በአገሪቱ እየታየ ያለው የከተሞች መስፋፋት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ስለመምጣቱ አይካድም። ይሁንና ክተማው ተገቢውን መስፈርትና አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት እየተከናወነ ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። ከዚህ አንጻር ደግሞ መሰራት የተገባቸው በርካታ ተግባራ እንዳሉ ይስተዋላልና በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን እንዲያጋሩን የጠየቅናቸው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ አቶ ተስፋዬ ወልደሚካኤልን አነጋግረናል።
እርሳቸውም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ የ10 ዓመት መሪ ዕቅድን መሰረት አድርገው፤ በቅድሚያ የገጠር የልማት ማዕከላት ቀጣይ ከተሞች እንደሚሆኑ ማለም ያስፈልጋል ብለዋል። በከተሞች ለኢንዱስትራላይዜሽን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ተገቢ መሆኑንም ይገልጻሉ። የከተማ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ማሳደግና የተመጣጠነና ፍትሃዊ አከታተም ማጠናከርም ወሳኝ እንደሆነ ያመላክታሉ።
የገጠር የልማት ማዕከላት ቀጣይ ከተሞች እንደሚሆኑ አልሞ መገንባትን አስመልክተውም እንዳስረዱት፤ ባለፉት ዓመታት የአገሪቱን ኢኮኖሚ በአማካይ 10 በመቶ እያደገ የመጣ መሆኑ እሙን ነው። ለዚህ እድገት ከተማን መሠረት ያደረጉ ዘርፎች (ኢንዱስትሪ፣ ኮንስትራክሽንና አገልግሎት የመሳሰሉት) ድርሻቸው በፍጥነት እያደገ የመጣ ቢሆንም የግብርናው ዘርፍ አሁንም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል። ከፕላንና ልማት ኮሚሽን በተገኘ መረጃ መሠረት ከ2003 እስከ 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ የግብርናው ዘርፍ በአማካይ 5 ነጥብ 7 በመቶ በማደግ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።
በግብርናው ዘርፍ እድገት ምክንያት በርካታ የገጠር መንደሮችና የማስፋፊያ አካባቢዎች በፈጣን ሁኔታ ወደ ከተማነት እየተለወጡ መጥተዋል፤ በቀጣይም መምጣታቸው አይቀርም። በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በገጠር የተሻሻሉ መሠረተ ልማቶችና ማህበራዊ አገልግሎቶች በመዘርጋታቸው፣ የገጠሩ ነዋሪ የገቢ አቅም እየጨመረ በመምጣቱ የአርሶ አደሩ እና የአርብቶ አደሩ ኑሮ እየተሻሻለ መጥቷል።
የገጠር የልማት ማዕከላት እና በተሰባሰቡ የአርብቶ አደር መንደሮች ዘመናዊ የሆኑ ቤቶችና የሌሎች አገልግሎቶች ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል። ይህ ፍላጎትና ዝንባሌ በፍጥነት እያደገ እንደሚመጣ የሚገመት ከመሆኑም በላይ እነዚህ የገጠርና የልማት ማዕከላት ለገጠር ቴክኖሎጂ አገልግሎት መስፋፋት ያላቸው ቁልፍ ሚና እጅግ ወሳኝ ነው።
በሌላ በኩል የገጠር የልማት ማዕከላትን መሠረት በማድረግ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ የሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች የአካባቢ የዕድገት አቅጣጫን የሚጠቁም በቀላሉ መሠረተ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማካተት የሚያስችል የአሰፋፈር ሥርዓትን ይዘው እንዲያድጉ የዕድገት ፕላን ማዕቀፍ ያስፈልጋቸዋል። በዚህም መሠረት ታዳጊ የገጠር ልማት ማዕከላት በሂደት ወደ ከተማነት የሚያደርጉትን ሽግግር ለማገዝ የሚያስችል አሰፋፈርን የሚያበረታታ፣ የገጠር-ከተማን እንዲሁም የከተማ-ከተማ ትስስርን የሚያጠናክር ሥርዓት ያለው አኗኗር በመፍጠር ሕብረተሰቡን ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
