ከሳምንት በፊት ምርጫ ቦርድ ምርጫውን በተያዘለት ጊዜ ማካሄድ እንደማይችል አሳወቀ፡፡የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም የቦርዱን ጥያቄ በአብላጫ ድምጽ ተቀበለ፡፡ ቀጥሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ሰብስበው ምርጫውን ለማራዘም የሚያስችሉ አራት አማራጮችን አቀረቡ:: ይህን ጊዜ የፖለቲካ ቁማርን ከሟርት ያዳበሉ ‹‹ቁ-ሟርተኞች›› ከያሉበት የመጨረሻ ካርዳቸውን መዝዘው ብቅ አሉ፡፡
የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከሁለት ቀን በፊት መግለጫ አውጥቷል፡፡ መግቢያው ላይ “በክልላችንና በሀገራችን እንዲሁም በንኡስ ቀጣናው የተከሰቱ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በስፋት በመመርመር የውሳኔ ሃሳቦችን አሳልፈናል” ይበል እንጂ ውሳኔዎቹ የትኛውን አገርና ንዑስ ቀጣና ነው የመረመሩት የሚያሰኙ ናቸው፡፡ ሌሎች የህጋዊነት ጥያቄዎችን ትተን ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ በርካታ ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተገደቡበት ወቅት ምርጫ ለማካሄድ አመቺ ተደርጎ መወሰዱ ሳይወዱ ያስፈግጋል፡፡
እንደ ህውሓት ሟርት ከሆነ አገሪቱ የለየለት የጥፋት አደጋ ተጋርጦባታል፡፡ ይህን መታደግ የሚቻለው ደግሞ ምርጫውን ቀደም ሲል በተያዘው ጊዜ በማካሄድ ብቻ ነው፡፡ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 102 ምርጫን ማካሄድ የፌዴራል መንግስትና የምርጫ ቦርድ ሥልጣንና ተግባር መሆኑ በግልጽ ተደንግጓል:: ስለዚህ ከቦርዱ እውቅና ውጪ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ኢ-ህገ መንግስታዊ ናቸው። አንድ ፖለቲከኛ እንዳሉት ፣ ህ.ወ.ሓ.ት ያለ ምርጫ ቦርድ እውቅና ክልላዊ ምርጫ ቀርቶ ድርጅታዊ ጉባኤ አድርጎ አመራሮቹን መቀየር እንኳን አይችልም። ምርጫ ማካሄድ የሚችልበት ህጋዊ መሰረት ሳይኖረው ከቀኗ ፍንክች አልልም የሚል ግትር አቋም መያዙን ስታይ ፣ ምርጫው እንደ አክስዮን ሽያጭ በተደጋጋሚ የተራዘመ ሊመስልህ ይችላል:: የተለመደ ቁማሩ እንደሆነ የሚገባህ ጥንተ አፈጣጠሩን ስታጠና ነው፡፡
‹‹ቁ-ሟርተኛው›› ህወሓት አይኑን በጨው አጥቦ በመግለጫው “በሀገር ደረጃ እየተካሄደ መጥቶ አሁን በመጨረሻ ደረጃ ላይ የደረሰውን ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓት የመናድ ዘመቻ …” እያለ ሲደሰኩር ለተተኪው በማሰብ ሳይንድ ያስቀረው የሕገ መንግስት አንቀጽ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ በፓርቲው ሊቀ መንበር ቀጭን ትዕዛዝ ብቻ ኮሽ ሳይል ሕገ መንግስትን የሚያህል ነገር ማሻሻሉን “ዘንግቶ” ዛሬ “ፓርቲዎች በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ እየተደረገ አይደለም” እያለ ይቆምራል፡፡ ድፍረቱ ልክ የለውምና