አዲስ አበባ፡- በአማራ ከልል ምእራብ ጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ከህብረተሰቡ፣ ከመስተዳድሩና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ የደህንነትና ሰላም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌ ገለጹ፡፡
ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት፤ ሰሞኑን ከጭልጋ ወጣ ብሎ ከአይከል ወደ ሰባት ኪሎሜትር ርቀት በሚገኙ ሦስት ቀበሌዎች በቅማንት ስም በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ጥቃት ተፈጽሟል፡፡ በእዚህም 200 ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡ ከ2 ሺ ያላነሰ ሰው ተፈናቅሏል፡፡ 55 ሰው ሕይወቱ አልፏል፡፡ ቀደም ብሎም ገንዳ ውሃ አካባቢ መንገድ ይሰራ የነበረው ሱር ኮንስትራክሽን የተባለው ድርጅት ንብረቱን ከስፍራው ሲያስወጣ በተፈጠረ አለመግባባት ስድስት ሰው ሞቷል፡፡
እንደ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ገለጻ፤ ተመሳሳይ የሆነ የጥፋት እርምጃ ሊወስዱ የነበሩ የተደራጁና የታጠቁ ኃይሎች አንድ ቦታ ላይ መሽገው ተገኝተው ሙሉ በሙሉ እርምጃ ተወስዷል፡፡ የኃይል ስምሪቱ ለፀጥታ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን የመቆጣጠር ሥራ ጀምሯል፤ ውጤትም ታይቶበታል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት የፀጥታ ኃይሉ ከሚወስደው እርምጃ ባሻገር ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር እየተሰራ ነው፡፡ ሕዝቡ የጀመረውን የሰላም ሂደት አጠናክሮ እንዲቀጥል እየተደረገ ሲሆን፤ የሀገር ሽማግሌዎች ለመፍትሄ እየመከሩ ይገኛሉ፡፡
‹‹ሕዝቡ አንድ የነበረ ነው፡፡ አንዳንዶች የማንን አጀንዳ ነው እያስፈጸሙ ነው የሚለውን ነገር እየተረዳው ነው›› ያሉት ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው፤ ህብረ ተሰቡ ችግሩን በው ይይት ለመፍታት የሚያ ጋጥሙትን እክሎች ሁሉ ተቋቁሞ በችግሮቹና በመፍት ሄዎቹ ዙሪያ በየቀ በሌው እየመከረ መሆኑን አመ ልክተዋል፡፡ በቅርቡም ወደ መግባባት ይደረሳል ተብሎ እንደሚ ታሰብ ጠቁመዋል፡፡
አዲስ ዘመን ጥር 10/2011
ወንድወሰን መኮንን