አማካሪው የአስር ዓመት መሪ እቅዱን መሰረት አድርገው እንደገለጹት፤ ከዚህም በተጨማሪ ማዕከላቱን የገበያ፣ የአገልግሎት (ትምህርትና የጤና አገልግሎት፣ መጋዘኖችና ወፍጮ ቤቶች፣ የዕምነት ቦታና የመሳሰሉት) እና የአነስተኛ አግሮ ኢንዱስትሪ ማዕከላት እንዲሆኑ በማድረግ የአካባቢያቸውን ልማት በማፋጠን በኩል ያላቸውን ድርሻ ማሳደግ ይገባል። ከዚህም ውጭ ተደራሽ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን (መንገድ፣ ውሃ፣ መብራት፣ ስልክ) በማስፋፋት ማዕከላቱ ነዋሪዎችን የሚስቡና ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ ተገቢ ነው። ከዚህ አንፃር የአገሪቱ ልማት ዋና ዓላማ የሕዝቡን አጠቃላይ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻልና የሕዝቡን የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ ሲሆን፣ የመኖሪያ ቤት ሁኔታም አንዱ የልማት አመላካችና መሠረታዊ ከሆኑ ፍላጎቶች አንዱ ነው።
አቶ ተስፋዬ፣ በከተሞች ለኢንዱስትራላይዜሽን ምቹ ሁኔታ የመፍጠር አስፈላጊነትንም አስመልክተው እንዳስረዱት ከሆነ፤ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ትራንስፎ ርሜሽን ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ለማሻገር ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ምርታማነት ደረጃ ላይ የደረሰ ዘመናዊ ግብርናና በኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነት ሚናን መጫወት የሚችልበት ደረጃ ላይ የደረሰ የአገልግሎትና የኢንዱስትሪ ዘርፍን መገንባት፣ ፈጣን፣ ቀጣይና ፍትሃዊ ኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
የዜጐች የነፍስ ወከፍ ዓመታዊ ገቢም ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ማሰለፍ ጊዜ የሚሰጠው ተግባር አይደለም። በተመሳሳይ መልኩ ፈጣንና ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት በማስፈን ዘርፉ ቀስ በቀስ ኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነት ሚና እንዲጫወት ማድረግ ያስፈልጋል ። በመሆኑም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማስፋፋት፤ መካከለኛና ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን ዕድገት በመደገፍ የኢኮኖሚ መዋቅር ሽግግር ለማምጣት የኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚኖረውን ሚና በላቀ ደረጃ ማሳደግ የሚጠይቅ ይሆናል ይላሉ።
የኢኮኖሚ መዋቅር ሽግግር ለማምጣትና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለመሰለፍ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ከአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት ወደ 35 ነጥብ 9 በመቶ ድርሻ እንደሚኖረውና ከዚህ ውስጥም 17 በመቶ የአምራች ኢንዱስትሪ ድርሻ እንደሚሆን ታሳቢ ተደርጓል። የአገልግሎት ዘርፍ ወደ 42 ነጥብ 1 በመቶ እና የግብርናው ዘርፍ ድርሻ ወደ 22 በመቶ ዝቅ ይላል። በዚሁ መሰረት በቀጣይነት የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት በዘርፉ የሚታዩ የቴክኖሎጂ አቅም መዋቅራዊ ችግሮችን መፍታት፤ ተጨማሪ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ፤ ገበያ ማስፋፋት፤ የግብዓት አቅርቦት ማሳደግ እንዲሁም የሰራተኛውና የኢንዱስትሪ አመራሩን ክህሎት ማዳበር ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው።
አማካሪው፤ በኢንዱስትሪ ከተሞች ልማት የሚታቀፉት ጥቃቅንና አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች በእሴት ጭማሪ ሂደት በሚኖራቸው ትስስር የኢኮኖሚ መዋቅር ሽግግሩን በማፋጠን ረገድ ከፍተኛ እገዛ ይኖራቸዋል ይላሉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሚገነቡት ኢንዱስትሪ ከተሞች አካባቢ በቂ፣ መሰረተ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት የተሟላላት መሬት ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግም ያመለክታሉ። ይህም እርምጃ ለከተማ ልማትና ለኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ወሳኝ ድርሻ ስለሚኖረው ለከተማ ልማት ሥራ ቀጣይ አንዱ መነሻ እንደሚሆን ይጠቅሳሉ።
