ዓለምን ለቀውስ የዳረገው የኮሮና ቫይረስ የጋዜጠኞችንና የቤተሰባቸውን ሕይወት ምስቅልቅል እያወጣ እንደሆነም እየተነገረ ነው። በተለይም ከሥራ ባህሪያቸው አኳያ ጋዜጠኞች ቀዳሚ ተጠቂ እየሆኑ ስለመምጣታቸው እየተነገረ ነው። ባለፈው ሳምንት በተከበረው የዓለም አቀፉ የነፃው ፕሬስ ድርጅት እንደተገለፀው፤ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ማርች 03 ቀን 2020 ዓ.ም ላይ አንድ አርጀንቲናዊ ጋዜጠኛ በቦነስ አይረስ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ እንደተጠቃ ከተገለፀ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ጋዜጠኞች ሕይወታቸው እንዳለፈ አሳውቋል።
ዘንድሮ በተከበረው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ከመከበሩ አስቀድሞ መቀመጫውን ጄኔቫ ያደረገውና ለብዙኃን መገናኛዎች (ጋዜጠኞች ተቋርቋሪ የሆነው በምህጻረ ቃሉ ‘ፔክ’ (PEC – Press Emblem Campaign) የተባለው ድርጅት እንደተናገረው፤ ጋዜጠኞች የዓለማችንን ቀውስ አስመልክቶ መረጃ ለማድረስ ሲሉ ራሳቸውን ለቫይረሱ እያጋለጡ እንደሚገኙና እንዲጠነቀቁ በእጅጉ አሳስቧል። ዳሩ ግን ፈተና የተሞላበት የጋዜጠኞች ሕይወት እንዲሁ በቃላት የሚገለጸውን ያክል ቀላል አልሆነም።
ፔክ’ (PEC – Press Emblem Campaign) የተባለው ድርጅት እንዳሳወቀው በባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ብቻ ቁጥራቸው 55 የሚሆኑ ጋዜጠኞች ሕይወታቸው እንዳለፈ ገልጿል። እነዚህ የ23 ሀገራት ጋዜጠኞች በእርግጠኝነት ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው እንዳለፈ እርግጠኛ
መሆን ባይቻልም በአመዛኙ ግን ይኸው የቫይረስ ጣጣ መሆኑን ደግሞ አሳሳቢነቱን ከፍ ያለ ስለመሆኑ አመላካች ነው።
ጋዜጠኞች በተለይም ቫይረሱ በደንብ ባልተሰራጨበት ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የነበሩ ናቸው የሚለው ማብራሪያው፤ በዚህ ጊዜ የቫይረሱ ስርጭትና ባህሪ እምብዛም ትኩረት ስላልተሰጠው ጋዜጠኞቹ በአመዛኙ መከላከያ ቁሳቁሶችን ባለመጠቀም እና ጥንቃቄዎችን ባለመተግበር ወደተለያዩ የሕክምና ተቋማት፣ የምርምርና ጥናት አጥኚዎች እንዲሁም ወደተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ለዘገባ በሚሄዱበት ጊዜ ለጉዳት መዳረጋቸውን ያትታል። ታዲያ በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ጋዜጠኞች ክፉኛ መጎዳታቸው አይቀሬ ሆኗል።
በከፍተኛ ደረጃ ጋዜጠኞችን በሞት ያጣችው ሀገር ኢኳዶር ስትሆን ዘጠኝ ባለሙያዎቿን በሞት ተነጥቃለች። አሜሪካ ደግሞ ስምንት ጋዜጠኞችን አጥታለች። ብራዚል አራት፣ እንግሊዝና ስፔን እያንዳንዳቸው ሦስት ጋዜጠኞችን ያጡ ሲሆን ይህም በዓለም ዙሪያ እጅጉን አሳሳቢ አንደሆነ ያመላክታል። አፍሪካም ቢሆን በዚህ ቫይረስ ፍዳዋን እየበላች ሲሆን፤ በ30ዎቹ መጀመሪያ የሚገኘው የዙምባብዌው ጋዜጠኛ ህልፈት ሕይወትም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።
እስከአሁን ድረስ የዓለማችንን ከሦስት ሚሊዮን በላይ ሕዝቦችን ያጠቃውና ወደ ሩብ ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት የነጠቀው ኮሮና ቫይረስ በመገናኛ ብዙኃን እና ባለሙያዎቹ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳረፈ ይገኛል። በዚህም የተነሳ ፔክ’ (PEC – Press Emblem Cam¬paign) የተባለው ድርጅት ስጋቱን እየገለፀ የሚገኝ
ሲሆን፤ ለጋዜጠኞች ትኩረት እንዲሰጥ ይመክራል።
ኮሮና ቫይረስ ለዓለም ስጋት መሆኑ ከታወጀበ በኋላ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ ሀገራት ብዙኃን መገናኛዎቹን ሳንሱር የማድረግ፣ ኢንተርኔት የማቆራረጥ፣ ጋዜጠኞችን በማሰር፣ በባለሙያዎች ላይ የተለያዩ አካላዊና የቃል ጥቃቶችን በማድረስ እንዲሁም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥም የመረጃ ገደቦችን እያደረሱ ይገኛሉ ሲል አሳውቋል። ድርጅቱ እንዳሳሰበው “በዚህ ወቅት ለሕዝቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚያስፈልገው ወቅታዊና የተጣራ መረጃ እንደመሆኑ ብዙኃን መገናኛዎቹ በግልፅነት እንዲሰሩና የዓለም የጤና ቀውስ የሆነውን ኮሮና ቫይረስ መከላከል እንዲቻል ብዙኃን መገናኛው ምቹ ሁኔታ ያስፈልገዋል ሲል ያሳስባል።
በመሆኑም ‹‹ለዓለም ጤና ቀውስ ግልጽነት እጅግ አስፈላጊ እንዲሁም ሕይወት አድን የሆነ ባለፍቱን መላ ነው›› ብሏል። በእርግጥ አሁን ባለው ሁኔታ ቫይረሱ ዓለም እያዳረሰ ሲሆን ከሥራ ባህሪያቸው አኳያ ሐኪሞች ጋዜጠኞችና የፀጥታ ኃይሎች በተለያዩ እንደሀገር በሚፈጠሩ ቀውሶች ተጋላጭነታቸው የሰፋ ነው። ታዲያ እነዚህን ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት በተቻለ አቅም የተለየ ትኩረት ተሰጥቷቸው እንደሀገር ጥንቃቄ ሊደረግላቸው ይገባል። ጋዜጠኞችም ቢሆኑ ራሳቸውን ከችግሩ ለማዳን የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ ግድ ይላል።
አዲስ ዘመን ግንቦት 1/2012
ፈተና ውስጥ የገባው የጋዜጠኞች ሕይወት