በግምገማ ስም እያሸማቀቃቸው አፋኝ ህጎችን በሙሉ ድምጽ እንዲያጸድቁ ሲያስገድዳቸው ለነበሩት የህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት “በጠራራ ፀሃይ ህገ-መንግስታዊ ሥርዓት ለማፍረስ የሚደረገውን እኩይ ተግባር በማስቆም ከታሪክ ተጠያቂነት ራሳችሁን አርቁ” ሲል ጥሪ ያቀርባል:: ይህ ሁሉ ስልጣንን በማጣት ስጋት ወስጥ ሆኖ የመጨረሻ ዕድልን ለመሞከር የሚደረግ ትርጉም የሌለው መወራጨት ነው፡፡
ሌላው ‹‹ቁ-ሟርተኛ›› 97 ላይ የጠለፈውን ገመድ 15 ዓመት ሙሉ ሳይሻገር ጠዋት ማታ ስለሽግግር መንግስት ያወራል፡፡ አንድ እንጉርጉሮ ለኀዘንም፣ ለደስታም፣ ለጦርነትም ሊውል እንደማይችል ሁሉ አንድ መፍትሄ የሁሉም አይነት ችግር መፍቻ ቁልፍ ሊሆን አይችልም:: ከ97 ቁጥር ጋር ለተቋጠረው ‹‹ቁ-ሟርተኛ›› ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠር ችግር ሁሉ መድኃኒቱ “የሽግግር መንግስት መመስረት” ነው:: በስልጣን አምሮት ፍም ሆኖ እኔ ያልኩት ካልሆነ በሚል ድምጸት “መንግስት ለብቻው ወስኖ አገር ለመምራት እንዳሰበ በቂ መረጃ አለን ። መንግስት ይሄን ድርድር ችላ ብሎ ለብቻው ቢወስን ከባድ ቀውስ ይፈጠራል” እያለ ያስፈራራል::
የ97ቱ ሰው “መንግስት የህገ መንግስት ማሻሻያ ማድረግ ይችላል” ይላል፡፡ ቀጠል አድርጎ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ እንዲሆን ከፈቀዱ በስልጣን ለመቆየት ሲሉ ሕገ መንግስት ካሻሻሉት አምባገነን የአፍሪካ መሪዎች አንዱ ይሆናሉ ሲል ይቆምራል፡፡ የአፍሪካ መሪዎች የሚታወቁት እኮ “አንድ ፕሬዚደንት አገር መምራት የሚችለው ለሁለት ዙር ነው” የሚል አንቀጽን በማሻሻል ነው:: ሁለተኛ የስልጣን ዘመናቸውን ለማጠናቀቅ የወራት ዕድሜ ሲቀራቸው አንቀጹ “አራት ዙር” እንዲል ያደርጉታል፡፡ በማያፈናፍን ወረርሽኝ ምክንያት ምርጫን ማካሄድ ሳይቻል ሲቀር ሕገ መንግስት ማሻሻልን እንደ አንድ አማራጭ ማየት እንዴት አምባገነን እንደሚያሰኝ የሚያውቀው ተናጋሪው ብቻ ነው፡፡ ፍቅር ሰክረው በሚጫወቱት ቁማር አራምባና ቆቦ መርገጣቸው ሊያስገርመን አይገባም፡፡ ሕገመንግስቱን “ሥልጣንን ለማራዘም ምንም ዓይነት ቀዳዳ እንዳይኖር በደንብ ታስቦበት ዝግ የተደረገ ነው” ብለው ሲያንቆለጳጵሱት ትሰማለህ፡፡ ነገር ግን ለቁማር ስለማይመች ያወደሱት ሕገመንግስት ራሱን አርሞ የመፍትሔ ምንጭ እንዲሆን አይፈልጉም፡፡ “በህግ-አግባብ የሚመጣ መፍትሔ ስለሌለ ብቸኛው አማራጭ ፖለቲካዊ መፍትሔ ነው” ይሉሃል፡፡ በአጭሩ በኮሮና ምክንያት ምርጫ ማካሄድ አለመቻሉን እንደ ወርቃማ ዕድል በመቁጠር በአቋራጭ ስልጣን ላይ ለመውጣት የሚችሉትንም የማይችሉትንም ቋጥኝ ፈንቅለው ተራራ ጫፍ ላይ ወጥተዋል፡፡ ቋጥኙን ቁልቁል ወደ ህዝቡ ለመልቅም ደጋግመው ያስተዋወቁትን መስከረም 30 እየተጠባበቁ ነው፡፡
