋ ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም።
ከዚህ አንጻር የግብጽ መንግሥት በአባይ ውሀ ተጠቃሚነት ዙሪያ እያነሳ ያለውን ጥያቄና ለጥያቄው ምላሽ ለማግኘት እየሄደበት ያለው መንገድ በየትኛውም መመዘኛ አለመግባባቱን ለዘለቄታው ለመፍታት የሚያስችል እንዳልሆነ ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ በአግባቡ ሊያስተውለው ይገባል ።ለጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚያደርጋቸውም ጥረቶች ይህንኑ ታሳቢ ሊያደርጉ ይገባል። አለመግባባቶችን ለዘለቄታው ለመፍታት መተኪያ የሌለው መፍትሄ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማስፈን ፣ ለዚህ የሚሆን በቂ ዝግጁነት መፍጠር ነው።
አዲስ ዘመን ግንቦት 12/2012
አለመግባባቶችን ለዘለቄታው ለመፍታት