የከተማ ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን የማሳደግ አስፈላጊነትንም በተመለከተ እንደሚገልጹት፤ ከተሞች ተወዳዳሪና ምርታማ ለመሆን ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ከተጠቀሙ፣ በቂና ደረጃውን የጠበቀ መሠረተ ልማትና አገልግሎት ማቅረብ ይችላሉ። በተጨማሪም ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራር እና አደረጃጀት ሲኖራቸው፤ ምርታማና ታታሪ ዜጋ ማፍራትና ለሁሉም ተደራሽ ሆነው ደህንነታቸው የተረጋገጠ ሲሆኑ ብቻ ተወዳዳሪነትን ያገኛሉ ይላሉ።
‹‹ሥራ ወዳድና ታታሪ ህዝብ የሚፈጠረው ደግሞ ከተሞቻችን በአስተሳሰቡ የዳበረ፣ በዕውቀትና ክህሎት ላይ የተመሰረተ ለአካባቢውም ሆነ ለአገሪቱ የማያቋርጥ ዕድገት መሰረት የሚሆን የተማረ ህብረተሰብ የሚፈጠርባቸው የብልጽግና ማዕከላት ሲሆኑ ነው›› የሚሉት አቶ ተስፋዬ፤ ስለዚህ የትምህርት ዘርፍ ዋናው የምርታማነት ማበልጸጊያ መስክ በመሆኑ በከተሞች ለሚከናወኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ያለውን ከፍተኛ ሚና በላቀ ደረጃና ፍጥነት ለማሳደግ መረባረብ እንደሚገባ ያመለክታሉ።
የትምህርት ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድግ ዕውቀት፣ ክህሎትና አስተሳሰቡ የዳበረ ህብረተሰብ በመፍጠር ለአገሪቱ ርዕይ ስኬት መረጋገጥ ዋስትና መሆኑን በመረዳትም በሁሉም ከተማ ሥራ ማለትም በመሬት ልማትና አቅርቦት፤ በመሰረተ ልማት አቅርቦት እና በመሳሰሉት የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ በህዝብ ተሳትፎ የሚፈጸም ይሆናል ብለዋል።
በከተሞች ደረጃቸውን የጠበቁ የመሰረተ ልማትና የከተማ አገልግሎት አቅርቦት አንዱና መሰረታዊ ፋይዳ ለበሽታ ተጋላጭ ያልሆነ፤ ጤናማና ምርታማነቱ የተረጋገጠ ህብረተሰብ ለመፍጠር ነው። ንጽህናው የተጠበቀ፣ በቂ መዝናኛና የመሰረተ ልማትና አገልግሎት ማሟላትና ተደራሽነት ማረጋገጥ፣ የተሟላ ጤና አገልግሎት ማስፋፋትና ማጠናከር ምርታማነቱ የተረጋገጠ ዜጋ ለመፍጠር ቁልፍ መሳሪያ ነው። ስለዚህ ለነዋሪዎቻቸውም ይሁን ለእንግዶች፣ ለሥራና ለመዝናኛ ምቹ የሆኑ ከተሞችን በማልማት ደህንነቱ የተጠበቀ ህብረተሰብ በመፍጠር ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ማረጋገጥ የቀጣይ ሥራቸው አንዱ መነሻ እንደሆነ አስረድተዋል።
አማካሪው የተመጣጠነና ፍትሃዊ አከታተም የማጠናከር አስፈላጊነትን በተመለከተም ሲያስረዱ፤ በአገሪቱ የተመጣጠነ ፍትሃዊ የአከታተም ሥርዓት ማጠናከር ሲባል በአገር ደረጃ እንዲሁም በክልሎች በትልልቅ፤ መካከለኛና አነስተኛ ከተሞች መካከል ያለውን የህዝብ ብዛት ልዩነት በተነፃፃሪ ተመጣጣኝ እንዲሆን እና በእያንዳንዱ የመጠን ክልል ያለው የከተሞች ብዛትም የተመጣጠነ ተዋረድ እንዲኖረው በማድረግ ጤነኛ የሆነ የአከታተም ተዋረድ መፍጠር ማለት ነው ብለዋል። ከትማው ሚዛን ያልጠበቀ ትልቁ ከተማ ከሚቀጥሉት ከተሞች በአስር እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን፣ መካከለኛ እርከን የሚታየው ከተሞች ደግሞ በስፋት አነስተኛ እርከን ከተሞች በተመሳሳይ ምጣኔ የተራራቁ ናቸው።
አሰፋፈራቸውም መንገድን የተከተለ ሲሆን፣ አገራዊ ሚዛንም በሚያሳይ መልክ አይደለም። ይህ እንዳለ ሆኖ ካለፉት አሥር ዓመታት ወዲህ የአነስተኛ ከተሞቹ ዕድገት ፍጥነት ከከፍተኞቹ ዕድገት ፍጥነት የበለጠ ስለሆነ የማመጣጠን ዝንባሌ እያሳየ ነው። የማመጣጠን ምልክት ታየ እንጂ በበቂ ደረጃ የማስተካከል ሥራው ባለመከናወኑ አሁንም ክፍተቱ ሰፊ ጥረት የሚጠይቅ ነው። በመሆኑም ይህን ጤናማ ያልሆነ የአከታተም ሥርዓት ለማስተካከል በአገራዊ የከተማ ልማት ስፓሻል ፕላን ጥናት መሠረት በክልል ደረጃ እንዲሁም በአካባቢ ደረጃ የሚኖረው የአከታተም ሥርዓት በመፍጠር የተመጣጠነና እርስ በእርስ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ከባቢያዊ ልማት የሚመጋገብና የተቀናጀ የአከታተም ሥርዓት በቀጣይ እንዲፈጠር ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
አዲስ ዘመን ግንቦት 11/2012
አስቴር ኤልያስ
የቀጣይ ክተማ ትልም