ራሱን “ባላደራ” እያለ የሚጠራው ስብስብ ደግሞ “አደራ” የሚል ቃል ላይ ተለክፎ “የባለአደራ መንግስት ይቋቋም” ሲል መግለጫ አውጥቷል:: ያልተጣለበትን አደራ ለመወጣት አስር ጊዜ መግለጫ በማውጣት የሚታወቀው ይህ ቡድን ታምር ተፈጥሮ አገር የመምራት ዕድል ቢገጥመው የሕጎች ሁሉ የበላይ ሕግ የሚሆነው ‹‹መግለጫ›› ብቻ ይመስለኛል፡፡ “ባላደራው” በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ መግለጫ ካላወጣሁ ምርጫ ቦርድ የሰጠኝን ጊዜያዊ ሰርቲፍኬት ይነጥቀኛል ብሎ የሚሰጋ ምስኪን ይመስላል፡፡
የኮሮና ወረርሽኝን ከነ መፈጠሩ በዘነጋበት በሰሞኑ መግለጫው “ከመስከረም 30 ቀን 2013ዓ.ም በኋላ ለኢትዮጵያ የሚበጃት የባለሙያዎች የባለአደራ መንግሥት ነው:: በገዢው ፓርቲ በኩል የቀረቡት አራት አማራጮችም ሆኑ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተሰባሰባሰቡ ኃይሎች ያቀረቡት “የሽግግር መንግሥት እንመስርት” ጥያቄ ለሀገሪቱ አይበጅም” ብሏል፡፡
“በአውሮፓ፣ እስያ፣ ላቲን አሜሪካና አፍሪካ ባሉት ተሞክሮዎች አዋጪነቱ ተፈትኖ የታየ” ሲል ያሞካሸውን አማራጩን ዋነኛ ጠቀሜታ ሲያትት “ገዢው ፓርቲም ይሁን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሀገራዊ ተግዳሮቱን በመጠቀም ለስልጣን ሽሚያ እንዳይጋበዙ ዋስትና ይሰጣል” ይልሃል:: ከመግለጫው የተነጠቀችው ይህች ዓረፍተ ነገር ብቻ “ባላደራው” አደራውን አሽቀንጥሮ ስልጣን ላይ ማነጣጠሩን ትረዳለህ:: ላይ ላዩን ሲታይ የተለየ አማራጭ ያቀረበ ይምሰል እንጂ እርሱም የተከተለው “ዶሮ ብታልም ጥሬዋን” የሚያሰኘውን አቋራጭ የስልጣን መንገድ ነው፡፡
እንደ እኔ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 83 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ምርጫውን ለማራዘም የሚያስችሉትን የሕገ መንግስቱን አንቀጾች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲተረጉም መወሰኑ የተሻለ አማራጭ ነው፡፡
በበርካታ የዳቦ ስሞች በመጠራት ሪከርድ የያዘው ስመ ብዙ ‹‹ቁ-ሟርተኛም››፤ “ተከበብኩ” የሚል ፉጨቱን ተማምኖ “ብቸኛው አማራጭ ድርድር ነው። መንግስት እምቢ ብሎ በሃይል እንዳለው ካደረገ የሚፈጠረውን የምናየው ይሆናል” ሲል ይፎክራል፡፡ ታዲያ ባለንበት ወቅት የፖለቲካ ድርድር ብቸኛ አማራጭ የሚሆነው ወደ ስልጣን መንደርደር ለሚፈልጉ ወገኖች መሆኑ ጠፍቶት አይደለም፡፡
ቀን ቆርጦ በማስጮህ ታክቲክ የበርካቶች ህይወት እንዲቀጠፍ በማድረግ የኢትዮጵያውያንን ደም ያንተከተከው “ታክቲከኛ” አሁንም አላረፈም:: ከመስከረም 30 በኋላ “መከላከያ አይታዘዝም ፤ ፖሊስ አይታዘዝም ፤ ዜጋ አይታዘዝም ፤ በትግራይ ክልል የተጀመረው ነገር ወደ ሌሎች ክልሎች ይዛመታል” ብሎ የአመጽ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
የማይታረቅ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ይዘው አንድ ጠረጴዛ ላይ የተገኙት ሁለቱ ‹‹ቁ-ሟርተኞች›› እየተፈራረቁ ከመስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ ቀውስ ይፈጠራል ሲሉ አሟርተዋል፡፡እንደሚታወቀው የሁለቱም ግብ አራት ኪሎ መግባት ነው፡፡ ስለዚህ በስልጣን ፍቅር ሰክረው በሚጫወቱት ቁማር አራምባና ቆቦ መርገጣቸው ሊያስገርመን አይገባም፡፡ ሕገመንግስቱን “ሥልጣንን ለማራዘም ምንም ዓይነት ቀዳዳ እንዳይኖር በደንብ ታስቦበት ዝግ የተደረገ ነው” ብለው ሲያንቆለጳጵሱት ትሰማለህ፡፡ ነገር ግን ለቁማር ስለማይመች ያወደሱት ሕገመንግስት ራሱን አርሞ የመፍትሔ ምንጭ እንዲሆን አይፈልጉም፡፡ “በህግ-አግባብ የሚመጣ መፍትሔ ስለሌለ ብቸኛው አማራጭ ፖለቲካዊ መፍትሔ ነው” ይሉሃል፡፡ በአጭሩ በኮሮና ምክንያት ምርጫ ማካሄድ አለመቻሉን እንደ ወርቃማ ዕድል በመቁጠር በአቋራጭ ስልጣን ላይ ለመውጣት የሚችሉትንም የማይችሉትንም ቋጥኝ ፈንቅለው ተራራ ጫፍ ላይ ወጥተዋል፡፡ ቋጥኙን ቁልቁል ወደ ህዝቡ ለመልቅም ደጋግመው ያስተዋወቁትን መስከረም 30 እየተጠባበቁ ነው፡፡
ራሱን “ባላደራ” እያለ የሚጠራው ስብስብ ደግሞ “አደራ” የሚል ቃል ላይ ተለክፎ “የባለአደራ መንግስት ይቋቋም” ሲል መግለጫ አውጥቷል:: ያልተጣለበትን አደራ ለመወጣት አስር ጊዜ መግለጫ በማውጣት የሚታወቀው ይህ ቡድን ታምር ተፈጥሮ አገር የመምራት ዕድል ቢገጥመው የሕጎች ሁሉ የበላይ ሕግ የሚሆነው ‹‹መግለጫ›› ብቻ ይመስለኛል፡፡ “ባላደራው” በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ መግለጫ ካላወጣሁ ምርጫ ቦርድ የሰጠኝን ጊዜያዊ ሰርቲፍኬት ይነጥቀኛል ብሎ የሚሰጋ ምስኪን ይመስላል፡፡
የኮሮና ወረርሽኝን ከነ መፈጠሩ በዘነጋበት በሰሞኑ መግለጫው “ከመስከረም 30 ቀን 2013ዓ.ም በኋላ ለኢትዮጵያ የሚበጃት የባለሙያዎች የባለአደራ መንግሥት ነው:: በገዢው ፓርቲ በኩል የቀረቡት አራት አማራጮችም ሆኑ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተሰባሰባሰቡ ኃይሎች ያቀረቡት “የሽግግር መንግሥት እንመስርት” ጥያቄ ለሀገሪቱ አይበጅም” ብሏል፡፡
“በአውሮፓ፣ እስያ፣ ላቲን አሜሪካና አፍሪካ ባሉት ተሞክሮዎች አዋጪነቱ ተፈትኖ የታየ” ሲል ያሞካሸውን አማራጩን ዋነኛ ጠቀሜታ ሲያትት “ገዢው ፓርቲም ይሁን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሀገራዊ ተግዳሮቱን በመጠቀም ለስልጣን ሽሚያ እንዳይጋበዙ ዋስትና ይሰጣል” ይልሃል:: ከመግለጫው በተነጠቀችው በዚህች ዓረፍተ ነገር ብቻ “ባላደራው” አደራውን አሽቀንጥሮ ስልጣን ላይ ማነጣጠሩን ትረዳለህ:: ላይ ላዩን ሲታይ የተለየ አማራጭ ያቀረበ ይምሰል እንጂ እርሱም የተከተለው “ዶሮ ብታልም ጥሬዋን” የሚያሰኘውን አቋራጭ የስልጣን መንገድ ነው፡፡
እንደ እኔ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 83 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ምርጫውን ለማራዘም የሚያስችሉትን የሕገ መንግስቱን አንቀጾች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲተረጉም መወሰኑ የተሻለ አማራጭ ነው፡፡
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 28/2012
የትናየት ፈሩ